Get Mystery Box with random crypto!

እዉነት እኔ የራሴን ቢዝነስ ሰርቼ ሃብታም መሆን እችላለሁ? ብዙ ሰዎች አሁን ካላቸዉ ኑሮ የተሻለ | 🇲 🇪ድያ Success



እዉነት እኔ የራሴን ቢዝነስ ሰርቼ ሃብታም መሆን እችላለሁ?

ብዙ ሰዎች አሁን ካላቸዉ ኑሮ የተሻለ ህይወት ለመኖር ይመኛሉ፡፡ ምኞት ብቻዉን ግን በቂ አይደለም፡፡ ብዙዉን ጊዜ ምኞት በስራና በጠንካራ ዲሲፕሊን ካልታገዘ የሚያልሙትን ህይወት ማግኘት ከህልምነት አያልፍም፡፡

በምኞት ብቻ የሚዋልሉ አቋራጭ ፍለጋ ላይ ያተኩራሉ፡ ሎተሪ መቁረጥ፣ ሃብታም ባል ወይንም ሚስት ፍለጋ መባዘን፣ ስራ ላይ በሚከሰት አደጋ ጠቀም ያለ ካሳ ለማግኘት ማለም፣ ዉርስ መጠበቅ፣ ሙስና፣ ወዘተ፡፡ ምንም እንኳን ከላይ የተጠቀሱት እና ሌሎች አቋራጮች አልፎ አልፎ ቢሳኩም አብዛኛዉን ጊዜ ግን መና ሆነዉ ሲቀሩ ይታያል፡፡

ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ደግሞ በተቃራኒዉ ገና በጠዋቱ እጅ ሰጥተዉ ያለ ህልም ወይንም ራእይ እድሜያቸዉን ይገፋሉ፡፡

በህሊናቸዉ ነገሮች ከባድ እንደሆኑ እና የተሳካ ህይወት የነርሱ ሊሆን እንደማይችል ራሳቸዉን አሳምነዉ ተቀምጠዋል፡፡ እኔማ ተምሬ ዲግሪ አልይዝም፣ የራሴን ቤት ሰርቼ ከኪራይ ልወጣ የማይታሰብ ነዉ፣ክብደትማ በፍፁም መቀነስ አልችልም፣ ወዘተ እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦች ብዙዎችን ሳይሞክሩ እጅ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል፡፡

በጣም በርካታ ሰዎች እድሜያቸዉን ሙሉ ለዚህ ወይንም ለዚያ ድርጅት ሲሰሩ አሳልፈዉ የጡረታ ጊዜ ሲቃረብ እንዴት እሆን ፡ ይሆን የሚለዉ ስጋት መምጣት ይጀምራል፡፡ እድሜ እየገፋ ሲሄድ አቅም ስለሚቀንስ ተሯሩጦ መስራት አማራጭ አይሆንም፡፡ ለጤና የሚደረገዉ ወጪም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የጡረታዉ ገቢም የሚያወላዳ አይደለም (በተለይም የዋጋ ግሽበት በቀጣይነት ሊኖር ስለሚችል) ፡፡

በደህና ጊዜ ልጆቹን ለቁምነገር ያበቃ የልጆቹን እጅ ማየት ሊኖርበት ነዉ፡፡ አሊያም ልጆቹን ያሳደገበትን ቤት ሸጦ ትንሽ ቤት ሰርቶ ወይ ገዝቶ ቀሪዉን እየበላ ኑሮዉን ይገፋል፡፡

ታዲያ ስኬትን እንዴት ማግኘት ይቻላል?

