Get Mystery Box with random crypto!

ልፌ እፎይታ ገበያ ጀርባ : 42 የንግድ ሱቆች በእሳት ወደሙ ትናንት ምሽት 2:20 ላይ በአዲ | Muktarovich Ousmanova

ልፌ እፎይታ ገበያ ጀርባ : 42 የንግድ ሱቆች በእሳት ወደሙ

ትናንት ምሽት 2:20 ላይ በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኮልፌ እፎይታ ገበያ ጀርባ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ በተከሰተ እሳት አደጋ 42 የንግድ ሱቆች መውደማቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር 15 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት የውሀ ቦቴ ከ100 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር መሰማራታቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ የእሳት አደጋው ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር የቻሉ ሲሆን በዚህ ሂደት ግምቱ ያልታወቀ ጥሬ ገንዘብ ከአደጋው በማትረፍ ለፖሊስ ማስረከባቸውንም ነው የተናገሩት።

የንግድ ሱቆቹ በቀላሉ ሊቀጣጠሉና እሳትን ሊቋቋሙ ከማይችሉ ግብአቶች መገንባታቸውና በገበያ ማዕከሉ የሚገኙ የጋዝ ሲሊንደሮች፣ ማስቲሽና መሰል ኬሚካሎች እሳቱ በቀላሉ እንዲስፋፋ ምክንያት መሆናቸውንም አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ስፍራው የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን አለማስገባቱም ሌላኛው አስቸጋሪ ሁኔታ እንደነበርም ገልጸዋል።

በዚህ ስፍራ በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ ሲያጋጥም የነበረና በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ለአደጋ ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ የገበያ ማዕከላት አንዱ ነው።

በእሳት አደጋው ምክንያት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የሌለ ሲሆን የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው ብለዋል።FBC