🇲 🇪ድያ Success

የቴሌግራም ቻናል አርማ mediasuccess — 🇲 🇪ድያ Success
ርዕሶች ከሰርጥ:
Share
Digital
Inspire
የቴሌግራም ቻናል አርማ mediasuccess — 🇲 🇪ድያ Success
ርዕሶች ከሰርጥ:
Share
Digital
Inspire
የሰርጥ አድራሻ: @mediasuccess
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.15K
የሰርጥ መግለጫ

#Motto
በልሕቀት እያደግን እናሳድጋለን

⭐️ስብእናችንን እንገንባ🇪🇹
⭐️አስተሳሰባችንን እንቀይር🇪🇹
ማንኛውንም አይነት ሀሳብ ለመስጠት
በ @ZHibretbot ወይም
@Zhibret24💟 ይጠቀሙ።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-13 15:19:13 ከፍታው ላይ እንገናኝ!

ውስጣችሁ የሚናገር አንበሳ የሆነ ድምፅ አለ፤ ምንም ነገር እንደማያቅታችሁ፣ እንደምትችሉ፣ ጀግና እንደሆናችሁ አጥብቆ የሚነግራችሁ፤

በደምብ አድርጋችሁ
ስሙት!

እመኑት!

እስከዛሬ ሰው ጫን አርጎ የሚነግራችሁን ድክመት አምናቹህ የለምን ?

ከዚህ በኋላ ግን ጆሯችሁ የሚከፈተው ለሚለውጣችሁ ወይም ለሚያሳድጋችሁ ነው እንጂ ወደ ኋላ ለሚጎትታችሁ አይሁን!

"የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም" ነው አባባሉ፤

አሁን ራሳችሁን ለመለወጥ ልባችሁ ተነስቷል ማፈግፈግ የለም!

ከፍታው ላይ እንገናኝ ቤተሰብ

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
846 viewsedited  12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 00:01:42

እዉነት እኔ የራሴን ቢዝነስ ሰርቼ ሃብታም መሆን እችላለሁ?

ብዙ ሰዎች አሁን ካላቸዉ ኑሮ የተሻለ ህይወት ለመኖር ይመኛሉ፡፡ ምኞት ብቻዉን ግን በቂ አይደለም፡፡ ብዙዉን ጊዜ ምኞት በስራና በጠንካራ ዲሲፕሊን ካልታገዘ የሚያልሙትን ህይወት ማግኘት ከህልምነት አያልፍም፡፡

በምኞት ብቻ የሚዋልሉ አቋራጭ ፍለጋ ላይ ያተኩራሉ፡ ሎተሪ መቁረጥ፣ ሃብታም ባል ወይንም ሚስት ፍለጋ መባዘን፣ ስራ ላይ በሚከሰት አደጋ ጠቀም ያለ ካሳ ለማግኘት ማለም፣ ዉርስ መጠበቅ፣ ሙስና፣ ወዘተ፡፡ ምንም እንኳን ከላይ የተጠቀሱት እና ሌሎች አቋራጮች አልፎ አልፎ ቢሳኩም አብዛኛዉን ጊዜ ግን መና ሆነዉ ሲቀሩ ይታያል፡፡

ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ደግሞ በተቃራኒዉ ገና በጠዋቱ እጅ ሰጥተዉ ያለ ህልም ወይንም ራእይ እድሜያቸዉን ይገፋሉ፡፡

በህሊናቸዉ ነገሮች ከባድ እንደሆኑ እና የተሳካ ህይወት የነርሱ ሊሆን እንደማይችል ራሳቸዉን አሳምነዉ ተቀምጠዋል፡፡ እኔማ ተምሬ ዲግሪ አልይዝም፣ የራሴን ቤት ሰርቼ ከኪራይ ልወጣ የማይታሰብ ነዉ፣ክብደትማ በፍፁም መቀነስ አልችልም፣ ወዘተ እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦች ብዙዎችን ሳይሞክሩ እጅ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል፡፡

በጣም በርካታ ሰዎች እድሜያቸዉን ሙሉ ለዚህ ወይንም ለዚያ ድርጅት ሲሰሩ አሳልፈዉ የጡረታ ጊዜ ሲቃረብ እንዴት እሆን ፡ ይሆን የሚለዉ ስጋት መምጣት ይጀምራል፡፡ እድሜ እየገፋ ሲሄድ አቅም ስለሚቀንስ ተሯሩጦ መስራት አማራጭ አይሆንም፡፡ ለጤና የሚደረገዉ ወጪም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የጡረታዉ ገቢም የሚያወላዳ አይደለም (በተለይም የዋጋ ግሽበት በቀጣይነት ሊኖር ስለሚችል) ፡፡

