Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-11-14 12:22:22
ጥቆማ

በቅርብ ጊዜ ትልቅ ተወዳጅነትን ያተረፈዉ እና ብዙ ተከታዮችን ያገኘው እንዲሁም “ወደ ቀድሞ ከፍታችን እንመለሳለን” በሚል  የሚዲያ ሽፋን ላልተዳረሰባቸዉ ድምፅ ለመሆን  የሸዋ ዜና አገልግሎት ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ #join        https://t.me/+0j24gRc38Gg2OGVk
1.2K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 20:18:38
የቂሊንጦ መልዕክት

በአቶ ስንታየሁ ቸኮል ~~

በላይነህ ክንዴም በላይ ዘለቀ ያስፈልገናል።

የአማራ ማዕከላዊ መናገሻ ባሕር ዳር አይደለም። አዲስ አበባ ነው። ማንም ሰዉ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ወይም ደብረ ብርሃን መኖር ይችላል። የነገሥታቱ ባድማ፤ የአማራ አፅመ እርስት ያለዉ ግን እዚህ ነው። የአማራ ባለሃብቶች ብዙ አሉ። እሱ ብቻ በቂ አይደለም፤ በላይነህ ክንዴም በላይ ዘለቀም ያስፈልገናል። የሸዋ አማራ ወልቃይት አዲስ አበባ ነው።
ከአጀንዳችን ፊታችንን አናዞርም።

(ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )


ነፍጠኝነት መሬት ላይ መውረድ አለበት።
የአማራ ሕዝብ ታሪኩን በቁመቱ ለክቶ የሚመጥን ትግል ባለማድረጉ እና የዓላማ ፅናት ባላቸዉ ሰዎች የተገነባ መሪ በማጣቱ እራሱንም ሀገሩንም ዋጋ አስከፈሏል። ዳግማዊ ምኒልክ መወለድ አለበት። ለዚህ ተግታችሁ ስሩ ጊዜ የለንም ሀገር እንዳናጣ።

( የታሪክ ተመራማሪዉ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ) ህዳር 04/2015 ዓ.ም

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.6K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 18:41:01
ሸዋ ደራ ጉንዶ መስቀል  ከአድስ አበባ 220 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች!

ከህዳር 03 ቀን ጀምሮ በኦነግ ሸኔ ከበባ ውስጥ ናት።

አሸባሪ ሸኔ አምሰት የደራ ቦታ ላይ ሰፍሯል
1. ባቡ ድሬ
2. ሀርቡ
3. ራቾ አሙማ
4.ጁሩ ዳዳ
5. ሰለልኩላ ዙሪያ ቡርቃ የሚባል አካባቢ

በተለይ ጉንደ መስቀል ከተማ ውስጥ ገብተው ብዙ ሰው አግተዋል ሞተዋል። ከከበባ ለመውጣት እየተፋለመ ያለው ሚሊሻ ብቻ ነው ፤ እስካሁን በአካባቢው የመንግስት አካል የለም።

ትኩረት ለደራ  ሽዋ!
3.5K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 15:10:16 በትግራይ ክልል ለወያኔ ስልጠና ሲሰጡ ሲያስታጥቁና ከጎኑ ተሰልፈው ሲዋጉ የነበሩ የውጭ ሃይሎች እንዲሁም በሐገር ውስጥ ራሳቸውን የፌደራሊስት ሃይሎች ብለው እየጠሩ የትግራይ ክልልን ምሽግ አድርገው የቆዩ የታጠቁ ሃይሎች ከትግራይ ክልል ለቀው መውጣት ለአማራ ሕዝብ እንደትልቅ ድል እንዲቆጠር የሚያደርገው ጉዳይ ነው።
እነዚህ ፀረ-አማራ ሃይሎች ከትግራይ ክልል ለቀው የሚወጡ ከሆነም የአማራ ልዩሃይል በጥምር ጦሩ በትግራይ ክልል በሽሬ በአክሱም ወይም በአድዋ እንዲንቀሳቀስ የሚያስገድደው አንዳች የሕልውና ስጋት ስለማይኖርበት ለቀው ይወጣሉ።
የአማራ ልዩሃይል ወደትግራይ ክልል ማለትም ወደሽሬ ወይም ወደሌሎቹ አካባቢዎች ከዚህ በፊት ካለም የሕልውና አደጋ ስለነበረበት እንጅ በትግራይ ክልል ቆላ ደጋ ወይም ጋራ ሸንተረር የማቋረጥ ፍላጎት ስለነበረው አለመሆኑ እሙን ነው። ስለሆነም በትግራይ ክልል ያሉ የውጭ ሃይሎች እንደሚወጡ ሁሉ የአማራ ልዩሃይልም ካለ መውጣቱ የሚጠበቅ ነው።

