Get Mystery Box with random crypto!

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጂማ ከተማ በፀጥታ አካላት ተወስደዋል። በነገው ዕለት አዲስ ሕንጻ ቤተ | Muktarovich Ousmanova

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጂማ ከተማ በፀጥታ አካላት ተወስደዋል።
በነገው ዕለት አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በጂማ ከተማ ለማስመረቅ የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመምሪያ ኃላፊዎች ጋራ ዛሬ ጠዋት ለመሄድ አዲስ አበባ አየር መንገድ ተገኝተው ነበር።
ከእነዚህም መካከል ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሲገኙ ሌሎች እንግዶች ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ንቡረ ዕድ ኤልያስ፣ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ፣ ሊቀ ትጉሃን እስክንድር ገ/ክርስቶስ ይገኙበታል።
አየር መንገድ ሲደርሱም የሀገረ ስብከቱ አባት ይበቃሉ በማለት ቀሲስ ታጋይ አብረው እንዲሄዱ በመፍቀድ ሌሎች አባቶችና እንግዶችን ከጉዞ መልሰዋቸዋል።
ጂማ ከተማ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ አካላት የተያዙ ሲሆን የያዟቸው አካላትም ከክልል የደረሰን አቅጣጫ ነው ማለታቸው ተሰምቷል።

ሌሎች መረጃዎች እንደደረሱን እናቀርባለን።

ከላይ ያለው ፅሁፍ

ምህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት የፌስቡክ ገፅ ያጋራው ነው