በደህና ጊዜ ልጆቹን ለቁምነገር ያበቃ የልጆቹን እጅ ማየት ሊኖርበት ነዉ፡፡ አሊያም ልጆቹን ያሳደገበትን ቤት ሸጦ ትንሽ ቤት ሰርቶ ወይ ገዝቶ ቀሪዉን እየበላ ኑሮዉን ይገፋል፡፡

ታዲያ ስኬትን እንዴት ማግኘት ይቻላል?

#ወደሃብት_ጉዞ 

ቢዝነስ ለነጋዴ ልጅ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች የንግድ ስራ በቤተሰብ የሚወረስ ብሎም ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ የተተወ ይመስላቸዋል፡፡ በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ቤተሰብ ዉስጥ መኖር ስለንግድ የተሻለ እዉቀት እንዲኖር ሊረዳ ቢችልም ሌላ ሰዉ ሊማረዉ አይችልም ማለት ግን አይደለም፡፡

ተነሳሽነቱ እና ቁርጠኝነቱ ካለ በየትኛዉም መስክ የሚፈለገዉን እዉቀት ማዳበር ይቻላል፡፡ መማር መመረቅ መቀጠር ከሚለዉ የተለመደ ወይንም ካደግንበት አስተሳሰብ ወጥተን ስራ ፈጠራን፣ የራስ ቢዝነስን ማደራጀት መሞከር ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ ኑሯችን ወይ ከእጅ ወደአፍ ነዉ አሊያም ሰዉ የቆረጠልንን ደሞዝ እየጠበቅን የሌሎችን ስኬት ማፋጠን ብቻ ይሆናል የኛ ሚና እና መዳረሻ፡፡

መቼም ሁሉም ሰዉ የራሱን ቢዝነስ የሚሰራ ሆኖ የሚቀጠር ሰዉ አይኖርም ወይንም አይኑር ማለት አይደለም፡፡ ህይወቱን መቀየር እና ሃብታም መሆን የሚፈልግ ሰዉ ግን ጠዋት ገብቶ እስከ አስራ አንደ ሰአት ሰርቶ በወሩ መጨረሻ ሰላሳ ቀን ሰርቶ አንድ ቀን የሚከፈለውን ወይም የሚሰጠዉን ደሞዝ ከመጠበቅ ወጥቶ የራሱ ጌታ ወደሚሆንበት አስተሳሰብ እና ተግባር መሸጋገር ይኖርበታል፡፡ ይህን ማድረግ ቀላል አይደለም ግን ከልብ ካለቀሱ እንደሚባለዉ ነዉ ነገሩ…. ቤተሰቦች!

ብዙዎች ስለኑሯቸዉና ህይዎታቸዉ ያማርራሉ ግን ደግሞ የለመዱትን ቢሮ ገብቶ መዉጣት አኗኗር ለመቀየር ቁርጠኝነት ይጎድላቸዋል፡፡ ስለሆነም ደስተኛም ባይሆኑ አዲስ ነገርን ፍራቻ ባሉበት መቆየትን ይመርጣሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜ ወሬያቸዉ ኑሮ ተወደደ፣ ኪራይ ጨመረ… ድሮ ጊዜዉ ጥሩ ነበር ወዘተ የሚሉ አይነት ባህሪያትን እነርሱ ላይ ማየት የተለመደ ነው፡፡

በተቃራኒዉ ለለዉጥ ቀበቷቸዉን ያጠበቁት ደግሞ ምን እናድርግ፣ ምን ብንሰራ ያዋጣል፣ እያሉ መረጃ መለዋወጥ እቅድ ማዉጣት ይሆናል፡፡

ችግርን ደጋግመዉ ቢያወሩት ጊዜን ለማቃጠል ካልሆነ በራሱ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ባሉበት መርገጥ ነዉ መጨረሻዉ፡፡ ራስን በመቀየር ሁሌ ደሞዝ ጭማሪና እድገት ከመጠበቅ አዙሪት ወጥቶ የሚፈልጉትን ህይወት መምራት ይቻላል፡፡ ይህን በማድረግ (የገንዘብ ነፃነትን በማግኘት) ሌሎች እድሜያቸዉን ሙሉ ደሞዝን ስለማብቃቃት ሲያወሩ ስለሌላ አላማ እና ግብ ወይንም የሚወዱት ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ ይቻላል፡፡

ብዙዎች አዳዲስ ሀሳብ የሚይዙበት ፣ ራሳቸውን እንዲመረምሩና እንዲጠይቁ እናግዛቸው ዘንድ #ሼር ይደረግ።

ደስ ብሎኛል ስላነበባችሁት .... ውብ አሁን ተመኘሁ !

