Get Mystery Box with random crypto!

በሰቆጣ ከተማና አካባቢው ከ50 በላይ የአሸባሪው ሕወሓት ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ | Muktarovich Ousmanova

በሰቆጣ ከተማና አካባቢው ከ50 በላይ የአሸባሪው ሕወሓት ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የዋግኽምራ ብሔረሰብ ዋና አስተዳዳሪ ስቡህ ገበያው ገልጸዋል።

ሰርጎ ገቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሰቆጣ ከተማ የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ በሕዝቡና በጸጥታ ኃይሉ ስለተደረሰባቸው መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው የዋግኽምራ ሕዝብ በአሸባሪው ሕወሓት የተፈጸመበትን ወረራ ለመከላከል እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ትግልና ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።