Get Mystery Box with random crypto!

አርቲስት ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተገናኘ ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ባለሙያ ቴ | Muktarovich Ousmanova

አርቲስት ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተገናኘ

ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ባለሙያ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑትን አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተገናኙ።

አምባሳደር አለልኝ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ከአርቲስት ቴዲ አፍሮ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ እና እስራኤልን የባህል ግንኙነት ስለማሳደግ ተወያይተናል ብለዋል። የባህል ግንኙነቱም በዋናነት በፈጠራ ባለሙያዎች እና የጥበብ ሰዎች እንዲታገዝ ለማድረግ ትኩረት ማድረጋቸውንም በኢትዮጵያ የእስራኤል አማባሳደሩ ገልፀዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ቴዲ አፍሮ በ2019 በእስራኤል ሀገር የሙዚቃ ጉዞ በማድረግ የሙዚቃ ስራዎቹን አቅርቦ ነበር።