አዘጋጅ : ዚ ( ጤናማ ቃላት)

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.3K viewsየሆነ ቦታ የሚኖር የሆነ ሰው, 21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 00:33:30

በጦርነት ጊዜ የአዕምሮ ጤንነትዎን መረዳት!

በሀገራችን ላይ ጦርነት እና የጦር ወሬ መስማት ከጀመርን ሰነባብተናል። ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠሩ ቀዉሶች እና መፈናቀሎች፣ አብዛኛዎቹ ሰዎች ፣ የጭንቀት ፣ የሀዘን ፣ እና የንዴት ስሜቶችን ማስተናገዳቸዉ ጤናማ እና ተገቢ ናቸው። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ለጦርነቱ የበለጠ ጥልቅ እና ደካማ ምላሽ ሊኖራቸው ይችላል።

ሁሉም ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ላይ በተለያየ መንገድ ምላሽ እንደሚሰጥ እና እያንዳንዱ ሰው ለከባድ ስሜቶች የራሱ የሆነ የመቻቻል ደረጃ እንዳለው ማስታወስ አስፈላጊ ነው። እነዚህን ስሜቶች ለመቋቋም ለራስህ እና ለሌሎች ልታደርጋቸው የምትችላቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ። በዓለማችን ውስጥ መሰማራታችን ፣ ከሰዎች ጋር መገናኘታችን እና ከፊታችን ስላሉ ፈተናዎች ብሩህ አመለካከት መያዝ ሌሎች አሰቃቂ ጊዜያትን ለማለፍ ቁልፍ ናቸው ይላሉ። በእርግጥ ፣ በችግር ጊዜ፣ ሰዎች ህይወታቸውን እና የህይወት እርካታን የሚያሻሽሉ ለውጦችን ማድረግ ይችላሉ።

ለተዛባ ሁኔታ መደበኛ ምላሽ ምን እንደሆነ እና ምን ምልክቶች የበለጠ ከባድ ችግር እንዳለቦት ማወቅ ከአእምሮ ጤና ባለሙያ እርዳታ መቼ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ይረዳዎታል።

◍ የተለመዱ ምላሾች

በጦርነት ጊዜ፣ ወይም በአሰቃቂ ሁኔታ ስሜትዎን ለመቆጣጠር መቸገር የተለመደ ነው። ብዙ ሰዎች እንደዚህ ያሉ ምልክቶች ያጋጥሟቸዋል፡

➲ግዴለሽት መደንዘዝ
➲ቁጣ
➲የአቅም ማጣት ስሜት
➲በአመጋገብ ዘይቤ ላይ ከፍተኛ ለውጦች ፤ የምግብ ፍላጎት ማጣት ወይም ከመጠን በላይ መብላት
➲"በማይታወቅ ምክንያት" ማልቀስ
➲ራስ ምታት እና የሆድ ህመም
➲ለመተኛት መቸገር
➲ከመጠን በላይ አልኮል እና አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም

እርዳታ ለመፈለግ ምልክቶች

ስሜቶች ካልጠፉ ወይም በጣም ኃይለኛ ከሆኑ በዕለት ተዕለት ኑሮዎ ውስጥ የመሥራት ችሎታዎን ሲያበላሹ የአእምሮ ጤና እንክብካቤ የሚያስፈልገው ሊታወቅ የሚችል መታወክ ሊኖርብዎ ይችላል። ለተፈጠረዉ ቀውስ መደበኛ ምላሽ እየሰጡ እንደሆነ ወይም የአእምሮ ጤና ችግር እያጋጠመዎት እንደሆነ ለማወቅ የሚረዱዎት ምልክቶች አሉ። እነዚህ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡

