Get Mystery Box with random crypto!

የሶማሌ ክልል ካቢኔ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅር እንዲገቡ የቀረበውን ሃሳብ በሙ | Muktarovich Ousmanova

የሶማሌ ክልል ካቢኔ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅር እንዲገቡ የቀረበውን ሃሳብ በሙሉ ድምፅ ደገፈ።
********
ካቢኔው ዛሬ በደረገው ስብሰባ ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ ለማድረግ የተወሰነው ውሳኔ ዕቅድ በሙሉ ድምጽ ደግፎታል።

ካቢኔው የሶማሌ ክልሉ ልዩ ኃይል ኢትዮጵያ አስቸጋሪ ፈተና በገጠማት ጊዜ ሕይወታቸውን ሠውተዋል። በክልላቸው መንግስት የተሰጣቸው ግዳጆችን በጀግንነት በመወጣት የሃገራችንን ዳር ድንበር አስከብረዋል ያለ ሲሆን የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ለሀገራችው የሚችሉትን ሁሉ ያደረጉ፤ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጀግንነት የተወጡ፤ ለወደፊትም በተሻለና ይበልጥ ኢትዮጵያን ማገልገል በሚያስችላቸው ቦታዎች ላይ እንደ የፍላጎታቸው ተመድበው እንዲያገለግሉ የተወሰነው ውሳኔ የክልሉ መንግስት በመደገፍ አስፈላጊ የሆነውን ሙሉ ደጋፍ ይሰጣል ብሏል።

በዚህም መሰረ ካቢኔው ተከታዮቹን ውሳኔዎች አሳልፏል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አመራሮችና አባላት በውሳኔው ላይ እንዲወያዩበት ይደረጋል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች እንደ ምርጫችው ወደ መከላከያ፣ ወደ ፌደራል ፖሊስ ወይም ወደ ክልል ፖሊስ የተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮችን እንዲቀላቀሉ ይደረጋል።

ጉዳዩ የትጥቅ መፍታት ጉዳይ ሳይሆን የበለጠ ሥልጠናና ትጥቅ አግኝተው ሀገርን በተሻለ ወደ ሚያገለግሉባቸው መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያደርግ መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ ካቢኔ በዛሬው ውሎው በሰፊው ውይይት ካደረገበት በኃላ ውሳኔውን በሙሉ ድምጽ መደገፉ ተገልፆአል።

Source
Somali fast Info