በሕገ መንግስቱ መሰረት የተባለው እያሉ በወያኔ ትርጉም በአማራ ስም በተቆርቋሪነት ስም ተሰልፈው ወልቃይትንና ራያን ወደትግራይ ያካለሉ ወያኔዎችና አፍቃሬ ወያኔዎች ማወቅ ያለባቸው በሕገ መንግስቱ  ከዚህና ከዚያ ወዲያ ያለው የአማራ ወይም የትግሬ ክልል መሬት ወይም ወሰን ነው የሚል የተካለለ በሕገ መንግስቱ የተብራራ አንቀፅ አለመኖሩን ነው።ምኞቶች ግን ስለመኖራቸው ያለ ልክ የሚጮሁ አጀንዳዎቹ ብቻ በራሳቸው ይናገራሉ።

ለማንኛውም ለኢትዮጵያ ስጋት ለመሆን ትግራይ ክልልን በምሽግነት መርጦ የነበረ የውጭም ሆነ የውስጥ የጥፋት ሃይል  ከእንግዲህ እንደፈለገ ለጥፋት አላማ የመፈንጨት ዕድሉ ጠባብ እየሆነ መምጣቱን ነው።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.8K viewsedited  12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 12:33:09
#መረጃ
ከአሸባሪው ህወሃት ወደ ተደራዳሪዉ ህወሃት የተቀየረዉ ትህነግ አሁን ደግሞ ግራ የገባዉ ህወሃት ሆኖአል ።
ትላንት በትግርኛ ቋንቋ ባወጣው መግለጫው በደቡብ አፍሪካ ሆነ በኬንያ የተደረገው ስምምነት ህወሃትን አይወክልም
,አሁን ከኢትዮጵያ ሀይሎች ጋር እየተፋለመ ያለዉ ሰራዊት ህወሃት የመሰረተው አይደለም..በጭቁኑ ህዝባችን የተቋቋመ ህዝባዊ ሰራዊት ነዉ ሲል በመግለጫው አስፍሯል ።
በዚህም ህወሃት ለሁለት መከፈሉን እና ጀኔራል ዩሀንስ እና ምግበ ሀይሌ የነ ጌታቸዉ ረዳና ፃድቃን ገብረተንሳይ ተቃራኒ እንደቆሙ ተነግሯል ።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.3K viewsedited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 20:06:03
#Africa

" ዛሬ የተፈረመው ስምምነት የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን ይፈታሉ የሚለውን እሳቤ እንዲጸና ያደረገ ነው ። " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.4K viewsedited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 15:54:06
#መረጃ
FIB ቴሌቪዥን በድንገት ሰራተኞቹን በተነ
የፊንፊኔ ኢንተግሪቲድ ብሮድካስት(fib) ከተመሰረተ 3 አመታትን ቢያስቆጥርም አሁን ላይ ድርጅቱ ሰራተኞቹን በትኖ ከሀገር መዉጣቱ ተረጋግጧል ።
ከዚህ በፊት በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር እንደነበረዉ በድርጅቱ እና በሰራተኞቹ መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል ።
SNN

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.7K viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 22:43:32 በነገው ዕለት በዝርዝር ነጥቦች ላይ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል

: ማምሻውን ከኬንያ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፤ ላለፉት አምስት ቀናት በናይሮቢ በከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ሲካሄድ የነበረው ውይይት ነገ ፍፃሜውን ያገኛል።

ሁለቱ ወገኖች በነገው ዕለት ቅዳሜ ከቀኑ 5:00 ሰዓት ገደማ በዝርዝር የስምምነት ነጥቦች ላይ ፊርማ እንደሚያኖሩ ለማወቅ ተችሏል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.9K viewsedited  19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 19:41:57
አስደሳች ዜና!

ደፋሩ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በአንድ መቶ ሺ ብር ዋስ ከእስር ተፈታ። እንኳን ተፈታህ ጀግናው!


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.8K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 18:55:18
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ መሆናቸውን ገለጹ

በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።

በክልሉ 70 በመቶ በሚሆኑ አካባቢዎች ዕርዳታው ከመቼውም ጊዜ በላይ እየደረሰ የጠቆሙት ሚኒስትሩ ዕርዳታውን በሌሎች ቀሪ አካባቢዎች ለማዳረስ በ35 ተሽከርካሪዎች ምግብ እና በ3 ተሽከርካሪዎች መድኃኒት ተጭኖ ሽሬ ገብቷል ብለዋል።

አምባሳደር ሬድዋን በቲውተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ ወደ ክልሉ በረራ መፈቀዱንና የሰብአዊ ዕርዳታን በተመለከተ ምንም ዓይነት መሰናክል እንደማይፈጠር አመልክተዋል። አንዳንድ አካላት የአፍሪካዊያን ዕውቀት በፕሪቶሪያ ባመጣው ስኬት ደስተኛ እንዳልሆኑ ጠቁመው ይህንን መልካም መንፈስ ለማወክ ሲጥሩ ይታያሉ ሲሉም ገልጸዋል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.3K views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