Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO ZENA (ኢትዮ ዜና)🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiozena24 — ETHIO ZENA (ኢትዮ ዜና)🇪🇹🇪🇹🇪🇹 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiozena24 — ETHIO ZENA (ኢትዮ ዜና)🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ethiozena24
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.26K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የሀገር ውሥጥ እና የውጭ ሀገር ዜናዎችን በፍጥነት ይደርስዎታል

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 23:22:53 በ4ቱም የአማራ ግዛት ላላችሁ ፋኖዎች!

ፋኖ ነኝ የምትሉ፣ በፋኖነት የሰለጠናችሁ በሙሉ ህዝባችሁን የምትታደጉበት ጊዜው አሁን ነው። ፋኖ ማለት ለሕዝብ የቆመ እስከሆነ ድረስ በጎጃም፣ በሸዋና በጎንደር የምትኖሩ ፋኖዎች ተነጋግራችሁ ወደ አስቸኳይ መፍትሔ መግባት ይኖርባችኋል። የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ የሚችሉትን እያደረጉ ናቸው። ለወንድሞቻችን የምንደርስበት ጊዜው አሁን ነው።

በዚህ ጊዜ ለዚህ መከረኛ ህዝብ ልትደርሱት ይገባል፤ ፊት እየመራችሁ ወጣቱን ከኋላ እያስከተላችሁ ይህን ወራሪ ልንመክተው ይገባል። ይህን የምታደርጉት ለብልፅግና ወይንም ለማንም አይደለም አምጦ ለወለዳችሁ ህዝብ ስትሉ ነው። አውቃለሁ በዚህ ሥርዓት ታስራችኋል፣ ተሳዳችኋል፣ ያላስማችሁ ስም ተሰጥቷል፣ ይህ ሁሉ ግፍ የደረሰባችሁ ለዐማራ ህዝብ ስትሉ በመሆኑ ልትኩሩ ይገባል እንጂ "ብልፅግና በደል አድርሶብናልና አንዋጋም" ብላችሁ ህዝባችሁ ለዳግም ባርነትና ስደት ሲዳረግ በዝምታ ማዬት የለባችሁም።

እያያችሁ፥ እየሰማችሁ ነው እንቆምለታለን፣ እንሞትለታለን የምትሉት ህዝብ ዳግም በህወሓት ቅኝ ግዛት ሥር እየወደቀ ይገኛል። ይህን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዜና ሰምታችሁ ያስችላችኋል ብዬም አላስብም። ህዝባችሁ በማንም ወራሪ ሲዋረድ፣ ሲታረድ፣ ሲፈናቀልና ሲደፈር ቆሜ አላየም አሻፈረኝ ብላችሁ ተነሱ። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ ያልተከፋ አልነበረም፥ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ግን "የተቀያየምነው ከሥርዓቱ እንጂ ከህዝቡ ጋር አይደለም" በማለት 'ኧረ ጥራኝ ጫካው' እያሉ አርበኝነትን፤ ፋኖነትን በይፋ ጀምረው ህዝባቸውን ነፃ አውጥተውታል።

እናተም የአባቶቻችሁን ገድል ድገሙት። እለምናችኋለሁ ፊት ሁናችሁ ምሩን እኛ እንከተላችኋለን። የሚያስፈልገውን ሎጂስቲክ እናቀርባለን። ከዚህ በኋላ ከብልፅግና መፍትሔ መጠበቅ ቂልነት ነው። ዛሬ ቆቦ፣ ነገ ወልድያ፣ ከዛ ሐይቅና ደሴ ተያዙ የሚል ዜና መስማት የሞት ሞት ነው።

