Get Mystery Box with random crypto!

'አርሶ አደሩ በዚህ ልክ መሸጥ አለብህ ሊባል አይገባም!' ዶክተር ይልቃል ከፋለ የግብርናው ዘርፍ | Muktarovich Ousmanova

"አርሶ አደሩ በዚህ ልክ መሸጥ አለብህ ሊባል አይገባም!" ዶክተር ይልቃል ከፋለ

የግብርናው ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት አድርገን መሥራታችን አጠናክረን እንቀጥላለን። ምርትና ምርታማነትን መጨመር ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም። በተመረጡ ሰብሎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት ይገባል።

በአማራ ክልል በቂ ምርት አለ፤ በምርት መጠን ላይ መጨመር እንጂ መቀነስ አልታየም፡፡ ነገር ግን ገበያው አሻቅቧል። በገበያ ሕግ የማይመራ የገበያ ሥርዓት በመኖሩ የዋጋ ንረቱ ምክንያት ሁኗል።

የክልሉን የምርት ፍላጎት ማርካት አስፈላጊ ነው፤ ከዚያ ያለፈውን ለገበያ ማቅረብ ያስፈልጋል። አርሶ አደሩ በዚህ ልክ መሸጥ አለብህ ሊባል አይገባም፤ ገበያ በወሰነው መሠረት ሊሸጥ ይገባል።

ዶክተር ይልቃል ከፋለ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር