Get Mystery Box with random crypto!

ለጊዜው ጅል መምሰል ወይም ለዘላለሙ ጅል መሆን? የሚጠይቅ ለደቂቃ ጅል ይሆናል የማይጠይቅ ግን | 🇲 🇪ድያ Success

ለጊዜው ጅል መምሰል ወይም ለዘላለሙ ጅል መሆን?

የሚጠይቅ ለደቂቃ ጅል ይሆናል የማይጠይቅ ግን ለዘለአለሙ ጅል እንደሆነ ይቀራል ይባላል።

እንደ ህዝብ ጅል ሆነን የቀረነው ስለማንጠይቅ ነው። የተነገረንን እንደ ፈጣሪ ቃል ሳናገናዝብ ስለምንቀበል፣ የሚወረወርልንን እንደወረደ ስለምንቀልብ፣ ያጎረሱንን ሳናላምጥ ስለምንውጥ፣ ያጠጡንን ሳናጣጥም ስለምንጋት ነው።

ብንጠይቅ ለቅፅበት ጅል እንመስላለን። አላዋቂዎችም ለግዜው ሊዘባበቱብን ይችላሉ። ሳንጠይቅ ከቀረን ግን ለዘለአለሙ ጅል ሆነን እንቀራለን። ምርጫው ሁለት ነው። ምርጫው ቀላል ነው። ለግዜው ጅል መምሰል ወይም ለዘለአለሙ ጅል መሆን!

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