Muktarovich Ousmanova

የቴሌግራም ቻናል አርማ muktarovichousmanova — Muktarovich Ousmanova
ርዕሶች ከሰርጥ:
Wazemaalert
Ebc
Pmoethiopia
Westandwithendf
Londonmarathon
Berlinmarathon
Inbox
Fastmereja
Ethiopia
Southafrica
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @muktarovichousmanova
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 74.31K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia forever

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-07 21:53:33
በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ አካላት ፊት አውራሪነት በግፍ በዱላ ተቀጥቅጦ በሐዋሳ ሕክምና ሲደረግለት የነበረው ወንድም አያሌው ተረፈ በሰማዕትነት አረፈ !

እስከ አሁን 37 ኦርቶዶክሳውያን በሻሸመኔ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ሲሆን በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ 2 ሆስፒታሎች ቁጥራቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ኦርቶዶክሳውያን በጽኑ ሕሙማን ክፍል እንደሚገኙ ተ.ሚ.ማ ያገኘው መረጃ ያመላክታል !
10.2K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 21:44:33
ጥዑመ ልሳን ቀሲስ ሐረገወይን የሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ በኦሮምያ ፖሊስ ድብደባ ተፈፅሞባቸው በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ አርፈዋል።
ምንጭ ዘሀበሻ
11.2K viewsedited  18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 13:32:07
#Inbox ሰላም መረጃ ዛሬ ማለዳ በኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ክልል ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ፋብሪካ ውስጥ ጥቁር ለብሳችሁ ስራ አትሰሩም ተብለን የክልሉ ተወላጅ የሆኑና የመሥሪያ ቤቱ ሰራተኞች ልዩ ሀይል ጠርተውብን ዛሬ ታስረናል። በትላንትናው እለትም ጥቁር ለብሰው ተገኝተው የነበሩትም ታስረዋል እኛን በፓትሮል ከምንሰራበት መስሪያ ቤት ግቢ በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ታፍነን ወደ ጣቢያ ተወስደን ቃላችንን ከተቀበሉ በዋላ የተወሰንነው በማስጠንቀቂያ ለቀውን የተቀሩት እዛው ታስረዋል። የነሱንም ውጤት እየጠበቅን ነው።

መረጃ ቲቪ
20.0K views10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 12:38:29
ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ ለማምለጥ የሞከረው ግለሰብ ጅብ ገጥሞት ባሰማው የድረሱልኝ ጥሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ ዐ1 ልዩ ቦታው ፖራዳይዝ ሆቴል ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ ጫካ በመግባት ለማምለጥ የሞከረው ግለሰብ ጅብ ገጥሞት ባሰማው ጩኸት በቁጥጥር ስር መዋሉን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ግለሰቡ ከጅማ ዞን ሊሙ ሰቃ ወረዳ የአቃቢ ህግ ባለሙያ መሆኑንና ቴዲ ድሪባ እንደሚባል የመምሪያው የኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ዮሀንስ በየነ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቡ የ4ኛ አመት የዩንቨርሲቲ ተማሪ የሆነችውን ፍቅረኛውን ለመጠየቅ ወደ ደብረማርቆስ መምጣቱ ተነግሯል።በሰዓቱ ተጎጂ የሆነችው ግለሰብ ከዚህ በኋላ አንድ ላይ መቀጠል እንደማይችሉ ስትነግረው በጩቤ ወግቶ በጫካ አድርጎ ሲያመልጥ ከምሽቱ 5:00 አካባቢ ጅብ አግኝቶት አላሳልፈው ሲል ባሰማው የድረሱልኝ ጩኸት የመንቆረር ኮንስትራክሽን ጥበቃዎች ደርሰው ለፖሊስ በሰጡት መረጃ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ግለሰቧ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ህክምና እየተደረገላት መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ዮሀንስ በየነ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

Via: ዳጉ ጆርናል
20.0K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 12:18:12
በቱርክ 7ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታወጀ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁን ላይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ4,800 በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው።

የነፍስ አድን ሠራተኞችም በፍርስ ራሾች ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በቱርክ የሰባት ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጀዋል።

ፕሬዝዳንቱ የሀዘን አዋጁን ያወጁት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎችን ለማሰብ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል።
19.1K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 08:51:13
የአዲስ ቴሌቪዥን ዜና አንባቢ ሳህለገብርኤል ይትባረክ በጠዋት የዜና ማንበብ ክፍለጊዜ ሰአቱን ጠብቆ ጥቁር በመልበስ ዜና ማንበብ ቢጀምርም ከስቱዲዮ አቋርጠው እንዲወጣ አድርገውታል ተብሏል:: በዚህ የዜና ሰአት ፋንታም ሌሎች ፕሮግራሞች ተለቀውበታል::

በተመሳሳይ የጣቢያው ጋዜጠኞች እና የአገልግሎት ዘርፍ ሰራተኞችም ጥቁር በመልበሳቸው ምክንያት ከግቢ እንዳይገቡ ታግደዋል::

በትናንትናው እለትም ተመሳሳይ ችግር ተፈጥሮ ሰራተኞች ተመልሰው እንደነበር በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች መዘገቡ አይዘነጋም::

ሮሐ ኒውስ
22.8K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 21:38:35
ገነቴዋ...