#ወደሃብት_ጉዞ 

ቢዝነስ ለነጋዴ ልጅ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች የንግድ ስራ በቤተሰብ የሚወረስ ብሎም ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ የተተወ ይመስላቸዋል፡፡ በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ቤተሰብ ዉስጥ መኖር ስለንግድ የተሻለ እዉቀት እንዲኖር ሊረዳ ቢችልም ሌላ ሰዉ ሊማረዉ አይችልም ማለት ግን አይደለም፡፡

ተነሳሽነቱ እና ቁርጠኝነቱ ካለ በየትኛዉም መስክ የሚፈለገዉን እዉቀት ማዳበር ይቻላል፡፡ መማር መመረቅ መቀጠር ከሚለዉ የተለመደ ወይንም ካደግንበት አስተሳሰብ ወጥተን ስራ ፈጠራን፣ የራስ ቢዝነስን ማደራጀት መሞከር ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ ኑሯችን ወይ ከእጅ ወደአፍ ነዉ አሊያም ሰዉ የቆረጠልንን ደሞዝ እየጠበቅን የሌሎችን ስኬት ማፋጠን ብቻ ይሆናል የኛ ሚና እና መዳረሻ፡፡

መቼም ሁሉም ሰዉ የራሱን ቢዝነስ የሚሰራ ሆኖ የሚቀጠር ሰዉ አይኖርም ወይንም አይኑር ማለት አይደለም፡፡ ህይወቱን መቀየር እና ሃብታም መሆን የሚፈልግ ሰዉ ግን ጠዋት ገብቶ እስከ አስራ አንደ ሰአት ሰርቶ በወሩ መጨረሻ ሰላሳ ቀን ሰርቶ አንድ ቀን የሚከፈለውን ወይም የሚሰጠዉን ደሞዝ ከመጠበቅ ወጥቶ የራሱ ጌታ ወደሚሆንበት አስተሳሰብ እና ተግባር መሸጋገር ይኖርበታል፡፡ ይህን ማድረግ ቀላል አይደለም ግን ከልብ ካለቀሱ እንደሚባለዉ ነዉ ነገሩ…. ቤተሰቦች!

ብዙዎች ስለኑሯቸዉና ህይዎታቸዉ ያማርራሉ ግን ደግሞ የለመዱትን ቢሮ ገብቶ መዉጣት አኗኗር ለመቀየር ቁርጠኝነት ይጎድላቸዋል፡፡ ስለሆነም ደስተኛም ባይሆኑ አዲስ ነገርን ፍራቻ ባሉበት መቆየትን ይመርጣሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜ ወሬያቸዉ ኑሮ ተወደደ፣ ኪራይ ጨመረ… ድሮ ጊዜዉ ጥሩ ነበር ወዘተ የሚሉ አይነት ባህሪያትን እነርሱ ላይ ማየት የተለመደ ነው፡፡

በተቃራኒዉ ለለዉጥ ቀበቷቸዉን ያጠበቁት ደግሞ ምን እናድርግ፣ ምን ብንሰራ ያዋጣል፣ እያሉ መረጃ መለዋወጥ እቅድ ማዉጣት ይሆናል፡፡

ችግርን ደጋግመዉ ቢያወሩት ጊዜን ለማቃጠል ካልሆነ በራሱ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ባሉበት መርገጥ ነዉ መጨረሻዉ፡፡ ራስን በመቀየር ሁሌ ደሞዝ ጭማሪና እድገት ከመጠበቅ አዙሪት ወጥቶ የሚፈልጉትን ህይወት መምራት ይቻላል፡፡ ይህን በማድረግ (የገንዘብ ነፃነትን በማግኘት) ሌሎች እድሜያቸዉን ሙሉ ደሞዝን ስለማብቃቃት ሲያወሩ ስለሌላ አላማ እና ግብ ወይንም የሚወዱት ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ ይቻላል፡፡

ብዙዎች አዳዲስ ሀሳብ የሚይዙበት ፣ ራሳቸውን እንዲመረምሩና እንዲጠይቁ እናግዛቸው ዘንድ #ሼር ይደረግ።

ደስ ብሎኛል ስላነበባችሁት .... ውብ አሁን ተመኘሁ !

አዘጋጅ : ዚ ( ጤናማ ቃላት)

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