Get Mystery Box with random crypto!

ወላጅ አባቱን በዘነዘና ቀጥቅጦ የገደለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት ተቀጣ፡፡ በከምባታ ጠም | Muktarovich Ousmanova

ወላጅ አባቱን በዘነዘና ቀጥቅጦ የገደለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት ተቀጣ፡፡

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሌሾ ማዞሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጉንጃ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ወላጅ አባቱን የገደለው አቶ መሐሩ ዮሐንስ የተባለ ግለሰብ ነው የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ የወሰነው፡፡

ተከሳሽ መሐሩ የሐንስ የተባለ በከምባታ ጠምባሮ ዞን በሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሌሾ ማዞሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጉንጃ ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ሟች ዮሐንስ ኬዕሚሶ የተባለ አባቱን የሰበሰብከውን ንብረት አትበላም ብሎ ስዝት ቆይቶ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ሟች ተኝቶ ባለበት በዘነዘና ጭንቅላቱን በመቀጥቀጥ ገድሏል ተብሎ በወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ ላይ የቀረበበትን ክስ አቃቤ ህግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጦ ተከሳሽ ክሱን እንዲያስተባብል ታዞ መከላከያ ማስረጃ የሌለው መሆኑን በጽሑፍና በቃል ማስረጃ የለኝም ብሎ በማረጋገጡ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት 03/08/2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ከምባታ ጠምባሮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