( ታደለ ጥበቡ )
896 views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, edited  20:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 07:49:33 “ አማራን የማንገላታት፣ የማሳቀቅ፣ ከከተማው የማራቅ እና አለፍ ሲልም የማገት ፓለቲካ በአስቸኳይ መቆም አለበት” ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙ መንገደኞች ላይ ባለፉት ጥቂት ቀናት የተፈጠረው የሰላማዊ መንገደኞችን ጉዞ ማስተጓጎል፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከል፣ በሰበብ አስባቡ አማራውን ማንገላታት እና ማገት ወዘተ ... የተጓዦችን በነፃነት የመንቀሳቀስ እና በፈለጉት የአገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሶ ሰርቶ የመኖር መሰረታዊ ሰብዓዊ መብትን የሚገድብ ግልጽ የሆነ የህግና ተደራራቢ የመብቶች ጥሰት ነው።

ድርጊቱ «ወንጀለኞች ወደ ከተማይቱ ሰርገው ገብተው ጥቃት እንዳይፈጽሙ ለመከላከል የሚደረግ ቅድመ ጥንቃቄ ርምጃ ነው» በሚል ሰበብ አማራን የማንገላታት፣ የማሳቀቅ፣ ከከተማው የማራቅ እና አለፍ ሲልም የማገት ፓለቲካ ሲሆን፣ ይሄንን እገታ በማን አለብኝነት የሚፈጽሙት አካላት ከዚህ ሀላፊነት የጎደለው የእብደት ድርጊታቸው ባስቸኳይ ሀይ ካልተባሉ ውሎ አድሮ የከፋ ችግር መፈጠሩ አይቀርም።

ይህ እብደት ዛሬ፣ ነገ ሳይባል በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል። ይሄንን የአገርን ሰላም ለማደፍረስ ታስቦበት በሚመስል መንገድ እየተሰራ ያለ ህገወጥ የወንጀል ድርጊት ምንም አይነት አመክንዮ እና የህግ መሰረት የሌለው፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምጽ ሊያወግዘው የሚገባ ተግባር ነው።

ድርጊቱን በአስቸኳይ ማስቆም ያለበት በዋነኝነት የፌደራል መንግስቱ ሲሆን፣ በፌደራል መንግስቱ ውስጥ በአማራ ስም ስልጣን ይዛችሁ ያላችሁ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ድኤታዎች፣ በተለይም ም/ጠ/ሚ/ሩ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ ሚ/ሯና ሌሎች ሚኒስትሮች ሀላፊነታችሁን በአግባቡ ባለመወጣታችሁ በህግ ተጠያቂ ባትሆኑ እንኳን በታሪክ ተጠያቂነት እንዳለባችሁ ልናሳስባችሁ ግዴታ አለብን። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ም/ር/ መስተዳድሮች፣ የካቢኔ አባላት እና የዞን አስተዳዳሪዎች እና የአዲስ አበባ ካቢኔ አባላትም በተመሳሳይ።

የችግሩ ግዝፈት አንገታችሁን እንደሰጎን አሸዋ ውስጥ ቀብራችሁ፣ አላየንም አልሰማንም ብላችሁ ልታልፉት አትችሉም። ይሄንን የለየለት አገር አፍራሽ ድርጊት ከማስቆም በተጨማሪ በይፋ ወጥታችሁ ማውገዝና ተጠያቂ የሆኑ የኦሮሞ ክልል ባለስልጣናት ተጠያቂ እንዲደረጉ በይፋ መጠየቅ አለባችሁ። መቼም ይህን ጉዳይ እንደቀላል ነገር ትቆጥሩታላችሁ ብየ በግሌ አልጠብቅም። አገርን ወደ አለመረጋጋት ሊመራ የሚችል ከባድ ጉዳይ እንደሆነ ፈጽሞ አትስቱትም።

የአማራ ሕዝብ ለእገታ ፓለቲካ አራማጅ ሃይሎች ፈጽሞ አይንበረከክም። አማራን በዋና ከተማው አዲስ አበባ ሙሉ የባለቤት መብት፣ ሰርቶ ከመኖር፣ ለንግድ ለስራ፣ ለህክምና፣ ለማንኛውም ማህበረ ኢኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች በፈለገው ጊዜ ከመውጣት እና ከመግባት የሚከለክለው አንዳችም ሀይል እንደሌለም ሊሰመርበት ይገባል።

https://t.me/ETHIOZENA24
2.2K views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, edited  04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 10:35:04 #መረጃ - አዲስ አበባ!

