Get Mystery Box with random crypto!

በቱርክ 7ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታወጀ (እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች) በቱርክ እና ሶሪያ | Muktarovich Ousmanova

በቱርክ 7ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታወጀ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁን ላይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ4,800 በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው።

የነፍስ አድን ሠራተኞችም በፍርስ ራሾች ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በቱርክ የሰባት ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጀዋል።

ፕሬዝዳንቱ የሀዘን አዋጁን ያወጁት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎችን ለማሰብ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል።