Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮ 251 ሚዲያ ስቱዲዮ በፀጥታ ኃይሎች ከበባ ላይ መሆኑ ተገለፀ። ሚያዝያ 05 ቀን 201 | Muktarovich Ousmanova

የኢትዮ 251 ሚዲያ ስቱዲዮ በፀጥታ ኃይሎች ከበባ ላይ መሆኑ ተገለፀ።

ሚያዝያ 05 ቀን 2015 ዓ.ም


አራት ኪሎ "ድንቅ ሥራ ኮምፕሌክስ" ህንጻ ላይ የሚገኘው የኢትዮ 251 ሚዲያ በፀጥታ ኃይሎች ከበባ እንደተፈፀመበት የአይን እማኞች ከቦታው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጸዋል።

ከበባውን የፈፀሙት የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ አባላት እንደሆኑ እና አሁንም ድረስ 8ተኛ ፎቅ ላይ እንደሚገኙ የመረጃ ምንጮቻችን ተናግረዋል።

መጋቢት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ኢትዮ 251 ሚዲያ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሚዲያው ዘረፋ እንደተፈፀመበት ይታወቃል።

ከበባ የተፈፀመበት የኢትዮ 251 ሚዲያ ስቱዲዮ አራት ኪሎ ሚዲያ እና ነገር ወልቃይት ሚዲያ በጋራ የሚጠቀሙበት መሆኑ ይታወቃል።

የነገረ ወልቃይት ሚዲያ የበላይ ኃላፊ ዶ/ር አሰፋ አዳነ በአዲስ አበባ መታሰራቸው ይታወቃል። የአራት ኪሎ ሚዲያ መሥራችና ባለቤት እንዲሁም አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በትላንትናው ዕለት በመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የደህንነት ሰዎች ታፍኖ የት እንደደረሰ ማወቅ አልተቻለም ሲል አሚማ ዘግቧል።

አሻራ ሚዲያ