አዲስ አበባ ፈረንሳይ ብረት ድልድይ አካባቢ አካኮ በሚባል ሰፈር የኦረሞ ወጣት ብቻ እንዲገኝ በተደረገው የድብቅ ስብሰባ የብረት ድልድይ ጊወርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያሳጠረውን የመድሀኒአለምን ፀበል የነፍጠኛ እምነት ነው አፍርሱት በማለት አፍርሰዋል ሲሉ የአካባቢው መረጃ ሰጭወቻችን ገልፀዋል።

በድብቁ ስብሰባው የተነሱ ነጥቦችም
*የአፄዎቹ አገዛዝ የኦረሞን ህዝብ ጨፍጭፏል፤ ገድሏል ባሪያ አድርገው ገዝተውናል ከዚህ በኋላ አማራ የተባለ እናጠፋለን። *አዲስ አበባ ውስጥ አማራ ለተባለ መሬት እንዳትሸጡለት፤ ቤት እንዳታከራዩ፤ ያከራያችሁ አስወጡ በሚሄዱበት ይሂዱ።
*አንድ ኦረሞ አንድን አማራ መከታተል አለበት
*ለሁሉም ኦረሞ ተወላጅ ትጥቅ እናስታጥቃለን የሚሉና ሌሎችም ነጥቦች በስብሰባው ሲንፀባረቁ እንደነበር የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል። በመጨረሻም ቀጣይ ስብሰባ እንደሚኖራቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ስብሰባቸውም መላው የኦረሞ ተወላጅ የሆነ የመንግስት ባለስልጣን ይገኝበታል እንዳትቀሩ በማለት ለነሀሴ 03/12/2014 በአሽዋ ሜዳ ቀጠሮ ይዘዋል። የአዲስ አበባ ህዝብ ይወቀውና ቀጣይ ህልውናውን ያስከብር ሲሉ መረጃ ሰጭወቻችን መልክታቸውን አክለው ገልፀዋል። በብረት ድልድይ የኦረሞ ተወላጅ ናቸው ተብለው እንደ ዋና አስተባባሪ የተመረጡትን ስም ዝርዝር መረጃ እያጣራን ነው እንዳገኘን የምናካፍላችሁ ይሆናል።

ንሥር ብሮድካስ
3.0K views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, edited  07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 17:12:11
"እንደ አሁኑ አይነት ዘረኝነት አላየሁም። ከሀገሬና ከተቋሜ በማንነቴ ምክንያት ተሰድጃለሁ" ጋዜጠኛ እማዋይሽ ግርማ

ሁሉ ነገር ተጨመላልቋል። አይን ያፈጠጠ ዘረኝነት ነው ያለው። እኔ በሁለቱም ሰርዓት ሰርቻለሁ። እንደ አሁኑ አይነት ዘረኝነት ግን አላየሁም። በአጠቃላይ ETV የሀገሪቱን ምስቅልቅል ፖለቲካ ይመስላል።

በግሌ ለ10 አመት ከሰራሁበት ETV በማንነቴ ተገፍቻለሁ። ሌሎችም በማንነታቸው ተገፍተዋል። ችሎታ ሳይሆን ማንነት ተቆጥሮ የማይመጥነን ቦታ ተመድበናል። ሀላፊዎቻችን ETV ን እየመሩ የማህበራዊ ሚዲያ ኘሮፋይላቸው ግን የOBN ጋዜጠኛ ነው የሚለው።

ፈጣሪ ካልታከለበት የሚመጣ ለውጥ ያለ አይመስለኝም። ነገሮች እየተወሳሰቡ ሄደዋል። በሀገሬ ተስፋ ቆርጫለሁ። በተቋሜ ተስፋ ቆርጫለሁ። በዚህም ለስልጠና በሄድኩበት ሀገረ ኔዘርላድ ጥገኝነት ጠይቄ ቀረቻለሁ። ከሀገሬና ከተቋሜ በማንነቴ ተሰድጃለሁ።

እማዋይሽ ግርማ - የETV ጋዜጠኛ የነበረች
3.3K views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, edited  14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:00:02 ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

አማራነት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አለ የተባለ ግድያ ጭፍጨፋ እና በአጠቃላይ ዘር ማጥፋት በአማራ ህዝብ ላይ ተፈፅሟል። እየተፈጸመም ይገኛል።

ይህ ድርጊት የተቀነባበረ ታሪካዊ የሀገራችን ጥላቶች ጋር ትስስር ያለው አማራ አንደ አማራ መኖር ቀርቶ አማርኛ ተናጋሪ እንዳይኖር በማይፈልጉ እንደ ኦነግ እና የትግራይ ወራሪ ሀይል ጥምር ሃይሎች የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እየተፈጸመበት ይገኛል።

አስተዋይነቱ የበዛው ህዝባችን በሁሉም አካባቢ የአብርሃም በግ ሁኖ ሲታረድ ተው ይህ መጠፋፋት ሀገርን እንደ ሃገር አያቆምም በሚል እሳቤ ትዕግስቱ እንደ ባህር ጥልቅ መሆኑ በጥላት በኩል አንድም በፍረሃት አሊያም አቅመቢስነት ሲያልፍም ጅላጅል ቂልነት እና ግዑዝ አካል አድርገው ቆጥረዉታል።

በሁሉም ያልፋል እሳቤ ከዚህ በላይ መታገስ እንደ ኩርድ ሀገር አልባ እንደ አሜሪካ ኢንዲያን ዘራችን እንዲጠፋ መተባበር መሆኑን ሁሉም ህዝባችን ሊያውቀው የሚገባ የፀሃይ እውነት ነው።

እጅግ አሳሳቢው ነገር አማራን የማጥፋት ህልማቸውን ለማሳካት የታቀደ የተቀነባበረ በመሪዎች የሚመራ ድርጊቱ እጅግ የከፋ መዋቅራዊ ሰንሰለት ያለው በቅብብሎሽ የሚፈፀም መሆኑ ነው።

የወለጋው መዋቅር መራሽ ጭፍጨፋ ሀዘናችን ሳይወጣ በየቀኑ የአማራ ደም ካልፈሰሰ የደም ስካራቸው የማይበርድ የዘመኑ ፊት አውራሪዎች እሳቱን ስበው ቀያችን ድረስ በማምጣት በአጣየ እና አካባቢው ለኩሰውታል። በዚህ ድርጊታቸውም ደራሽ አልባው ህዝባችን እየተቃጠለ ይገኛል።

በተለይ ከሰሞኑ በአጣየ እና አካባቢው ህዝብ ብሎም በአማራ ልዩ ሀይል ላይ የተፈፀመው ድርጊት አማራው ላይ የታወጀው የዘር ማጥፋት እንደሆነ ትልቅ ማሳያ ነው።

ይባስ ብሎ የውስጥ የፖለቲካ ብሶቱን አማራን የማጥፋት ፓሊሲውን ለመፈፀም ከዚህ ቀደም እሰከ ሰሜን ሸዋ ድረስ ወረራ የፈጸመው የትግራይ ወራሪ ሃይል መግስት ያቀረበለትን የሰላም የመደራደሪያ ሀሳብ ውድቅ በማድረግ ለዳግም ወረራ ተዘጋጅቶ የትግራይን መሬት አስመልሳለሁ በሚል አባዜ ወረራ ለመፈፀም ተዘጋጅቻለሁ የሚል መግለጫ ጋጋታ በቡችላው ጌታቸው ረዳ በኩል መተንፈስ ጀምረዋል።

ከዚህ አንፃር ፦
1.መላው ህዝባችን ለአይቀሬው የህልዉና ትግል እራሱን አንዲያዘጋጅ እና ራያ ግንባር እንዲከት!