➲ ስለ ጦርነት ወይም አሰቃቂ ክስተት ቅዠቶች እና ተደጋጋሚ ሀሳቦች

➲ስለ ጦርነቱ ወይም ስለ አንድ አሰቃቂ ክስተት ማሰብ ማቆም አለመቻል

➲አሰቃቂ ክስተትን የሚያስታውሱ ሀሳቦችን፣ ስሜቶችን ወይም ንግግሮችን ማስወገድ

➲አሰቃቂ ክስተት የሚያስታውሱ ቦታዎችን ወይም ሰዎችን ማስወገድ አስቀድሞ የታሰበ የወደፊት ስሜት መኖር

➲ለመተኛት መቸገር

➲ የመዝለል ወይም በቀላሉ የመደንገጥ ስሜት

➲ ስለ ደህንነት ከመጠን በላይ መጨነቅ

➲ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ዋጋ ቢስ ወይም ተስፋ ቢስነት

➲ በእንቅስቃሴዎች ደስተኛ አለመሆን

➲ ስለ ሞት ወይም ራስን ስለ ማጥፋት ማሰብ እነዚህ ምልክቶች ከታዩ፣ አልያም እነዚህን ስሜቶች የሚሰማዎ ከሆነ እባክዎን በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የአዕምሮ ህክምና ተቋም በመሄድ ከባለሙያ ሙያዊ ድጋፍን ይጠይቁ፡፡

◍ ስለ ጉዳዩ ይነጋገሩ:

ከሌሎች ጋር በመነጋገር፣ ጭንቀትን ማስታገስ እና ሌሎች ስሜትዎን እንደሚጋሩ መገንዘብ ይችላሉ።

◍እራስዎን መንከባከብ፡

ብዙ እረፍት ያድርጉ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ ፣ ከመጠን በላይ መጠጣትን ያስወግዱ ፤ ምግብ በትክክል ይመገቡ። ከፍተኛ የካሎሪ እና የስብ ይዘት ያላቸውን ምግቦች ያስወግዱ።

◍ ለጦርነቱ ምስሎች ያሎትን ተጋላጭነት ይገድቡ፡

በተለይም በምስል በማህበራዊ የመገናኛ አዉታሮች እንዲሁም በቴሌቭዥን የሚቀርቡ ፕሮግራሞችን ያስወግዱ።

◍ አንድ አዎንታዊ ነገር ያድርጉ፡

ደም ይስጡ፣ በሠራዊቱ ውስጥ ላሉም ሆነ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ የድጋፍ ዝግጅቶች ያዘጋጁ፣ ጦርነቱን ብደግፉም ቢቃወሙም ፣ ለተመረጡት ባለስልጣናት ደብዳቤ ፃፉ ፤ ሃሳብዎን ያጋሩ ፣ በማህበረሰብ ስብሰባዎች ላይ መሳተፍን ይልመዱ ፣ ወዘተ...

➲እርዳታ ይጠይቁ፡ እርዳታ መጠየቅ የድክመት ምልክት አይደለም። ከታመነ ዘመድ ፣ ጓደኛ ወይም መንፈሳዊ አማካሪ ጋር ይነጋገሩ። የባለሙያ እርዳታ ከፈለጉ ፣ እባክዎን በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የአዕምሮ ህክምና ተቋም በመሄድ ከባላሙያ ጋር ይነጋገሩ።


አዘጋጅ : ዚ ( ጤናማ ቃላት)

ምንጭ፡- ብሔራዊ የአእምሮ ጤና ማህበር (ለፔጁ በሚያመች መልኩ እርማት የተደረገበት)
በፊራኦል መስፍን


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.0K viewsየሆነ ሰው, 21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-01 14:10:56

#ፍርሀት

ብዙ ሰዎች ሕይወትን የሚኖሩት ልክ ለዝግጅት እንደሚደረግ ልምምድ ነው። ህይወት ልምምድ ሳትሆን የዋንጫ ጨዋታ ናት፡፡ ማንም ሰው ነገ በሕይወት ለመኖሩ ማረጋገጫ የለውም። ያለን ጊዜ አሁን ብቻ ነው። ልንቆጣጠረው የምንችለውም አሁናችንን ብቻ ነው። የአሁኑ ቅፅበት ላይ ትኩረት ስናደርግ ፍርሀትን ከአዕምሯችን እናስወጣዋለን።

ፍርሀት ማለት ምናልባት ወደፊት ሊፈጠር ስለሚችል ነገር መስጋት ነው። በቂ ገንዘብ ላይኖረን ይችላል፤ ልጆቻችን የሆነ ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤ እያረጀን ነው፤ ልንሞት እንችላለን . . . የመሳሰሉት።

