Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ላ | Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጠ!

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተከሰተው ክስተት አየተባባሰና እየተካረረ መሄዱ በእጅጉ እንዳሳሰበው ተቋሙ በመግለጫው አሳውቋል። የስድስቱ አባል የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ስለጉዳዩ በመጨነቅ አብዝተው ከመጸለይ ባለፈ ከቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ችግሩ በሰላማዊ ሁኔታ ስለሚፈታበት ሁኔታ መወያየታቸውም ተገልጿል።በተያያዘም በዚህ ሂደት ተቋሙ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

ቤተክርስቲያኒቱ ለዘመናት የኖረ ሕገ ቤተክርስቲያን፣ ቀኖና እና ሥርዓት ያላት አንጋፋ ተቋም ከመሆኗ አንጻር ያጋጠማትን ውስጣዊ ችግር በቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት ሊፈታ እንደሚችል እንጠብቃለን በማለት ገልጿል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ መሆኑን ጠቅሶ ባለ አምስት ነጥብ መግለጫም አውጥቷል።