2. በሁሉም አካባቢ ያለ የታጠቀ ያልታጠቀ ህዝባችን እንደ ህዝብ ተደራጅቶ ትግሉን በመቀላቀል እኛ ተሰዉተን ቀሪው ህዝባችን ፍትህ እኩልነትና ነጻነት ሰፍኖለት በሰላም የሚኖርበትን አውድ መፍጠር ይኖርብናል!

3.የፊት ተዋጊ ግንባር ሲገባ የኋላ ደጀን ሀይላችን ትጥቅና ስንቅ በማቀበል እንዲያግዝ ባለው አደረጃጀት እንዲጠባበቅ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን።

በመጨረሻም በህግ ማስከበር ስም አማራዉን እርስ በርሱ ለማጋጨት እና ያለዉን አንድነቱን ጭምር ለማሳጣት ብሎም የከፋ ማህበራዊ ቀዉስ ዉስጥ እንዲገባ ታስቦ እየተሰራ መሆኑን ሁሉም የአማራ ህዝብ የጸጥታ አደረጃጀቶች የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ህዝባችንን ደጀን አድርገን የጋራ ጠላቶቻችንን በጋራ እንድንታገል ስንል በአማራ ህዝብ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

" ፋኖነት ለኢትዮጵያዊነት ህያው ምስክር ነው።"
2.9K views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:36:32 ይድረስ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት!
*
ሶርያውያን፣የመናውያን፣ደቡብ ሱዳናውያን፣ ኮንጓውያን እና ሌሎችም የሥራ ሁኔታ ተመቻችቶላቸው ጭምር በሰላም በሚኖሩባት ኢትዮጵያ፥ አማሮች በራሳቸው አገርና ምድር ዓይናችሁን ለአፈር እየተባሉ በጅምላ ይጨፈጨፋሉ። መነሻ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን፤ ይኼ ጉዳይ የአገር አንድነት እና ብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ሆኖ በሁሉም ዘንድ እኩል ሊወገዝ ይገባው ነበር። በአገር ደረጃ ብሔራዊ የኃዘን ቀን እንዲታወጅ እና በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ የጋራችን ኃዘን እንዲሆን ደጋግመን ብንወተውትም ጉዳዩን ጉዳዬ ያለው አልተገኘም።

በዚህ ጉዳይ ዝም ብንል እንኳንስና ሰው፥ እግዚአብሔርም ይቅር አይለንም። ዝምታ ግፍና ግፈኞችን መተባበር ይሆናል። የሚመለከታችሁ አካላት ከመቅረት መርፈድ ይሻላልና ለራሳችሁ ስትሉ ኃዘናችንን በጋራ የምናደርግበትን ብሔራዊ ቀን አውጁልን። እንዴት የክብር ሞት እንነፈግ? እንዴት የክብር አፈር እንነፈግ?

(ለአገር አንድነት ስንል…ለመንግስታዊ ወግና ባሕሉም ስንል…ነው እንጂ ከልክ በላይ መታገሳችን፤ የወገኖቻችን ጅምላ ጭፍጨፋ ሳያሳዝነንና ሳይቆጨን ቀርቶ አይደለም! )
2.3K views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, 05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:58:28
የአዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ፤ ኃላፊነታቸውን ለቀቁ!

