Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ፊት የሚቋቋሙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፤ ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ ትምህርት ሚኒስቴር አስታ | Muktarovich Ousmanova

ወደ ፊት የሚቋቋሙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፤ ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

በፌደራል መንግስት ወደ ፊት የሚቋቋሙ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች፤ ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተናገሩ። ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት፤ ከፍለው የሚማሩ መሆን እንዳለባቸውም ሚኒስቴር ዴኤታው አስታውቀዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ይህን ያሉት፤ ስለ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን ለመደንግግ በወጣው የአዋጅ ረቂቅ ላይ በተጠራ የአስረጂ መድረክ ላይ ነው። በተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ዛሬ ሰኞ ሚያዚያ 2፤ 2015 የተደረገውን ይህን የአስረጂ መድረክ የጠራው፤ የፓርላማው የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ሳሙኤል በዚሁ መድረክ ላይ ባቀረቡት ገለጻ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ የሚሆኑበትን ሂደት አብራርተዋል። “አዋጁ ባስቀመጠው መልኩ ዩኒቨርሲቲዎች መስፈርት ሲያሟሉ፤ ደንቦቻቸው በዚህ አዋጅ መሰረት መልሶ እንዲከለስ ይደረግ እና ራስ ገዝ ሆነው መልሰው ይደራጃሉ” ብለዋል። ለፓርላማው የቀረበው የአዋጅ ረቂቅ፤ “ጠንካራ የፋይናንስ አቅም እና አካዳሚያዊ ተወዳዳሪነት” ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ከሚያበቁ መስፈርቶች መካከል እንደሚካተቱ አስፍሯል።

ይህ አዋጅ በፓርላማ ከጸደቀ በኋላ “ራስ ገዝ” የሚሆኑት፤ አሁን በትምህርት ሚኒስቴር ስር የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ አለመሆናቸውን ዶ/ር ሳሙኤል በዛሬው ማብራሪያቸው ጠቁመዋል። “መስፈርቱን አሟልተው የሚፈጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲኖሩ፣ ወደፊት አዲስም ቢሆኑ፤ እንደራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ይደራጃሉ” ሲሉ አዋጁ ወደፊት የሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎችንም የሚመለከት መሆኑን ሚኒስቴር ዴኤታው አስረድተዋል።
Ethio Insider