ፍርሀትን ለመፋለም ምርጡ መንገድ ትኩረታችንን አሁን ላይ ማድረግ ነው።

በተሻለ መንገድ ልገልፀው የምችል አይመስለኝም ማርክ ትዌይን “በሕይወቴ ስለ ብዙ ነገሮች ተጨንቄ አውቃለው። ግን የተወሰኑት ብቻ ናቸው የእውነት የተከሰቱት።” ብሏል።

ቀላሉን ነገር አታካብድ ፤
ዶ/ር ሪቻርድ

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.0K views , 11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-17 12:19:24 ለጊዜው ጅል መምሰል ወይም ለዘላለሙ ጅል መሆን?

የሚጠይቅ ለደቂቃ ጅል ይሆናል የማይጠይቅ ግን ለዘለአለሙ ጅል እንደሆነ ይቀራል ይባላል።

እንደ ህዝብ ጅል ሆነን የቀረነው ስለማንጠይቅ ነው። የተነገረንን እንደ ፈጣሪ ቃል ሳናገናዝብ ስለምንቀበል፣ የሚወረወርልንን እንደወረደ ስለምንቀልብ፣ ያጎረሱንን ሳናላምጥ ስለምንውጥ፣ ያጠጡንን ሳናጣጥም ስለምንጋት ነው።

ብንጠይቅ ለቅፅበት ጅል እንመስላለን። አላዋቂዎችም ለግዜው ሊዘባበቱብን ይችላሉ። ሳንጠይቅ ከቀረን ግን ለዘለአለሙ ጅል ሆነን እንቀራለን። ምርጫው ሁለት ነው። ምርጫው ቀላል ነው። ለግዜው ጅል መምሰል ወይም ለዘለአለሙ ጅል መሆን!

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.7K viewsየሆነ ቦታ የሚኖር የሆነ ሰው, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-27 09:20:40

ዓለም በተቃራኒ ሃሳቦችና ደስ በማይሉ ስሜቶች ስትከባቹ፤ ውስጣዊ እናንተነታቹ ዋጋ ሲያጣ፤ በራስ መተማመናቹ ሲያሽቆለቁል፤ ራሳቹን ዋጋ የሌለው ሰው
አድርጋቹ ማሰብ ስትጀምሩ፤ ለራሳቹ ያላቹ ክብር ዝቅ ሲል፣ ጥያቄያቹ ብቻ በዝቶ አዕምኣቹ መልስ ማመንጨት ሲቸገር፤ ልቦናችሁ ሲፈዝ፣ እይታችሁ ሲደበዝዝ፣ የሃሳብ ጨለማ ሲውጣችሁ፣ ተስፋችሁ ሲሟጠጥ፣ ለመኖር ያላችሁ ፍላጎት ጣዕም ሲያጣ፤ ደስታ ዳገት ሲሆንባችሁ፣ እርካታ እንደሰማይ ሲርቅባችሁ፣ ሰውነታችሁን የሚያድን፣ የአዕምሮ ሕመምህን የሚያሽል፣ ከጥቀርሻ አስተሳሰባችሁ የሚያላቅቃችሁ መድሐኒት ስታጡ፣ ከራሳችሁ ጋር ቁርሾ ውስጥ ስትገቡ፤ ከትናንታችሁ ስትጣሉ፤ ከትዝታችሁ ጋር ጣውንት ስትሆኑ፣ አጠገባችሁ ካሉ ሰዎች ጋር ተግባብቶ መኖር
ሲከብዳችሁ፣ እውነት ሲርቃችሁ፣ ሐቅ ሲጠፋባችሁ፣ የእኔ የምትሉት ሃሳብም ሆነ ሰው ሳይኖራችሁ ሲቀር፣ የሕይወት ትርጉሙ ሲምታታባችሁ፣ ዓላማ የለሽ ስትሆኑ፣ የምትኖሩለትና የምትሞቱለት ነገር ስታጡ፣ ወዘተ በማንነታችሁ ላይ አደጋ ሲጋረጥ፣ በሰውነታችሁ ላይ ተግዳሮት ሲበዛ፣ አዕምሯችሁ ሲዋከብ፣ ስሜታችሁ ሲጣደፍ አደጋ ላይ ናቹ፡፡

አዎ አደጋ ላይ ናችሁ!
ቀይ እያበራችሁ ነው!


የነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ምንጩ ማንም ሳይሆን የገዛ ራሳችሁ አስተሳሰብ ነው፡፡

➣መከራችሁ የተሰራው በራሳችሁ ነው፡፡

➣ጠላታችሁን የምታስቡበት መንገድ ነው፡፡

➣ባላንጣችሁ የተጭበረበረው እይታችሁ ነው፡፡

➣ሞራላችሁ የወደቀው፣ መንፈሳችሁ ታች የወረደው በሌላ በማንም ሳይሆን በራሳችሁ አመለካከት ነው፡፡ ማንም ተጠያቂ የለም፡፡ ተጠያቂው እናንተና እናንተ ብቻ ናችሁ። እናስ? ካላችሁ...
እናማ ከፍ እያለ የመጣውን የወደቀ ስሜታችሁን ተቆጣጠሩት።

➣ከራሳችሁ ጋር ተነጋገሩ

➣አመለካከታችሁን ወይም አተያየታችሁን ለውጡ።

➣ጥሩ የሆናችሁበትን ስራ ደጋግማችሁ ስሩ።

➣ባለፈው ታሪክ መደሰት ወይም ትዝታችሁን ለሌሎች አጋሩ።

➣ዋጋ እንዳላችሁ እመኑ።

➣ስሜቶችህን በጥንቃቄ አካፍሉ። ተንቀሳቀሱ።

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.9K viewsየሆነ ቦታ የሚኖር የሆነ ሰው, 06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-09 17:38:06

Law of attraction

አንድ የመንደር ሰው ገንዘብ ገንዘብን ይስባል የሚል ጥቅስ የሆነ መፅሀፍ ላይ ያነባል።እጁ ላይ ያለው አንድ ብር ብቻ ሲሆን በጣም ድሀ ነበር።ገንዘብ ገንዘብን የሚስብ ከሆነ ብዙ ገንዘብ ያለበት ቦታ በመሄድና አንዷን ብር ከገንዘቡአጠገብ በማስቀመጥ ብዙ ገንዘብ መሳብ እንደሚችል አሰበ።እናም ወደ ከተማ ሄደና ከአንድ ሀብታም ነጋዴ ሱቅ ደረሰ።ምሽት ላይ ስለነበር ሁሉም የሽያጭ ገንዘቦች በመቆጠር ላይ ነበሩ።በሱቁ የመግቢያ ደረጃ ላይ ቁጭ ብሎም የያዛትን አንድ ብር ማርገብገብ ጀመረ።ለረጅም ጊዜ ቢያርገበግብም ሌላ ምንም ብር ተስቦ ሊመጣ አልቻለም።ይሄን ጊዜ በጣም ስለራቀ እንደሆነ አሰበ።እናም የያዘውን አንድ ብር ባልኮኒው ላይ ከተከመሩት የነጋዴው ረብጣ ብሮች ላይ ወርውሮ ጣለው።የሱ አንድ ብር ከሌሎች ብሮች ጋር ሆኖ ተመልሶ ይመጣል በሚል ጥቂት ጠበቀ። ይህ ግን አልተከሰተም።ከዛም ወደ ነጋዴው ሄደና:-"መፅሐፉ ትክክል አይደለም፤እባክህን ብሬን መልስልኝ።"ሲል ጠየቀው።

#ነጋዴውም:-"የትኛው መፅሀፍ?"ሲል ጠየቀው።
#መንደሬውም:-"ገንዘብ ገንዘብን ይስባል የሚል ጥቅስ አንድ መፅሀፍ ውስጥ አንብቤ ነበር፤"ሲል መለሰ።
#ነጋዴውም:-"ታዲያ ትክክል ነዋ፤ገንዘቦቹኮ ገንዘብን ስበዋል።አሁን ቀጥ ብለህ ወደ ቤትህ ሂድ፤ሁለተኛ አንድን ነገር ባንድ አቅጣጫ በኩል ማየት የለብህም የግብፅ ፒራሚድ እንኳን ከተለያየ አቅጣጫ ሲታይ የተለያየ ቅርፅ አለው።" አለው። ከዚያ ቀን ወዲያ ያ ምስኪን ሰው መፅሐፉ ስህተት እንደነበር ለማንም ተናግሮ አያውቅም፤ምክንያቱም መፅሐፉ ትክክል መሆኑን አረጋግጧል።

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.4K viewsየሆነ ሰው, 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-26 22:18:19