የብልፅግና ተመራጭ እና የአዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ዕጩ ዶክተር ዮናስ ዘውዴ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ከታማኝ ምንጭ አረጋግጫለሁ።

የመረጃ ምንጬ የለቀቁበትን ምክንያት ሲያብራሩ አገዛዙ በሙስና የተዘፈቀ እና ለአገሪቱ መጻኢ ተስፋ የማያስብ በመሆኑ ከዚህ ሥርዓት ጋር ለመቀጠል ስለከበዳቸው መልቀቃቸውን ገልጸውልኛል።

( ምንጭ Mulugeta Anberber )

https://t.me/ETHIOZENA24
1.8K views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, edited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 18:53:09
" እዚሁ ሰላሌ ውስጥ 52 ቀበሌዎች 100 ሺህ እና 50 ሺህ ብር ለኦነግ ሸኔ ግብር ከፍለዋል።" - አቶ ውብሸት ታዬ

ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ውስጥ ያያ ጉለሌ የሚባል አካባቢ ከ150 አመት በላይ የኖሩ 10 ሺህ የሚሆኑ አማሮች ለቅቃችሁ ውጡ ተብለው ነቅለው ወጥተዋል። የሚሄዱበት ሀገር ስለሌላቸው ወደ ልመና ጭምር ገብተዋል። የሚጠብቃቸው አካል ስለሌለ ነው።

በሰላሌ አካባቢ አማሮች ነቅለው እንዲወጡ ሲደረግ፣ ኦሮምዎች ደግሞ ግብር እንዲከፍሉ ሆኗል። ሰላሌ ውስጥ ሀብት ያላቸው ሰዎች ለኦነግ ሸኔ ግብር ከፍለዋል። 100 ሺህ እና 50 ሺህ ብር ግብር ከፍለዋል፣ ኦነግ ሸኔም ማህተም ያለበት ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል። ኦነግ ሸኔ ሰላሌ ውስጥ ከ52 ቀበሌ በላይ ግብር አስከፍሏል።

ወለጋ ብቻ አይደለም አማራ የሚገደለው። እዚሁ ሰሜን ሸዋ ጭምር እንጂ። ይሄ ሁሉ ሲሆን መንግስት እርምጃ አልወሰደም። አንዳንዴ እየተጠቃቀሱ የሚሰሩ ይመስለኛል።

(አቶ ውብሸት ታዬ - ለBlue24 የተናገረው)
1.7K views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, edited  15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 22:48:03 በሰሜን ሸዋ አጣዬ አካባቢ በአማራ ልዩ ኃይል ላይ የደረሰዉን ገዳት አስመልክቶ ከአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ህዝብ መከታ መሆኑን በተደጋጋሚ በተግባር ያረጋገጠዉ የአማራ ልዩ ኃይል ባልተሟላ ሎጅስቲክስ እና አመራር ውስጥ ሆኖ የአማራን ህዝብ ከጥ*ፋት ለመታደግ መ*ራር መስዋዕትነት በመክፈል ላይ መሆኑ ይታወቃል።

ሐምሌ 03 እና 04 ቀን 2014 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተውን ጥ*ቃት በመከላከል ላይ እያሉ በተቀነባበረ ሴ*ራ ምክንያት ቁጥራቸው በርከት ያለ የልዩ ኃይል አባላት ተሰ*ውተዋል። በርካቶችም ከባድ እና ቀላል ጉ*ዳት ደርሶባቸዋል። የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በክልሉ ውስጥ በተደራጀ ታ*ጣቂ አማካኝነት በአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ በደረሰው ጉዳት መሪር ሀዘን የተሰማው መሆኑን ይገልፃል።

