Get Mystery Box with random crypto!

አንድ . . . በ . . . አንድ ማንኛውንም ተግባር በተዋጣለት ሁኔታ ለመፈጸም ብቃቱ ኖሯችሁ | 🇲 🇪ድያ Success



አንድ . . . በ . . . አንድ

ማንኛውንም ተግባር በተዋጣለት ሁኔታ ለመፈጸም ብቃቱ ኖሯችሁ ሳለ እንዳይሳካ ከሚያደርጉ እንቅፋቶች አንዱ ሁሉን ነገር በአንድ ላይ የማሰብ ዝንባሌ ነው፡፡ አንድን ተግባር የማጠናቀቅ ሂደት ሶስት ነገሮችን ይነካል፡፡ መጀመር፣ መቀጠልና መጨረስ፡፡ ምንም ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ስለእነዚህ ሶስት ሂደቶች በሚገባ ካሰባችሁ በኋላ እያንዳንዳቸውን ሂደቶች ሳትደራርቡ መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው፡፡

ማለትም ለምሳሌ፣ በመጀመር ሂደት ጊዜ ስለመቀጠልና ስለመጨረስ መጨነቅ ትኩረታችሁን ከጅማሬው ላይ እንድታነሱ ወይም የመቀጠሉንና የመጨረሱን ጉዳይ ፈርታችሁ እንድትመለሱ ያደርግላቹኃል፡፡ አንዴ ከጀመራችሁ በኋላ ደግሞ መለስ ብላችሁ፣ “ምነው ባልጀመርኩት!” ወይም ደግሞ ወደፊት አይታችሁ “እንዴት ይሆን የምጨርሰው!” በማለት ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን ካባከናችሁ ወደፊት መቀጠላችሁ አጠራራሪ ነው፡፡

የመጀመር ሂደት

ማንኛውም ነገር እንዲቀጥልና እንደፈጸም በቅድሚያ ሊጀመር ይገባዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሁሉን ነገር በአእምሯቸው በማውጣትና በማውረድ ሲያስቡት ይከርማሉ እንጂ አንድም ነገር አይጀምሩም፡፡ የተግባር ሰው አለመሆን፣ ስለነገሩ ቀጣይነት መጨነቅና ምናልባት ካልጨረስኩት አፍራለሁ የሚል ፍርሃት ሊጠቀሱ የሚገባቸው እንቅፋቶች ናቸው፡፡

የመቀጠል ሂደት

ማንኛውንም ነገር አንዴ አምናችሁበት ከጀመራችሁ በኋላ በሙሉ ኃይላችሁ ወደፊት የመቀጠልን ነገር በቁርጠኝነት መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደጠቀስነው “ምነው ባልጀመርኩና እንዴት ይሆን የምጨርሰው” የሚሉ ሃሳቦች ለቀጣይነት አስጊ የሆኑ እንቅፋቶች ናቸው፡፡

የመጨረስ ሂደት

አንድን ነገር በምንም መልኩ ጀመራችሁት፣ በምንም መልኩ ቀጠላችሁት ዋናው ቁም ነገር የመጠናቀቁ ጉዳይ እንደሆነ አትዘንጉ፡፡ የመጀመርን አስፈላጊ ደረጃ አልፋችሁና የመቀጠልን ፈታኝ ወቅት ተሻግራችሁ ወደመጨረሻው ስትደርሱ ጉልበታችሁ ይፈተናል፣ እልህ ያስጨርሳቹሃል፣ እረፍት ያምራቹሃል . . .፡፡ አለመጨረስ ግን ክስረታችሁን ዘርፈ-ብዙ ያደርገዋል፡፡

አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ስለሶስቱም ደረጃዎች በሚገባ ማሰብና ማቀድ ተገቢ ነው፡፡ ሆኖም፣ አንዴ ከተራመዳችሁ በኋላ በመጀመሪያ ስለመጀመር ብቻ አስቡ፣ ከዚያም ስለመቀጠል ብቻ አስቡ፣ ከዚያም ስለመጨረሳችሁ ብቻ አስቡ፡፡

የጀመራችሁትን ስራ እየጨረሳችሁ የምትሄዱ ሰው እስክትሆኑ ድረስ በእርግጥም “ሰው” እንዳልሆናችሁ አትዘንጉ !



ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