Get Mystery Box with random crypto!

ከሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የተሰጠ ወቅታዊ  መግለጫ ለሀገር ክብር እና ለወገን ደጀን ለመሆን | Muktarovich Ousmanova

ከሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የተሰጠ ወቅታዊ  መግለጫ

ለሀገር ክብር እና ለወገን ደጀን ለመሆን ውድ ህይወታችሁን መስዋእት ላደረጋችሁ  ጀግኞቻችን ነፍሳችሁን በአጸደ ገነት እንዲያውልልን እንመኛለን ።

የአማራን ህዝብ እረፍት ለመንሳት ጠላት ትላንትም ዛሬም ነገም ሳይታክት እየሰራ ነው ፤ ወደፊትም ይሰራል።

የህጻናትና የአረጋዊያን ማንገላታት  ፣ የንብረት ውድመት ፣ አረመናዊ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ግድያ መፈጸም በጥቅሉ የአማራ ህዝብ ህልውና አደጋ የሆኑ ወረራዎችን ለመከላከል ብሎም አጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት ውድ ህይወታችሁን ለተሰዋችሁ ጀግኖቻችን ነፍሳችሁን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን እና ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ደግሞ መጽናናትን ከተማ አስተዳደሩ ከልብ ይመኛል።

የከተማችንን ህልውና በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ማስቀመጥ ዛሬ ነገ የማይባልና   የሁላችንም የጋራ ትብብር ይጠይቃል ለዚህም  አንድነታችንንና ትብብራችንን በማይናወጥ አቋም ልናስቀጥል ይገባል እንላለን ።

ምንም እንኳን ጥላቶቻችን በመካከላችን አንድነትና ትብብር  እንዳይኖር በርካታ የሴራ ድግሶችን ደግሰው ለማራራቅ ሞክረዋል፤  ባይሳካላቸውም ።

ጊዜው ሁሉም በአቅሙ ያልተገደበ ድጋፋን የሚያደርግበትና ከተማውን ከመቼውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ሰላም እንድታረጋግጥ ማድረግ ጊዜ የምንሰጠው ጉዳይ አይደለም ።
በጋራ ትብብርና ወንድማማችነት በጋራ ሰርቶ ሀገርን ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የሚጥሩ ወገኖች ታላቅ ክብር አለን ፤ ዛሬም ነገም በትብብር እንሰራለን ።
ራሳችንን ከተለያዮ አሉባልታዎችና ወሬ ወለደ ወሬዎች በመጠበቅ በህልውናችን ላይ የተቃጣውን አደጋ እንቀለብሳለን ።
(ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር)