Get Mystery Box with random crypto!

በጦርነት ይብቃ ሰላም ይፅና መርሃግብር ላይ ጌታቸው ረዳ የተናገረው 'የፕሪቶሪያው የሰላም ስምም | Muktarovich Ousmanova

በጦርነት ይብቃ
ሰላም ይፅና መርሃግብር ላይ ጌታቸው ረዳ የተናገረው

"የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲፋጠን የጠሚ አብይ አህመድ ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው። አሁንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈጣን እርምጃዎች የተጀመረውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ መስራት አለበት እላለሁ።

የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል። ከማንም ጋር ጦርነት መግባት አንፈልግም። ከአማራም ከአፋርም የሚያቀራርብ እንጂ የሚያቃቅር ነገር የለንም።

ትናንት በአፋር በኩል የሰላም ባስ አገር አቋራጭ አልፏል። ሐጂ አወል ይህንን ለማጠናከር መስራት ይገበዋል።

በተመሳሳይ ከአማራ ክልል ጋር በተያያዘም ዶክተር ከፋለ ኃላፊነት ወስደህ መስራት አለብህ ለማለት እፈልጋለሁ።

ዶክተር አብይ በጀመረው እጁ በሌሎች አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን በሆደ ሰፊነት ለመፍታት መስራት እንደለበት ለመጠቆም እፈልጋለሁ!

በመጨረሻ ከይዋጣልን መንፈስ ወጥተን የፍቅር፣ የስራ ቋንቋ መጀመር አለብን። ሰላም እንዲፀና የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መንግስት የበኩሉን ይሰራል"

አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መስተዳድር ፕሬዚደንት