Get Mystery Box with random crypto!

☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ huda4eth — ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA
የቴሌግራም ቻናል አርማ huda4eth — ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA
የሰርጥ አድራሻ: @huda4eth
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.10K
የሰርጥ መግለጫ

☀ሁዳ መልቲሚዲያ - ‌🇭‌🇺‌🇩‌🇦 ‌🇲‌🇺‌🇱‌🇹‌🇮‌🇲‌🇪‌🇩‌🇮‌🇦 -قناة هدى الاسلامية
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ንፁህ ኢስላማዊ እውቀት ይደርሳቸው ዘንድ እንሰራለን!
ለአስተያየት @nuugaa

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-05 17:45:57 ፨ሉቃስ ቴዎፍሎስ ለሚባለው ጓደኛው የጻፋለት ደብዳቤ እንጂ ወንጌል አይደለም፥ ለጓደኛው የጻፈው ደግሞ ጓደኛው ስለ ተማረው ቃል እርግጡን እንዲያውቅ መልካም ሆኖ ስለታየው እንጂ በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ አይደለም።
፨ማቴዎስ ደግሞ በ 50 ድኅረ ልደት ለዕብራውያን በዕብራይስጥ ደብዳቤ ጽፎ ሳለ ይህ ደብዳቤ ሲጠፋ በማቴዎስ ስም ማንነቱ የማይታወቅ ሰው የማርቆስን ትርክት መሠረት አድርጎ የማቴዎስ ወንጌልን አዘጋጀ።
፨የዮሐንስን ወንጌል የጻፈው ሽማግሌ ዮሐንስ"John the Presbyter" ሲሆን ከሐዋርያው ዮሐንስ ይለያል።
፨ሉቃስ እና ማርቆስ ደግሞ የጳውሎስ ጓደኞች ናቸው እንጂ የኢየሱስ ሐዋርያት አይደለም።

ሆነም ቀረ የመጀመሪያዎቹ የማቴዎስ፣ የማርቆስ፣ የሉቃስ፣ የዮሐንስ ወንጌላት ጠፍተዋል፥ ከአንዱ አምላክ ለኢየሱስ የተሰጠው ወንጌል አንድ ሆኖ ሳለ የኢየሱስን ወንጌል ከሠራው ተአምር ጋር ታሪክን ብዙዎች ሲያዘጋጁ ወደ 47 የሚደርሱ ወንጌላት ደርሰው ነበር።
ከእነዚህ ወንጌላት ሄለናዊ ክርስትና"hellenistic christianity" ስለ ህማማት(ስቅለት እና ግድለት) የሚናገረው አራት ወንጌላት መርጦ ሌሎችን ወንጌላት ሳይቀበል ቀርቷል፥ እነዚህ አራት ወንጌላት ከመጻፋቸው በፊት አንድ ወንጌል እንደነበረ እና ያ ወንጌል እንደጠፋ ምሁራን እንዳስቀመጡ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአዲስ ኪዳን መግቢያ ላይ ተቀምጧል።
ስለዚህ ሄለናዊ ክርስትና ከአሏህ ዘንድ ለዒሣ በተሰጠው ኢንጂል ላይ ታሪክን በመጨመር "ከአሏህ የሆነ ግልጠተ መለኮት ነው" ብለው ዋሽተዋል፦
2፥79 ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَـٰذَا مِنْ عِندِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ
3፥71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በሐሰት ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?» يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

"እውነቱን በሐሰት ለምን ትቀላቅላላችሁ" የሚለው ይሰመርበት! ሄለናዊ ክርስትና ከአሏህ ዘንድ ለዒሣ በተሰጠው ኢንጂል ላይ ታሪክን መጨመር ብቻ ሳይሆን ከተሰጠው ኢንጂል ላይ እውነትን በመደበቅ ቀንሰዋል፥ ከተቀነሱት መካከል ስለ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት የሚናገረው የምስራች ነው፦
7፥157 ለእነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራት እና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍ እና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልእክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት በእርግጥ እጽፍለታለሁ፡፡ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِندَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنجِيلِ
61፥6 የመርየም ልጅ ዒሣም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥ እና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልእክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልእክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِن بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ

"የማበስር" የሚለው ይሰመርበት! "ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልእክተኛ ስሙ አሕመድ" የሚለው የምስራች አራቱ ወንጌላት ላይ ከሌለ እንግዲያውስ አምላካችን አሏህ ኢንጅል እያለ የሚነግረን ከእርሱ ዘንድ ወርዶ ለዒሣ የተሰጠው ስለ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት የሚናገረው ነው፦
3፥3 ተውራትን እና ኢንጂልን አውርዷል፡፡ وَأَنزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ
3፥4 ከቁርኣን በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፡፡ "ፉርቃንንም አወረደ"፡፡ مِن قَبْلُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ الْفُرْقَانَ

"ፉርቃን" فُرْقَان የሚለው ቃል "ፈረቀ" فَرَقَ ማለትም "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "እውነትን ከሐሰት የሚለይ" ማለት ነው፥ አሏህ ስለ ተውራት እና ኢንጅል መውረድ ከነገረን በኃላ በእነርሱ ላይ የተጨመረውን ሐሰት ከአሏህ ዘንድ ከወረደው እውነት የምንለይበትን ፉርቃን በባሪያው በሙሐመድ"ﷺ" ላይ አውርዷል፦
25፥1 ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብር እና ጥራት ተገባው፡፡ تَبَارَكَ الَّذِي نَزَّلَ الْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِ لِيَكُونَ لِلْعَالَمِينَ نَذِيرًا
5፥48 ወደ አንተ መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭ እና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ

ቁርኣን ከበፊቱ ከአሏህ ዘንድ የወረደውን 4፥136 "ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ" በማለት መለኮታዊ ቅሪትን የሚያረጋግጥ ስለሆነ "ሙሶዲቅ" مُصَدِّق ተብሏል፥ በእርሱ ላይ የጨመሩትን የሚያርም እና የሚቆጣጠር ስለ ሆነ ደግሞ "ሙሀይሚን" مُهَيْمِن ተብሏል። ቁርኣንን ፉርቃን፣ ሙሶዲቅ፣ ሙሀይሚን አርጎ ለሰጠን ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ክብር እና ምስጋና ይሁን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ


ወሠላሙ ዐለይኩም
1.8K viewsedited  14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 15:46:49
አሰላሙዓለይኩም
የነሲሓ ቲቪ የማህበራዊ ሚድያ ኦፊሽያል ገፅና ቻናሎቻችንን በተመለከተ፤ በፌስቡክ ቴሌግራምና ዩትዩብ ብቻ በ @nesihatv አድራሻ የምንገኝ መሆኑን እየገለፅን፤ ድጋፍ የምንጠይቅባቸው ሒሳቦቻችንም በ ibnu Masoud Islamic Center ስም ብቻ የተመዘገቡ በመሆናቸውን ለተከበራችሁ የነሲሓ ቤተሰቦች ማሳወቅ እንወዳለን።

ሰኔ 28/2015

ነሲሓ ቲቪ
2.1K views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 15:41:05
ኔትወርካቸው እንደነበረ ነው። የጥቅም ትስስሩን ባለሀብቶቻቸው አስቀጥለውታል። በፈለጉት ላይ የፈለገትን ለማድረግ የከረመ ልምድ አላቸው። ከሀሰት ምስክር እስከ ማስፈረድ የሚደርስ አቅም። ፍትህን ሀብታሞቻቸው በገንዘብ ተከፋዮቻቸው ደግሞ በጩኸት ይቀብሯታል። ፅንፈኛው ይመታህና ይከስሃል። ከዚያ ያሳስርሀል። በአንዲስአበባ በብዙ ቦታዎች እየሆነ ያለው ይህ ነው። የሚታሰረው ሌላ ነው። የተበደለው ሌላ ነው።

በጠሮ ኡስማን ኢብኑ አፋን መስጅድም የሆነው ይህ ነው። በጠሮ መስጂድ በሚገኙ በ5 አባቶችና ኡስታዞች ላይ የ3 አመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል!

ፍትህ ፍትህ ፍትህ

ፅንፈኛው እየሄደበት ያለው የረቀቀ አካሄድ የተቀናጀና በበጀት የታገዘ ለይቶ የማጥቃት ነጥሎ የማሰሰር እያሳሰረ በጩኸትና በገንዘብ ፍትህን መደበቅ ተክኖበታል። ያሳዝናል። በጣም ያሳዝናል።

Adugnaw Muche

تعليق
Note:-ፅንፈኛው =አህባሽ
1.9K viewsedited  12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 15:39:29
ጠሮ መስጂድ ላይ የተፈጠረው ምንድን ነው
===============================
የአሕባሽ ባለሃብቶች የበፊት ሰንሰለታቸውን ተጠቅመው ከአሐዳዊ የሙስሊም ጠል አመራር ጋር በማሴር የ3 አመት ጽኑ እስራት በንጹሐን ሙስሊሞች ላይ የማስፈረድ አቅም እንደት አገኙ?

