Get Mystery Box with random crypto!

የጦርነት ሎጅክ…. የመጀመሪያዉ የዓለም ጦርነት በአዉሮፓ ጦርነቶችን ሁሉ ለማስቆም የተደረገ ጦርነ | Muktarovich Ousmanova

የጦርነት ሎጅክ….

የመጀመሪያዉ የዓለም ጦርነት በአዉሮፓ ጦርነቶችን ሁሉ ለማስቆም የተደረገ ጦርነት ነበር ይባላል። ግን የብዙ ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት ቀጥፎ፣ ዓለምን ለሌሎች በርካታ ጦርነቶች ዳርጎ አለፈ። በዓለም ላይ በፍፁም በጦርነት ጥሩ ነገር ተገኝቶ አያዉቅም። ነገር ግን አንዱ ጠብ-መንጃ ስያነሳ ሌላኛዉ ዝም ብሎ ማየት አይቻልም። ጠበብ-መንጃ ያነሳዉ ጠብ-መንጃዉን እንድያስቀምጥ ጠብ-መንጃ የተነሳበት ጠብ-መንጃ ማንሳት የግድ ይሆናል። በዓለም ላይ ከጦርነት የከፋ ነገር ብኖር ጦርነትን አለመመከት ብቻ ይሆናል። ብቸኛ የጦርነት ጄስትፍከሽን ይሄ ብቻ ይሆናል።
(ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ)