Get Mystery Box with random crypto!

ከጓደኞቼ ጋር አዲስ አመትን ካዝሚር ዛፍ ስር ተሰባስበን እያከበርን ነበር፡፡ ፡ ከትንሽ ቆይታ በኋ | 🇲 🇪ድያ Success



ከጓደኞቼ ጋር አዲስ አመትን ካዝሚር ዛፍ ስር ተሰባስበን እያከበርን ነበር፡፡

ከትንሽ ቆይታ በኋላ የበሰለ ፍሬ እጄ ውስጥ ወደቀ፡፡ ስቀምሰው እጅግ ጣፋጭ ሆኖ አገኘሁት በኋላ እንጨት አምጡ ብዬ ፍሬውን ዳግም አርግፌ መብላት ስጀምር መረረኝ፡፡

እንዴት ነው ነገሩ ?! እጄ ላይ የወደቀው ፍሬ ጣፋጭ ነበር ፡ አሁን ያራገፍኩት ግን መረረኝ ስል፤ ከጓደኞቼ መካከል አንዱ እንዲህ አለኝ

"የመጀመሪያው በጊዜው ስለወደቀ ጣፈጠህ ሁለተኛውን ያለጊዜው ስላራገፍከው መረረህ" አለኝ፡፡

ተመልከቱ ፈጣሪ የሚጠቅመንን ነገር በጊዜ እጃችን ውስጥ ይጥለዋል፡፡ እኛ ግን በግድ ይሁን ብለን በምናስቸግረው ጊዜ ጣፋጭ ያልሆነ ፍሬ እጃችን ውስጥ ይቀራል፡፡

የትዕግስት ተራራ ላይ ሆነን አምላካችንን
እንጠብቀው፡፡ ልመናችንን በራሱ ጊዜ ይፈጽመው ዘንድ እድል እንስጠው፡፡
የእርሱ ከሆነ ጣፋጭ ነውና።

ትዕግስት ሀያል ናት።

ጥረታችሁን ቀጥሉ ... የበሰለ ፍሬ ምንበላበት ጊዜ እየቀረበ ነው ወዳጆቼ


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