Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja — ETHIO-MEREJA®
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 132.47K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-17 22:42:46
#ጤናመረጃ

ቲማቲም ለፊት ጥራት ያለው አስደናቂ ጥቅም!!

ቲማቲም ለቆዳችን እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡ ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው ቤታካሮቲን፣ ላይኮፔን እና ፍላቮኖይድስን አለው፤ ይህን ንጥረ ነገር ደግሞ ለፊት ጥራት ተብለው በውድ ዋጋ የሚሸጡ መዋቢያዎች ይጠቀሙበታል፡፡

በቀላሉ የምናገኘው ቲማቲምን በመጠቀም ቡጉርን፣ የቆዳ ጥቁረትንና ጥቁር ነጠብጣቦችን ከፊታችን ላይ ለማጥፋት ይረዳናል፣ በተጨማሪም ቲማቲም የቆዳን እርጅና እና መሸብሸብ ፍጥነትን የመቀነስ ችሎታ አለው፡፡

ለማዘጋጀት አስፈላጊ ነገሮች -

- 1 ቲማቲም
- 2 የሻይ ማንኪያ ስኳር
- 2 የሻይ ማንኪያ ማር
- 1 መለስተኛ የቡና ሲኒ >>

አዘገጃጀት

1) በመጀመርያ የፊታችን የቆዳችን ቀዳዳዎች መከፋፈት ስላለባቸው ፊታችንን በሙቅ ውሀ እንፋሎት መታጠን፡፡

2) ቲማቲሙን ይቆርጡና በሲኒ ላይ ይጨምቁታል፡፡
3) ጭማቂው ላይ ቅድሚያ ስኳሩን ቀጥሎ ማሩን ይጨምሩና ያዋህዱታል፡፡

4) ውህዱን ፊትዎ ላይ በስሱ ይቀቡታል ፡፡
5) ለ 2 ደቂቃ በዝግታ ያሹታል፡፡
6) ለተጨማሪ 2 ደቂቃ ደግሞ ባለበት ይተውታል፡፡

7) ባጠቃላይ ከ 4 ደቂቃ በኋላ በ ቀዝቃዛ ውሀ ይታጠቡታል፡፡ ማስጠንቀቂያ:- ለቲማቲም ሆነ ከላይ ለተጠቀሱት ውህዶች አለርጂክ ከሆኑ እንዲጠቀሙት አይመከርም፡፡ 
......
በተጨማሪም ቲማቲም ለቆዳ ጤንነት ያለውን ጥቅም በቀላሉ ሞክሮ ማየት ካስፈለገ የሚከተለውን ማድረግ ይቻላል።

ከ8 እስከ 12 የሚሆኑ ቲማቲሞችን ልጦ የልጣጩን የውስጠኛ ክፍል ፊት ላይ መለጠፍ፡፡ ቢያንስ ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ልጣጮቹን አንስቶ ፊትን መታጠብ፡፡ ከዛም ይህንን በተደጋጋሚ በማድረግ ለውጡን ማስተዋል እንችላለን።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
14.5K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 21:55:54
አረብ ኤምሬትስ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ ዝናብ ማስተናገዷ ተገለጸ።

የዝናብ መጠን መመዝገብ ከጀመረበት 1949 ወዲህ ከፍተኛ ነው የተባለው ዝናብ በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ጎርፍ አስከትሏል።የኤምሬትስ ብሄራዊ የሜትዮሮሎጂ ማዕከል በትናንትናው እለት ለ24 ስአታት የተመዘገበው የዝናብ መጠን ኤምሬትስ ከተመሰረተችበት 1971ም ሆነ በአካባቢው የዝናብ መጠን መመዝገብ ከጀመረበት 1949 ወዲህ ከፍተኛው ነው።

ማዕከሉ ከፍተኛው የዝናብ መጠን (254 ሚሊሜትር) በአል አይን “ካትም አል ሻክላ” በተባለው አካባቢ መመዝገቡን ገልጿል።የሜትዮሮሎጂ ተቋሙ ዝናቡ የኤምሬትስን የገጸምድር ውሃ ክምችት እንደሚያሳድገው መጠቆሙንም ዋም የዜና ወኪል ዘግቧል።

ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ጎርፍ ያስከተለ ሲሆን፥ በአለማችን ስራ ከሚበዛባቸው አውሮፕላን ማረፊያዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የዱባይ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉ ነው የተገለጸው።

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja
14.3K viewsedited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 14:59:49
Slook.AI - የእርስዎ የግል ስቲስት በስልክዎ ላይ!

በልብስህ የፈለከውን ሁሉ ያደርጋል!
ለውጥ፣ ንፁህ፣ አሻሽል!

ይህ ልብስ ለእርስዎ የሚስማማ መሆኑን ያረጋግጡ!
የሚያውቋቸው ሰዎች በተለየ መልክ እንዴት እንደሚመስሉ ይመልከቱ።

በ2 እርምጃ ከ15 ሰከንድ በኋላ የሚፈለገውን ውጤት ታገኛለህ፡-

ፎቶህን ስቀል።
የእርምጃውን አይነት በራስዎ ወይም ከተጠቆሙት አማራጮች ይምረጡ።
ሁለት ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምስሎች ያግኙ።

ቀጥል እና Slook.AI ን ለራስህ ሞክር፣ የፈለከውን ነገር በልብስህ አድርግ"
16.9K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 10:20:50
ቪዲዮ:- አየር ላይ ሊሰራ የታሰበው ተንጠልጣዩ ሕንፃ!

ህንፃው ከኅዋ ወደ ምድር ይገነባል የተባለ ሲሆን የበርካታ አስደናቂ ህንፃዎች ባለቤት በሆነችው ዱባይ እንደሚገነባም ተነግሯል።

ቁመቱም 32000ሜትር ይሆናል የተባለለት ይህ ህንፃ በክላውድስ አርትቴክትስ ንድፉ እንደወጣለትም ተገልጿል።

ከህዋ ላይ የህንፃው መሰረት እንደሚሰራ የተነገረለት ይህ ህንፃ ከአስትሮይድ ጋር እጅግ ጠንካራ ከሆነ ኬብል ጋር በማያያዝ ቁልቁል ወደ መሬት ይወርዳል ተብሏል።

የሀይል ምንጩንም ህዋን መሰረት ያደረገ የሶላር ሲስተም ጋር እንደሚያገኝ የተነገረ ሲሆን ዉሀ ደግሞ ከዳመና ላይ በመሰብሰብ ይጠቀማል።በህንፃ ላይ ሰዎች እንዴት መውጣት እንደሚቻል ግልፅ ባያደርጉም፣ ከህንፃው መውረድ የፈለገ ሰው ግን ፓራሹት ይጠቀማል ተብሏል። የዚህ ህንፃ እውን መሆን ግን ብዙዎችን አጠራጥሯል።(ምንጭ፣ሀገሬ ቲቪ)

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja
17.6K views07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 09:45:18
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተወሰደው ገንዘብ 95 በመቶ ማስመለሱን ገለጸ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ከተወሰደበት ገንዘብ ውስጥ ከ762 ሚሊየን ብር በላይ ማስመለሱን አስታውቋል፡፡

ከሲስተም ጋር በተገናኘ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊየን 417 ሺህ 747ብር ከ81 ሳንቲም ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር ተገልጿል፡፡ከዚህም ገንዘብ ላይ 762 ሚሊየን 941ሺህ 341 ብር ማስመለስ ተችሏልም ብሏል፡፡

ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ነውም ብሏል ባንኩ፡፡ቀሪውን 5 በመቶ ወይም 38 ሚሊየን 474 ሺህ 938 ብር ተመላሽ ካላደረጉ ግለሰቦች የማስመለስ ሥራው እንደሚቀጥልም ነው ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀው፡፡

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja
16.8K viewsedited  06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 09:13:49 «ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ህወሓት ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል» ሲል የአማራ ክልል መግለጫ ሰጠ!!

