Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ ቴሌቪዥን ዜና አንባቢ ሳህለገብርኤል ይትባረክ በጠዋት የዜና ማንበብ ክፍለጊዜ ሰአቱን ጠብቆ | Muktarovich Ousmanova

የአዲስ ቴሌቪዥን ዜና አንባቢ ሳህለገብርኤል ይትባረክ በጠዋት የዜና ማንበብ ክፍለጊዜ ሰአቱን ጠብቆ ጥቁር በመልበስ ዜና ማንበብ ቢጀምርም ከስቱዲዮ አቋርጠው እንዲወጣ አድርገውታል ተብሏል:: በዚህ የዜና ሰአት ፋንታም ሌሎች ፕሮግራሞች ተለቀውበታል::

በተመሳሳይ የጣቢያው ጋዜጠኞች እና የአገልግሎት ዘርፍ ሰራተኞችም ጥቁር በመልበሳቸው ምክንያት ከግቢ እንዳይገቡ ታግደዋል::

በትናንትናው እለትም ተመሳሳይ ችግር ተፈጥሮ ሰራተኞች ተመልሰው እንደነበር በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች መዘገቡ አይዘነጋም::

ሮሐ ኒውስ