መላው የልዩ ኃይላችን አመራር እና አባላት ውድ ህይወታችሁን የምትሰጡለት የአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነበትን የህልዉና አ*ደጋ ለመቀልበስ የምታደርጉትን ተጋድሎ እያደነቅን የአማራ ብልፅግና የሚባለውን ድርጅት ተጠቅመው ሊያ*ጠፋፉን የሚፈልጉ ዋነኞቹ ጠላ*ቶቻችን እናንተን ከፋኖ ወንድሞቻችሁ ጋር በማጋጨት የአማራዉን ኃይል በመ*በተን ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉትን ጥረት እንድትረዱ እና ከቆማችሁለት ዓላማ ውጭ ስምሪት የሚሰጣችሁን የፖለቲካ አመራር በቃ*ህ እንድትሉት፤ ባልተሟላ የመረጃ፣ የአመራር እና የሎጅስቲክስ አቅርቦት ለአደጋ እያጋለጣችሁ ያለዉን የፖለቲካ አመራር ልዩ ኃይሉን ለከፋ አደ*ጋ ከሚያጋልጥ ስዉር ሴ*ራው እንዲታቀብ ወታደራዊ አካሄዱ በሚፈቅደው አሰራር መሰረት በየአደረጃጀታችሁ እንድትታገሉት ጥሪ እናስተላልፋለን።

በአካባቢው ያላችሁ የአማራ ፋኖ አባላት ልዩ ኃይሉ ላይ ከሆነውም የከፋ ጉ*ዳት እንዳይደርስ ላደረጋችሁት ተጋድሎ ከፍተኛ አድናቆት ያለን መሆኑን እየገለፅን ሁሉም የፋኖ አመራር እና አባላት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ጥበብ እና ብስለት የተሞላበትን አካሄድ በመከተል ከልዩ ኃይላችን ጋር ስምሪት ጋር ተያይዞ ጠላ*ቶቻችን የሸረቡልንን የመጠ*ፋፋት ሴ*ራ እንድና*ከሽፍ ጥሪ እናቀርባለን።

በመጨረሻም መስዋዕትነት ለከፈሉ የልዩ ኃይላችን ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ)
ሐምሌ 05 ቀን 2014 ዓ.ም
ባሕርዳር-ኢትዮጵያ
1.6K views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, edited  19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:48:33 # "መላ ሀገሪቱን ያቀጣጠለ ማዕበል እንፈጥራለን" የዩኒቨርስቲ መምህራን ማስጠንቀቂያ!!
/
በአርባ አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ መምህራን ከደሞዝ ጭማሪ፣ ከቤት ኪራይ አበል እና ከደረጃ እድገት ጋር በተያያዘ ለረጅም ወራት ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ ባለማግኘታቸው፣ እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጥያቄዎቻቸው ተግባራዊ ምላሽ የማያገኙ ከሆነ፤ ከነሐሴ 5 ጀምሮ ተማሪዎችንም ባካተተ መልኩ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እና አድማ እንደሚያደርጉ አሳስበዋል።

"መላ ሀገሪቱን ያቀጣጠለ ሀገራዊ ማዕበል እንፈጥራለን" ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ከዚህ ቀደም ሊደረግ የነበረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ "አሁን ካለው የሀገሪቱ ሁኔታ አኳያ መንግሥትን ችግር ውስጥ ይከተዋል" በሚል በመምህራን ማሕበር ሸምጋይነት ተራዝሞ ቆይቷል።

በሂደት እንደታየው ግን፣ ማህበሩ ከአገዛዙ ጋር በመወገኑ፣ ለመምህራኑ ጥያቄ ትኩረት አለመስጠቱን መምህራኑ ተናግረዋል። መምህራኑ ደምወዝ እንዲጨምርላቸው፣ የማዕረግና የደረጃ ዕድገት አሰጣጡ ፍትሐዊ እንዲሆን፣ የቤት ኪራይ አበል እንዲሰጣቸውና የሚሰጣቸው አበልም የወቅቱን የኪራይ ሁኔታ ያገናዘበ እንዲሆን ትምህርት ሚንስቴርን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ ተቋማትን ሲጠይቁ ቆይተዋል።

በቢሮ ደረጃ ሲቀርብ የነበረውን ጥያቄ ወደ አደባባይ በማምጣትም የማሕበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎችን ሊጀምሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ
/
#ኢትዮጵያ

https://t.me/ETHIOZENA24
1.5K views🅝🅔🅖🅡🅞 🅜🅐🅝, edited  14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