Get Mystery Box with random crypto!

#ፍርሀት ብዙ ሰዎች ሕይወትን የሚኖሩት ልክ ለዝግጅት እንደሚደረግ ልምምድ ነው። ህይወት ልምምድ | 🇲 🇪ድያ Success



#ፍርሀት

ብዙ ሰዎች ሕይወትን የሚኖሩት ልክ ለዝግጅት እንደሚደረግ ልምምድ ነው። ህይወት ልምምድ ሳትሆን የዋንጫ ጨዋታ ናት፡፡ ማንም ሰው ነገ በሕይወት ለመኖሩ ማረጋገጫ የለውም። ያለን ጊዜ አሁን ብቻ ነው። ልንቆጣጠረው የምንችለውም አሁናችንን ብቻ ነው። የአሁኑ ቅፅበት ላይ ትኩረት ስናደርግ ፍርሀትን ከአዕምሯችን እናስወጣዋለን።

ፍርሀት ማለት ምናልባት ወደፊት ሊፈጠር ስለሚችል ነገር መስጋት ነው። በቂ ገንዘብ ላይኖረን ይችላል፤ ልጆቻችን የሆነ ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤ እያረጀን ነው፤ ልንሞት እንችላለን . . . የመሳሰሉት።

ፍርሀትን ለመፋለም ምርጡ መንገድ ትኩረታችንን አሁን ላይ ማድረግ ነው።

በተሻለ መንገድ ልገልፀው የምችል አይመስለኝም ማርክ ትዌይን “በሕይወቴ ስለ ብዙ ነገሮች ተጨንቄ አውቃለው። ግን የተወሰኑት ብቻ ናቸው የእውነት የተከሰቱት።” ብሏል።

ቀላሉን ነገር አታካብድ ፤
ዶ/ር ሪቻርድ

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