Get Mystery Box with random crypto!

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ “በሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ ላይ ለመወያየት” ለሶስተኛ ጊዜ ወደ | Muktarovich Ousmanova

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ “በሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ ላይ ለመወያየት” ለሶስተኛ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው

ከአንድ ወር በፊት አዲስ አበባ የነበሩት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር፤ “በሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ ላይ ለመወያየት” በድጋሚ ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው። አምባሳደር ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙት፤ ሁሉም ወገኖች ውጊያ አቁመው የሰላም ንግግር እንዲያደርጉ የሚያሳስብ መልዕክት ይዘው እንደሆነ የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ካሪን ጄን ፒየር ትላንት አርብ ምሽት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

ካሪን ጄን ፒየር በዚሁ መግለጫቸው “የፕሬዝዳንት ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ማይክ ሐመር በሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ ላይ ለመነጋገር ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ” ብለዋል። የአሁኑ የአምባሳደር ሐመር ጉዞ በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ዳግም ውጊያ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ ነው።

የዋይት ሐውሷ ቃል አቀባይ በትላንቱ ጋዜጣዊ መግለጫቸው፤ አምባሳደር ማይክ ሐመርም ሆነ አሜሪካ ህወሓት ከትግራይ ክልል ውጪ እያደረገ የሚገኘውን ማጥቃትም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽመውን የአየር ጥቃት እንደሚያወግዙ ገልጸዋል። ቃል አቃባይዋ “ኤርትራ ወደ ግጭቱ ተመልሳ መግባቷን” በተመሳሳይ መልኩ ኮንነዋል።

* * ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/7987/