ህፃን ሴት የደፈረ ባለጌ በ6 አመት እስራት ወዘተ በሚጨመላለቅበት ተጨባጭ፤ ምን ወንጀል ሠርተው ነው 3 አመት የተፈረደባቸው?

እነርሱ እንደሚሉት ዲናችንን እንማራለን በማለታቸው ውሃብያ ስላሏቸው ብቻ አሕባሽ አለመሆን እንደ ወንጀል ተቆጥሮ እንደት 3 አመት ይፈረድባቸዋል?

መጅሊሱስ ይሄን ጉዳይ ለምን በዝምታ አለፈው ዝም ካላለ ምን እየሠራ ነው? ምክንያቱም ብዙ ስሞታዎች በዚህ ጉዳይ ከአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ በአካል ቀርበውለታል።

አሁንም አልረፈደም። ያለ አንዳች ወንጀላቸው በግፈኞች የሴራ ሰንሰለት የተፈረደባቸው ንጹሐን ወንድሞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነፃ ተብለው በምትኩ ግፈኛ አሳሳሪዎች፣ የሐሰት መስካሪዎችና ያለ አግባብ ፈራጅ የሆኑ በደለኛ ዳኞች ተጠያቂ መደረግ አለባቸው።


አስቸኳይ ፍትሕ ለጠሮ መስጂዶች ወንድሞቻችንና ኡስታዞች

Cc:
===
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Addis Ababa Police

#ሼር_አርጉ
⊱⊰━━━━━━━⊱⊰━━━━━━━⊱⊰
1.9K viewsedited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 15:38:32
ለሎሚ ሜዳ አካባቢ ወጣቶች።
1.8K views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 15:36:20
ሰይድ ቁጥብን ረሂመሁላህ በተመለከተ ድሮ እለው እንደነበረው አሁንም የምለው "እርሱ ዓሊም አይደለም። ነገር ግን ለዲኑ ተቆርቋሪ የሆነ ሙስሊም ነበር።
"የስነ ፅሁፍ ሰው ነው ያልኩትም ከቋንቋ አንፃር በስነ ፅሁፎቹ የቃላት አጠቃቀሙን ለማለት ፈልጌ ነው።)

ሸይኽ ዶ/ር ዑስማን አልኸሚስ



(ግዜያችሁን ስለ ሰይድ በማጥናት የምታቃጥሉ ወንድሞች ሌላ ጠቃሚ እውቀት ላይ ግዜያችሁንና ጉልበታችሁን ብታሳርፉ እላለሁ!)

ኑጋ።
1.9K viewsedited  12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 22:09:41
ዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የሽሪዓ እዉቀት ማዕከል

መርካዛችን በአዲስ መልኩ በዘርፉ ልምድ ባላቸዉ ኡስታዞች መህበረሰቡን ለማገልገል ዝግጅቱን አጠናቆ ለመማርና ማስተማር ምቹ በሆነ ቦታ (አዳር እና ተመላላሽ)  ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ላይ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነዉ።

የትምህርት ፈረቃዎች

አዳር

ቀን ሙሉ

ከ 2:30-6:00

ከአስር እስከ መግሪብ


የሚሰጡ የት/ት አይነቶች

ቃዒደቱ አኑራኒያ (ለጀማሮዎች) ሐዲስ

ቁርአን በነዘር    (በእይታ)        ፊቅህ

ቁርአን በሒፍዝ (በሽምደዳ)    ሲራ

ሙራጀዓህ       (ክለሳ)           አዝካር

ዓቂዳ                                   አዳብ

ተፍሲር                                ቋንቋ

በተጨማሪም በ online ትምህርት እንሰጣለን

አድራሻ  አንፎ አደባባይ ከንግድ ባንክ ጀርባ ከሰዒድ መስጂድ ዝቅ ብሎ

          ለበለጠ መረጃ
            

+251911171786

+251910034682

በቴሌግራም ለመመዝገብ ከታች
ያለዉን ዩዘር ኔም ይጠቀሙ።
            

https://t.me/Ibnu_Yusuf1
https://t.me/Ibnu_Yusuf1

ዳሩል ዒልም የቂርአት ቻናላችንን ለመቀላቀል

https://t.me/merkezdarulilm1
https://t.me/merkezdarulilm1

ዳሩል ዒልም የቂርአት ግሩፓችንን ለመቀላቀል
https://t.me/merkezdarulilm2
https://t.me/merkezdarulilm2
2.7K views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 09:11:33
ለመሆን ሲኦሲ አለው ወይስ እንዲሁ ነው ወደ ስራ የሚገቡት?i የሚከተላቸው ህዝብ ግን ምን ቢያስነኩት ነው የነዚህ መጫዎቻ የሆነው? ብለውት ብለውት ልቡን ስለፈተሹት ያሻቸውን ይሰሩታል። ሲፈልጉ ሳር ያስግጡታል። ሲያሻቸው እየሱስን እንድታይ ብለው በርሃብ ይፈጁቷል። ሲያሰኛቸው ብልግና ይፈፅሙበታል። ህዝብ ሊነቃ ነው? የለም። ህግ አይጠይቃቸው ህዝብ አይጠይቃቸው። ህሊና የላቸው ሞራል አያውቁ። ግን ምን ሆነው ነው በዚህ መጠን አይናውጣ የሆኑት? በጣም ነው እንዴ የሚያማቸው?
ከነሱ በላይ ግን ህዝቡ ምን ሲሆን ነው የሚነቃው? የሮማው ቄሳር ኔሮ "ምነው ይሄ ህዝብ አንድ አንገት ኖሮት በሰይፍ በቀላሁት!" ያለው እውነት እሱ ስለሚያመው ብቻ ነበር ወይስ እንዲህ አይነት ህዝብ ገጥሞት ነው? ምን ጉድ ናቸው እባካችሁ!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
3.2K views06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 12:20:32
ዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የሽሪዓ እዉቀት ማዕከል

መርካዛችን በአዲስ መልኩ በዘርፉ ልምድ ባላቸዉ ኡስታዞች መህበረሰቡን ለማገልገል ዝግጅቱን አጠናቆ ለመማርና ማስተማር ምቹ በሆነ ቦታ (አዳር እና ተመላላሽ)  ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ላይ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነዉ።

የትምህርት ፈረቃዎች

አዳር

ቀን ሙሉ

ከ 2:30-6:00

ከአስር እስከ መግሪብ


የሚሰጡ የት/ት አይነቶች

ቃዒደቱ አኑራኒያ (ለጀማሮዎች) ሐዲስ

ቁርአን በነዘር    (በእይታ)        ፊቅህ

ቁርአን በሒፍዝ (በሽምደዳ)    ሲራ

ሙራጀዓህ       (ክለሳ)           አዝካር

ዓቂዳ                                   አዳብ

ተፍሲር                                ቋንቋ

በተጨማሪም በ online ትምህርት እንሰጣለን

አድራሻ  አንፎ አደባባይ ከንግድ ባንክ ጀርባ ከሰዒድ መስጂድ ዝቅ ብሎ

          ለበለጠ መረጃ
            

+251911171786

+251910034682

በቴሌግራም ለመመዝገብ ከታች
ያለዉን ዩዘር ኔም ይጠቀሙ።
            

https://t.me/Ibnu_Yusuf1
https://t.me/Ibnu_Yusuf1

ዳሩል ዒልም የቂርአት ቻናላችንን ለመቀላቀል

https://t.me/merkezdarulilm1
https://t.me/merkezdarulilm1

ዳሩል ዒልም የቂርአት ግሩፓችንን ለመቀላቀል
https://t.me/merkezdarulilm2
https://t.me/merkezdarulilm2
3.5K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 11:03:03
ታላቅ የምስራች ለላፍቶና አካባቢዋ ነዋሪዎች!
---------------
ክረምቱን ለልጅዎ ልዩ ኢስላማዊ ኮርስ በላፍቶ ቢላል መስጂድ ተሰናድቶ እየጠበቃችሁ ነው።

ቀድመው ልጅዎን ያስመዝግቡ

አላህ ካለ ሐምሌ 3 ይጀመራል
3.2K viewsedited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