Get Mystery Box with random crypto!

በቆቦው ግጭት ኹለት የካቶሊክ ርዳታ ሠራተኞች ተገደሉ source VOA በኢትዮጵያ የአማራ ክልል | Muktarovich Ousmanova

በቆቦው ግጭት ኹለት የካቶሊክ ርዳታ ሠራተኞች ተገደሉ
source VOA
በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ውስጥ፣ የመንግሥትን የልዩ ኃይል መዋቅራዊ ለውጥ ውሳኔ በመቃወም በተቀሰቀሰው ሁከት፣ ኹለት የካቶሊክ ርዳታ ሰጪ ሠራተኞች መገደላቸውን፣ የርዳታ ቡድኑ አስታወቀ።

ሠራተኞቹ የተገደሉት፣ ባለፈው እሑድ እንደነበረ የጠቀሰው አሶሽየትድ ፕሬስ፣ መንግሥት በአገሪቱ የሚገኙ የ11 ክልሎች ልዩ ኃይሎችን መዋቅር አፍርሶ ወደ ፌዴራል ኃይሎች ለመቀላቀል ያሳለፈው ውሳኔ፣ ሕዝባዊ ዐመፅ መቀስቀሱን በዘግባው አመልክቷል።

በኢትዮጵያ ላለፉት 60 ዓመታት ሲንቀሳቀስ መቆየቱን የገለጸው የርዳታ ቡድኑ በአወጣው መግለጫ፣ ቹል ቶንጊክ የተባለው የጸጥታ መኰንኑና አማረ ክንደያ የተባለ አሽከርካሪ፣ እሑድ ዕለት ወደ ዐዲስ አበባ በመመለስ ላይ እያሉ “በጥይት ተመተው ተገድለዋል” ያለ ሲኾን፣ ስለ ግድያው ዝርዝር መረጃ አለመኖሩን ገልጿል።

በጉዳዩ አሳሳቢነት ምክንያት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሦስት የሰብአዊ ርዳታ ሓላፊዎች ለአሶሽየትድ ፕሬስ እንደተናገሩት፣ ግድያው የተፈጸመው፥ ባለፈው እሑድ፣ በቆቦ ከተማ አቅራቢያ፣ በፌዴራሉ የመከላከያ ሠራዊት እና በአማራ ክልል ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው።