Get Mystery Box with random crypto!

'ያሳደገችኝን ቤተ ክርስቲያንን የከፈለ አባቶችንና ምእመናንን ያሳዘነ ድርጊት በመሆኑ ይቅርታ እ | Muktarovich Ousmanova

"ያሳደገችኝን ቤተ ክርስቲያንን የከፈለ አባቶችንና ምእመናንን ያሳዘነ ድርጊት በመሆኑ ይቅርታ እጠይቃለሁ "
መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ
በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የተመራው "የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት" ሕገ ቤተ ክርስቲያን የጣሰ በመሆኑ ከሕገ ወጥ ቡድኑ መውጣታቸውን መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ገለጹ።
አባ ጸጋ ዘአብ "አቡነ ኤጲፋንዮስ" በሚል በምሁር ኢየሱስ ገዳም "የበላይ ሓላፊ ጳጳስ" በሚል ተሹመው የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ምሽት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ "ያሳደገችኝን ቤተ ክርስቲያንን የከፈለ አባቶችንና ምእመናንን ያሳዘነ ድርጊት በመሆኑ የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸውን አሳውቀዋል።
ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በእንባ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን አስገብተዋል።
ምንጭ EOTV