Get Mystery Box with random crypto!

እጅግ በጣም ልብ የሚሰብር ዜና ከሐረር!! በሐረር ከተማ ማብቂያ ያጣው የባጃጅ ላይ ዘረፋ የባለ ተ | Muktarovich Ousmanova

እጅግ በጣም ልብ የሚሰብር ዜና ከሐረር!!
በሐረር ከተማ ማብቂያ ያጣው የባጃጅ ላይ ዘረፋ የባለ ተስፋዋን ወጣት ሕይወት ቀጥፏል።

ረቡዕ መጋቢት 13/2015 አመሻሽ 1:30 አካባቢ ወጣት የኔወርቅ አበበ ከማታ የትምህርት ገበታዋ ከጓደኞቿ ጋር በመመለስ ላይ ሳለች በተለምዶ ሞቢል ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በሶስት እግር ተሽከርካሪ(ባጃጅ) የዝርፊያ ተግባር በሚፈፅሙ ሌቦች አማካኝነት የእጅ ስልኳንና ቦርሳዋን ተነጥቃ፣ ወደ አስፓልት በመገፍተሯ በተቃራኒ መንገድ በሚመጣ መኪና ይሁን በዘራፊዎቹ ባጃጅ ተሽከርካሪ ባልታወቀ ሁኔታ ክፉኛ ተገጭታ የሞት ሰለባ ሆናለች።

በአቅራቢያ ወደሚገኘው ሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል በፍጥነት ቢደረስም ከደረሰባት ጉዳት አንፃር ሕይወቷን ማትረፍ አልተቻለም።

ወጣት የኔወርቅ አበበ በ2014 ዓ.ም ከሐረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካውንቲንግና ፋይናንስ በዲፕሎማ ተመርቃ በቅርቡ በሐረር መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ትምህርቷን ለማሻሻል በዲግሪ መማር ከጀመረች 3 ቀናት ብቻ እንደተቆጠሩ በሚያሳዝን ሁኔታ ይህችን ዓለም ተሰናብታለች።

ስርዓተ ቀብሯም ዛሬ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም በትውልድ ሐገሯ ጉርሱም ከተማ ይፈፀማል።

ፈጣሪ አምላክ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ በእጅጉ መፅናናትን እንዲሰጥልን እመኛለው
#ነፍስሽ_በሠላም_ትረፍ

ሙላው ገ/ሕይወት
ሐረር/ኢትዮጵያ