አንድ . . . በ . . . አንድ

ማንኛውንም ተግባር በተዋጣለት ሁኔታ ለመፈጸም ብቃቱ ኖሯችሁ ሳለ እንዳይሳካ ከሚያደርጉ እንቅፋቶች አንዱ ሁሉን ነገር በአንድ ላይ የማሰብ ዝንባሌ ነው፡፡ አንድን ተግባር የማጠናቀቅ ሂደት ሶስት ነገሮችን ይነካል፡፡ መጀመር፣ መቀጠልና መጨረስ፡፡ ምንም ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ስለእነዚህ ሶስት ሂደቶች በሚገባ ካሰባችሁ በኋላ እያንዳንዳቸውን ሂደቶች ሳትደራርቡ መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው፡፡

ማለትም ለምሳሌ፣ በመጀመር ሂደት ጊዜ ስለመቀጠልና ስለመጨረስ መጨነቅ ትኩረታችሁን ከጅማሬው ላይ እንድታነሱ ወይም የመቀጠሉንና የመጨረሱን ጉዳይ ፈርታችሁ እንድትመለሱ ያደርግላቹኃል፡፡ አንዴ ከጀመራችሁ በኋላ ደግሞ መለስ ብላችሁ፣ “ምነው ባልጀመርኩት!” ወይም ደግሞ ወደፊት አይታችሁ “እንዴት ይሆን የምጨርሰው!” በማለት ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን ካባከናችሁ ወደፊት መቀጠላችሁ አጠራራሪ ነው፡፡

የመጀመር ሂደት

ማንኛውም ነገር እንዲቀጥልና እንደፈጸም በቅድሚያ ሊጀመር ይገባዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሁሉን ነገር በአእምሯቸው በማውጣትና በማውረድ ሲያስቡት ይከርማሉ እንጂ አንድም ነገር አይጀምሩም፡፡ የተግባር ሰው አለመሆን፣ ስለነገሩ ቀጣይነት መጨነቅና ምናልባት ካልጨረስኩት አፍራለሁ የሚል ፍርሃት ሊጠቀሱ የሚገባቸው እንቅፋቶች ናቸው፡፡

የመቀጠል ሂደት

ማንኛውንም ነገር አንዴ አምናችሁበት ከጀመራችሁ በኋላ በሙሉ ኃይላችሁ ወደፊት የመቀጠልን ነገር በቁርጠኝነት መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደጠቀስነው “ምነው ባልጀመርኩና እንዴት ይሆን የምጨርሰው” የሚሉ ሃሳቦች ለቀጣይነት አስጊ የሆኑ እንቅፋቶች ናቸው፡፡

የመጨረስ ሂደት

አንድን ነገር በምንም መልኩ ጀመራችሁት፣ በምንም መልኩ ቀጠላችሁት ዋናው ቁም ነገር የመጠናቀቁ ጉዳይ እንደሆነ አትዘንጉ፡፡ የመጀመርን አስፈላጊ ደረጃ አልፋችሁና የመቀጠልን ፈታኝ ወቅት ተሻግራችሁ ወደመጨረሻው ስትደርሱ ጉልበታችሁ ይፈተናል፣ እልህ ያስጨርሳቹሃል፣ እረፍት ያምራቹሃል . . .፡፡ አለመጨረስ ግን ክስረታችሁን ዘርፈ-ብዙ ያደርገዋል፡፡

አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ስለሶስቱም ደረጃዎች በሚገባ ማሰብና ማቀድ ተገቢ ነው፡፡ ሆኖም፣ አንዴ ከተራመዳችሁ በኋላ በመጀመሪያ ስለመጀመር ብቻ አስቡ፣ ከዚያም ስለመቀጠል ብቻ አስቡ፣ ከዚያም ስለመጨረሳችሁ ብቻ አስቡ፡፡

የጀመራችሁትን ስራ እየጨረሳችሁ የምትሄዱ ሰው እስክትሆኑ ድረስ በእርግጥም “ሰው” እንዳልሆናችሁ አትዘንጉ !ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.5K viewsየሆነ ሰው, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-17 20:14:29

ሴትየዋ ችግሯን ልታማክር ወደ ዶክተር ሄደች።

"ዶክተር እባክህ አንድ ችግር ገጥሞኛል።"

"ምን ገጠመሽ?"

".…ከወለድኩ ገና አንድ አመት አልሞላኝም። ሆኖም ሌላ ልጅ አርግዣለሁ። እኔ ደግሞ ተጨማሪ ልጅ በዚህ ወቅት እንዲኖረኝ አልፈልግም።"

"እና ምን ልርዳሽ?""

