Get Mystery Box with random crypto!

የጌታቸው ረዳ ፕሬዝዳንትነት መመረጥ የህወሀትን መንደር ለሁለት ከፍሎ እያናቆረ ነው። ጌች የቀድሞ | Muktarovich Ousmanova

የጌታቸው ረዳ ፕሬዝዳንትነት መመረጥ የህወሀትን መንደር ለሁለት ከፍሎ እያናቆረ ነው።
ጌች የቀድሞ የህወሃት ታጋይ አለመሆኑ እና ህወሃትን ከመምህርነት በቅርቡ 1999 አካባቢ መቀላቀሉን እያነሱ ክህደት ተፈፀመ እያሉ ነው። በአማራ አንመራም እያሉ ነው ይህ ቢድን። ጌች ራያ መሆኑ ይታወቃል። በተዘዋዋሪ ራያን መሬቱን እንጂ ሰዉን አለመፈለጋቸውን ማሳበቁን አልተረዱትም።

በሌላ በኩል የጌችን መመረጥ የደገፉ በርካቶች ናቸው። ህወሃት በስብሳለች ወጣቶችን እና ሙህራንን ጌች ያቅፋል፣ ያስጠጋል፣ የፖለቲካ አረዳዱም ከፍተኛ ነወ በማለት ለውጡን የደገፉ በርካታ ናቸው። የህወሃት ስልጣን ከአድዋ መውጣቱ ብዙዎችን አስደስቷል።

ሰለሞን ገሪማ ይህን ይፅፋል
ከዚህ በፊት ዶ/ር ደብረፅዮን በስራ ኣስፈፃሚ ተሽሞው በብዙ ተቃውሞ በማእከላይ ኮምቴ ኣይሆንም ቢባሉም "ግድ የላቹም ለኣብዪ በኣካል ሄጄ እለምነዋለሁ እቢ ካለ ሌላ ትመርጣላቹ" ማለታቸው ሁላችን የምናስታውሰው ነው።
ይህ በፌደራል መንግስት ተቀባይነት ሲያጣ በስራ ኣስፈፃሚ መሾም ቀርቶ በቀጥታ በማእከላይ ኮምቴ ትላንት የተደረገ ምርጫ
የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ለምርጫ የተወዳደሩትና ውጤታቸው እንሆ

ጌታቸው ረዳ 18
ዶ/ር ፍሰሃ ሃብተፅዮን 17
ዶ/ር ኣማንኤል ሃይለ 3
ፕሮፌሰር ህንደያ ገ/ሂወት 2
ዶ/ር ሓጎስ ጎዲፋይ 0
ረዳኢ ሓለፎም 0

ይህ ምርጫስ ተቀባይነት ያገኝ ይሆን?
ኣብረን የምናየው ይሆናል።