Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያን የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት የሚያደርገው ፖሊሲ በስራ ላይ እንዲ | Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያን የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት የሚያደርገው ፖሊሲ በስራ ላይ እንዲውል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ። ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 28፤ 2014 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ነው።

የመንግስት ፖሊሲው ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነው በአራት ምክንያቶች እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ፖሊሲው ስራ ላይ እንዲውል ካስፈለገበት ምክንያቶች አንዱ የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪነት፣ ወጤታማነትና ቀልጣፋነት በመጨመር፤ በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር እና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንዲሳለጥ ለማድረግ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

አዲሱ ፖሊሲ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር “ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር” ያስችላል ተብሎ ታምኖበታል። ፖሊሲው ከዚህ በተጨማሪ “የስራ እድል ፈጠራ እንዲጎለብት” እንዲሁም “ኢኮኖሚያዊ ውጤታማነትን እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ” የሚያስችል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ ጠቁሟል። የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ “የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ” የሚያግዝ መሆኑንም የጽህፈት ቤቱ መግለጫ አክሏል።

ጠ/ አብይ አህመድ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ባንክ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ስለማድረግ ተናግረው ነበር፣ ባለፈው የካቲት 15፤ 2014 በፓርላማ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፤ የውጭ ሀገር ባንኮችን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት “የፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት” እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠ/ሩ ማብራሪያቸው “ተጨማሪ ሀብት፣ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ስላለብን [የውጭ] ባንኮች እናመጣለን። የሀገር ውስጥ ባንኮች ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል” ሲሉ አሳስበው ነበር። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)