Get Mystery Box with random crypto!

በኬንያ ክርስቶስን ቶሎ ለማግኘት በረሃብ አድማ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ በኬንያ | Muktarovich Ousmanova

በኬንያ ክርስቶስን ቶሎ ለማግኘት በረሃብ አድማ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

በኬንያ የባህር ጠረፍ ኪሊፊ አውራጃ አራት ሰዎች ህይወታቸው አልፈው የተገኙ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ክፉኛ መጎዳታቸው የተሰማ ሲሆን የምግብ አድማ በማድረግ የዓለምን ፍጻሜ ሲጠባበቁ እንደነበረ ተጠቁመሟማ። ፖሊስ እንዳስታወቀው ለተከታታይ ቀናት ባጫካ ውስጥ ግለሰቦቹ በፃም "ኢየሱስን ለማግኘት እንዲጠበቁ በኃይማኖት አባት" ከተነገራቸው በኋላ ይህው ድርጊት አጋጥሟል።

ፖሊስ ባደረገው የነፍስ አድን ጥረት 11 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ችሏል። በህይወት ከተረፉት መካከል ስድስቱ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በከፋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል ። ሌሎች የቀሩ ሰዎች በጫካ ውስጥ እንዳሉ መነገሩን ተከትሎ ፖሊስ ዛሬ ጠዋት ተጨማሪ ኃይል በማሰማራት ፍለጋ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ፖሊስ በጫካው ውስጥ በቅርብ ቀናት የተቀብሩ ሰዎች አስክሬን ማግኘቱን አስታውቋል። ግለሰቦቹ ፈጥነው ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመድረስ በረሃብ እንዲሞቱ ያደረገው የጉድ ኒውስ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን መሪ መሆኑ ተነግሯል።

#ዳጉ_ጆርናል