Get Mystery Box with random crypto!

ሴትየዋ ችግሯን ልታማክር ወደ ዶክተር ሄደች። 'ዶክተር እባክህ አንድ ችግር ገጥሞኛል።' 'ምን | 🇲 🇪ድያ Success



ሴትየዋ ችግሯን ልታማክር ወደ ዶክተር ሄደች።

"ዶክተር እባክህ አንድ ችግር ገጥሞኛል።"

"ምን ገጠመሽ?"

".…ከወለድኩ ገና አንድ አመት አልሞላኝም። ሆኖም ሌላ ልጅ አርግዣለሁ። እኔ ደግሞ ተጨማሪ ልጅ በዚህ ወቅት እንዲኖረኝ አልፈልግም።"

"እና ምን ልርዳሽ?""

"ሆዴ ውስጥ ያለውን ልጅ ማስወረድ እፈልጋለሁ!"

ዶክተሩ ትንሽ አሰብ አደረገና “ለምን ከዚህ የተሻለ ሀሳብ አላቀርብልሽም?” ሲል ጠየቃት።

“ምን አይነት ሀሳብ?”

“አየሽ ይሄን ልጅ ከሆድሽ ለማስወረድ ብዙ ችግር ውስጥ ትገቢያለሽ ፤ ደም ይፈስሻል ፣ በቀጣይ ላትወልጂ የምትችይበት አጋጣሚም ሊፈጠር ይችላል ፣ ልትሞቺ ወይም ህይወትሽን ልታጪ ትችያለሽ ። ስለዚህ ይሄን ሁሉ ችግር ከምታስተናግጂ ለምን በእጅሽ ያቀፍሽውን ልጅ አንገድለውም?” አላት ።

ሴትየው ከልቧ አደነገጠች። ዶክተሩ ንግግግሩን ቀጠለ።

“አዎ! ለእናት እንደሆነ ሁሉም ልጅ እኩል ነው። ስለዚህ አንዱ መሞት ካለበት ሆድሽ ውስጥ ያለው ከሚሞት ይሄኛው የተወለደው ቢሞት ምንም ችግር ሳይገጥምሽ ሀሳብሽን ታሳኪያለሽ…” እያለ ምክረ ሀሳቡን መተንተን ጀመረ።

ሴትየዋ ግን በጆሮዋ የሚንቆረቆረው የዶክተሩ ሀሳብ ሳይሆን የአምላክ ማሳሰቢያ መሆኑን እያሰበች ለማስወርድ የዘረጋቻቸውን ሁለት እግሮቿን ሰብስባ ብድግ ብላ ክፍሉን ለቃ መውጣት ጀመረች።..…ልጆቿን አንዱን በክንዷ ሌላውን በሆዷ እንዳቀፈች ወደ ቤቷ ተመለሰች።

አዎ! የተወለደም በሆድ ውስጥ ያለም ቢሆን ለእናት ልጆቿ ሁሉ እኩል ናቸው!!!

አዎ! የተሰጠንን ብናውቅ ፣ የተቀመጠልንን ብናገናዝብ ብዙ ጥፋት ውስጥ ባልገባን !


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