<<ቤተክርስትያን በአሏህ የተመሰለች ናት፤ አሏህ አንድ ነው፣ አሏህ አይከፈልም ኦርቶዶክስ ኃይማኖትም ጥንትም አንድ ናት ዛሬም አንድ ናት አትከፈልም!

ከጥንት ጀምሮ በታሪክ የምንሰማው እኛም በእድሜያችን የተመለከትነው ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሰላማዊ እንግዶችን በክብር ስትቀበል፣ ከሌላው ኃይማኖት ጋር ተከባብራ አብራ ስትኖር፣ ህመም ወረርሽኝ ሲመጣ፣ በሃገር ላይ ጦርነትና ሃዘን ሲመጣ ዱኣ አድርጋ ስትታደግ፣ አንድ ሆና ሃገርን አንድ ስታደርግ ነው።

የቤተክርስትያኗ አባቶችም አንድም ቀን እንኳን ሊለያዩ ቀርቶ አንድ አካል አንድ አምሳል ሆነው አባት ልጁን ልጅም አባቱን አክብረው ከመኖር ያለፈ በመሃላቸው ልዩነት ተፈጥሮባቸው አይተን አናውቅም። ዛሬ ልጆች ከአባቶቻቸው ለመለየት የሚያበቃ ምን ተገኘና ነው አባቶቻቸውን አስቀይመው አሳዝነውና አስለቅሰው ለመለየት የፈለጉት?

አባቱን የናቀ ሁሉ አላህን የናቀ ነው፣ አባቱን ያከበረ ሁሉ አላህን ያከበረ ነው። አባቶችን ንቆ እነርሱ ያቆሟትን ጥንታዊና አንድ የነበረችዋን የኦርቶዶክስን ሃይማኖት በመክፈል ከአባቶች መለዬት ማለት ከአላህ መለዬት ማለት ነው።

ኧረ ተው! ይሄኮ አላህን ለማስቆጣት መቻኮል ነው! እኔ እስከገባኝ ድረስ ቤተክርስትያን በአሏህ የተመሰለች ናት፣ አሏህ አንድ ነው፣ አሏህ አይከፈልም፣ አሏህ አንድ ሁኑ ተደጋገፉ በአንድነት ድመቁ ይላል። ኦርቶዶክስ ኃይማኖትም ጥንትም አንድ ናት ፤ ዛሬም አንድ ናት አትከፈልም።>>

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስ
23.6K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 15:02:10
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጠ!

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተከሰተው ክስተት አየተባባሰና እየተካረረ መሄዱ በእጅጉ እንዳሳሰበው ተቋሙ በመግለጫው አሳውቋል። የስድስቱ አባል የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ስለጉዳዩ በመጨነቅ አብዝተው ከመጸለይ ባለፈ ከቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ችግሩ በሰላማዊ ሁኔታ ስለሚፈታበት ሁኔታ መወያየታቸውም ተገልጿል።በተያያዘም በዚህ ሂደት ተቋሙ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

ቤተክርስቲያኒቱ ለዘመናት የኖረ ሕገ ቤተክርስቲያን፣ ቀኖና እና ሥርዓት ያላት አንጋፋ ተቋም ከመሆኗ አንጻር ያጋጠማትን ውስጣዊ ችግር በቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት ሊፈታ እንደሚችል እንጠብቃለን በማለት ገልጿል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ መሆኑን ጠቅሶ ባለ አምስት ነጥብ መግለጫም አውጥቷል።
12.3K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 12:27:12
" ... የቤተክርስቲያንን ቀኖናና ዶግማ መሰረት ያደረገ እና ሲኖዶሳዊ እውቅና ያለው ነው " - የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ አትሌት ደራርቱ ቱሉ መፈንቅለ ሲኖዶስ የፈጸሙና ከቤተክርስቲያን ተወግዘው የተለዩ ወገኖች ጥፋታቸውን አምነውና ተጸጽተው እንዲመለሱ ለማድረግ የሽምግልና ጥረት እያደረገች ትገኛለች ስትል አሳወቀች።

አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፤ የምታደርገው ጥረት የቤተክርስቲያንን ቀኖናና ዶግማ መሰረት ያደረገና ሲኖዶሳዊ እውቅና ያለው መሆኑን  ቤተክርስቲያኗ ገልፃለች።
16.4K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 18:48:01
.                           ውብ ነገን

                            ዛሬ ይግዙ
                           ነገ ይክፈሉ!!!


እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በ15% ቅድመ ክፍያ የራስዎ ያድርጉ ።

15% ቅድመ ክፍያ በመክፈል ቀሪውን ክፍያ በሶስት አመት ከወለድ ነፃ አልያም ደሞ ከ 5 እስከ 30 ዓመት በጣም በዝቅተኛ የወለድ መጠን ዘና ብለው ይክፈሉ

እስከ 30% የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተን እርሶን እየጠበቅን ነው

ለበለጠ መረጃ
ኢንጅነር ናሆም
0911085103
22.0K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