Get Mystery Box with random crypto!

ወጉማ ተይዟልኮ! ይልቅስ ሄደህ አስከሬን ቁጠር በለው! ትናንት ብሉምበርግ የሚባል ሚዲያ ለትህነ | Muktarovich Ousmanova

ወጉማ ተይዟልኮ! ይልቅስ ሄደህ አስከሬን ቁጠር በለው!

ትናንት ብሉምበርግ የሚባል ሚዲያ ለትህነግ ተስፋ የሚሆን አንድ ዜና ሰርቶ ነበር። ኢትዮጵያ በሰላም አስከባሪነት የላከቻቸው የትግራይ ተወላጅ መኮንኖች ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም ብለው ወደ ሱዳን አቅንተው ነበር። 528 ናቸው። ሁሉም ሰሞኑን ውጊያ በተደረገበት አካባቢ ስልጠና እየሰጡ ነበር። ብሉምበርግ ታዲያ ከትህነግ በተሰጠው የውሸት መረጃ መሰረት እነዚህ መኮንኖች የሚመሩት የትህነግ ታጣቂ ሁመራን ሊይዝ እንደሆነ አድርጎ አውርቶ ነበር። ውሸት ቁርሳቸው፣ ምሳቸው፣ ራታቸውም ነው።

እውነታው ሌላ ሆነ። ጥምር ጦሩ ገና በመጀመርያው ቀን የት ልግባ አስባላቸው። በሁለት ቀን ሁሉም ምሽግ ተሰባብሮ የተረፉት ወደ ሱዳን እግሬ አውጭኝ ሲሉ አብዛኛውን ጥይትና ቀሪውን የተከዜ ውሃ በላው።

ተበታትኖ የሚገኘውን የትህነግ ኃይል ጥምር ጦሩ የማፅዳት ስራ እየሰራ ይገኛል። እንደምንም ወደ ሱዳን የተሻገረው የትህነግ ታጣቂ አሻባ የተባለ ቦታ ላይ የሱዳን ወታደሮች መሳሪያህን አራግፍ እያለው ነው። ሱደን የከረመው የትህነግ ኃይል ሲፎክር ስለከረመ አሁን እግሬ አውጭኝ ሲል ሱዳኖቹ እንዴት ይታዘቡታል?

ከሱዳን አቅጣጫ የመጣው የትህነግ ኃይል ሁመራን እይዛለሁ ብሎ አስወርቶ በጥምር ጦሩ አሳሩን ሲበላ ከፍተኛ አዛዦቹን ጭምር አጥቷል። በዚህ ውጊያ ኮ/ል መኮነን ኃይሉ የተባለ የትህነግ ክ/ጦር አዛዥን ጨምሮ በሺህ የሚቆጥር ሬሳውን ጭኖ ለመሸሽ ሞክሯል። በርካታ ታጣቂ ሲሮጥ ተከዜ ሲወስደው፣ በውጊያ የሞቱበትን ግን በጀልባ እየጫነ ወደ ሱዳን ለመሻገር ጥሯል። ነፍስ ያለውን ወንዝ ላይ ጨምሮ ሙት ተሸክሞ ይሄዳል። ትህነግ በብሉምበርግ ያሰራው ደግሞ በጀግኖቻችን መስዋዕነት ህልም ሆኖ ቀርቷል። ወግ ብቻ!

https://t.me/GetachewShiferaw