Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ኹለት ቢሊዮን ዶላር ብድር ትሻለች በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም | Muktarovich Ousmanova

ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ኹለት ቢሊዮን ዶላር ብድር ትሻለች

በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም መሠረት፣ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት/አይኤምኤፍ/፣ ኹለት ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት በመወያየት ላይ እንደኾነች፣ ሮይተርስ የተቋሙን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።

ከውይይቱ ምስጢራዊነት የተነሣ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አራት የሮይተርስ ምንጮች፣ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና የተቋሙ ሓላፊዎች እያደረጉ በሚገኙት ውይይት፣ አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የመበደር ዐቅም እየገመገመ መኾኑን ተናግረዋል።

በተቋሙ ግምገማ፣ እአአ እስከ 2026 ባለው ጊዜ ውስጥ፣ ኢትዮጵያ ቢያንስ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ያህል የገንዘብ እጥረት ሊገጥማት እንደሚችል፣ ለውይይቱ ቅርበት ያላቸው ኹለት ምንጮች ለሮይተርስ ገልጸዋል፡፡ አሁን በግምገማ ላይ ያለው የብድር ጥያቄ ቢሳካላት እንኳ፣ ኢትዮጵያ አራት ቢሊዮን ዶላር እጥረት ሊያጋጥማት እንደሚችል፣ ቅድመ ትንበያ ተቀምጧል።