Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ዋጋ እንዳይጨመር የተጣለው ክልከላ እስከ ሰኔ ወር ተራዘመ #Ethiop | Muktarovich Ousmanova

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ዋጋ እንዳይጨመር የተጣለው ክልከላ እስከ ሰኔ ወር ተራዘመ

#Ethiopia | በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ዋጋ እንዳይጨመር የተደረገው ክልከላ እስከ ሰኔ ወር መራዘሙን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው 2ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የከተማውን ልማት ለማፋጠን የነዋሪውን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ፣ ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች ፣ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ጥያቄ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

በዚህ መሰረትም ፡-

1. የመኖሪያ ቤቶችን በመንግስትና የግል አጋርነት በ70/30 አሰራር መቶ ሺህ የሚደርሱ ቤቶችን ለመገንባት የተዘጋጀውን 35 ሄክታር መሬት ላይ ተወያይቶ ወስኗል።

2. ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች እና የስራ እድል የሚፈጥሩ የ373 ፕሮጀክቶች የመሬት ጥያቄ
እነሱም ፦

2.1 ለኢንዱስትሪ ልማት፣

2.2 ሆቴሎችና ሞሎች ፣

2.3 የሃይማኖት ተቋማት ፣

2.4 ቀደም ሲል በካቢኔ ተወስነው የመሬት ለውጥ የቀረበባቸው ቦታዎች ፣ ለተለያዩ የግንባታ ግብዓት ማስቀመጫ የሚሆኑ ጊዜያዊ መጠቀሚያ ቦታዎች ናቸው።

3. ወቅታዊ የኑሮ ውድነትና የገበያ መረጋጋት የዋጋ መናር መነሻ በማድረግ በአስቸኳይ ምርት ወደ ከተማ እንዲገባና እንዲሰራጭ ግብረ ኃይል አቋቁሟል።

4. ለተማሪዎች ምገባ የሚያቀርቡ እናቶች በአሁኑ ዋጋ ማቅረብ መቸገራቸውን መነሻ በማድረግ ለተማሪዎች ምገባ፣


5. ከወቅቱ ዋጋ መናር እና የገበያ አለመረጋጋት ጋራ ተያይዞ የነበረው የቤት ኪራይ ዋጋ አከራዮች እስከ ሰኔ እንዳይጨምሩ ተውስኗል።

የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
(ኤፍ ቢ ሲ)