"ሆዴ ውስጥ ያለውን ልጅ ማስወረድ እፈልጋለሁ!"

ዶክተሩ ትንሽ አሰብ አደረገና “ለምን ከዚህ የተሻለ ሀሳብ አላቀርብልሽም?” ሲል ጠየቃት።

“ምን አይነት ሀሳብ?”

“አየሽ ይሄን ልጅ ከሆድሽ ለማስወረድ ብዙ ችግር ውስጥ ትገቢያለሽ ፤ ደም ይፈስሻል ፣ በቀጣይ ላትወልጂ የምትችይበት አጋጣሚም ሊፈጠር ይችላል ፣ ልትሞቺ ወይም ህይወትሽን ልታጪ ትችያለሽ ። ስለዚህ ይሄን ሁሉ ችግር ከምታስተናግጂ ለምን በእጅሽ ያቀፍሽውን ልጅ አንገድለውም?” አላት ።

ሴትየው ከልቧ አደነገጠች። ዶክተሩ ንግግግሩን ቀጠለ።

“አዎ! ለእናት እንደሆነ ሁሉም ልጅ እኩል ነው። ስለዚህ አንዱ መሞት ካለበት ሆድሽ ውስጥ ያለው ከሚሞት ይሄኛው የተወለደው ቢሞት ምንም ችግር ሳይገጥምሽ ሀሳብሽን ታሳኪያለሽ…” እያለ ምክረ ሀሳቡን መተንተን ጀመረ።

ሴትየዋ ግን በጆሮዋ የሚንቆረቆረው የዶክተሩ ሀሳብ ሳይሆን የአምላክ ማሳሰቢያ መሆኑን እያሰበች ለማስወርድ የዘረጋቻቸውን ሁለት እግሮቿን ሰብስባ ብድግ ብላ ክፍሉን ለቃ መውጣት ጀመረች።..…ልጆቿን አንዱን በክንዷ ሌላውን በሆዷ እንዳቀፈች ወደ ቤቷ ተመለሰች።

አዎ! የተወለደም በሆድ ውስጥ ያለም ቢሆን ለእናት ልጆቿ ሁሉ እኩል ናቸው!!!

አዎ! የተሰጠንን ብናውቅ ፣ የተቀመጠልንን ብናገናዝብ ብዙ ጥፋት ውስጥ ባልገባን !


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.4K viewsCEO MediaSuccess, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-13 12:35:30

ከጓደኞቼ ጋር አዲስ አመትን ካዝሚር ዛፍ ስር ተሰባስበን እያከበርን ነበር፡፡
፡
ከትንሽ ቆይታ በኋላ የበሰለ ፍሬ እጄ ውስጥ ወደቀ፡፡ ስቀምሰው እጅግ ጣፋጭ ሆኖ አገኘሁት በኋላ እንጨት አምጡ ብዬ ፍሬውን ዳግም አርግፌ መብላት ስጀምር መረረኝ፡፡
፡
እንዴት ነው ነገሩ ?! እጄ ላይ የወደቀው ፍሬ ጣፋጭ ነበር ፡ አሁን ያራገፍኩት ግን መረረኝ ስል፤ ከጓደኞቼ መካከል አንዱ እንዲህ አለኝ

"የመጀመሪያው በጊዜው ስለወደቀ ጣፈጠህ ሁለተኛውን ያለጊዜው ስላራገፍከው መረረህ" አለኝ፡፡

ተመልከቱ ፈጣሪ የሚጠቅመንን ነገር በጊዜ እጃችን ውስጥ ይጥለዋል፡፡ እኛ ግን በግድ ይሁን ብለን በምናስቸግረው ጊዜ ጣፋጭ ያልሆነ ፍሬ እጃችን ውስጥ ይቀራል፡፡

የትዕግስት ተራራ ላይ ሆነን አምላካችንን
እንጠብቀው፡፡ ልመናችንን በራሱ ጊዜ ይፈጽመው ዘንድ እድል እንስጠው፡፡
የእርሱ ከሆነ ጣፋጭ ነውና።

ትዕግስት ሀያል ናት።

ጥረታችሁን ቀጥሉ ... የበሰለ ፍሬ ምንበላበት ጊዜ እየቀረበ ነው ወዳጆቼ


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.5K viewsየሆነ ቦታ የሚኖር የሆነ ሰው, 09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