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ!

ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ከጦርነት ውጭ ማሰብ የማይችለው የህወሓት ቡድን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ በእርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ በጊዜያዊ አሥተዳደሩ ካቢኔ አማካኝነት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ይህን የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት የሆነውን የህወሓት ቡድን ባለፉት ሦስት ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ  የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈፀም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈፀመባቸው አካባቢዎች  ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች ስቃይ በተሞላበት ችግር ውስጥም ሆነው በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መሆኑ በበርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች የተረጋገጥ ጉዳይ ነው፡፡

ተቸንካሪነት ዋና መለያ የሆነው የህወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን አሰቃቂና ታሪክ ምንጊዜም የማይዘነጋው የባንዳነት ተግባር ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያዊያን እና በጀግኖች የፀጥታ ኀይሎች አማካኝነት የሽንፈት ፅዋን ከመጎንጨቱ ባሻገር የማንነትና የራስ አሥተዳደር ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት ችለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ ያልተመቸው ተቸንካሪው የህወሓት ቡድን በሦስት ዙሮች ከተደረገው ጦርነት ማግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡አሁንም እየፈጸመ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የአማራ ክልል መንግሥት ይህን መሰሉን የህወሓትና የግብረ አበሮቹን ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማክበር በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ እየጠየቅን ይህ የማይሆን ከሆነ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል የምንገደድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የተከበራችሁ በክልላችን በየደረጃው ያላችሁ የፖለቲካና የጸጥታ መዋቅር አባላት፡- ከሰሜን ዕዝ ጥቃት በኋላ ትህነግ በቀሰቀሰው ጦርነት ሕዝባችን ቀጥተኛ ተጠቂ በመሆኑ ምክንያት ለበርካታ ችግሮች ተዳርጎ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በየደረጃው የሚገኙ የመዋቅር አባላት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ጥምር የጸጥታ ኃይሎችና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሀገር አፍራሽ የጥፋት ኀይሉ ላይ የተቀዳጀው ድል ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ ዛሬም እንደ ትናንንቱ በፅናትና በቁርጠኝነት ሕዝቡን በማደራጀት አካባቢያችሁን በመጠበቅ ታሪካዊ ኀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የተከበርከው የክልላችን ሕዝብ፡- በተደጋጋሚ ጥቃት የፈፀመብህ የጥፋት ኀይል ዛሬም እንደ ትናንቱ ወረራ ፈፅሟል፡፡ በመሆኑም መላ የክልላችን ሕዝብ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ሠርጎ ገቦች ራስህን በመጠበቅ ከክልል መንግሥትና በየአካባቢው ከሚገኙ አሥተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቻችን የከፈቱብንን ጥቃት ለመመከት  በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የድርሻህን እንድትወጣ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት፡- የፌደራል መንግሥት ህወሓት የቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ ማድረጉን ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተደረገውን ጥረት በሙሉ ልብ በመደገፍ ለውጤታማነቱ የድርሻችንን ስንወጣ ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን ህወሓት በተደጋጋሚ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሲያፈርስ ቆይቷል፡፡ አሁንም በሙሉ አቅሙ ወደ ጦርነት ገብቷል፡፡ ይህን እኩይ ድርጊቱን የአፍሪካ ሕብረትና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በቦታው ተገኝተው አረጋግጠዋል፡፡በመሆኑም ይህን እብሪተኛ ቡድን በአጭር ጊዜ ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ሕዝባችንን ከጥፋት መታደግና የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ይገባል፡፡

ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ
ህወሓት ከምስረታዉ ጀምሮ ለአማራ ሕዝብ ባለው ሥር የሰደደ ጥላቻ  ምክንያት በአማራ ሕዝብና በመላ ሀገሪቱ ሕዝብ ላይ የማያባራ ደም አፋሳሽ ጦርነትን ሲቀሰቅስ ኖሯል፡፡ ለዚህም ነው ህወሓት የኢትዮጵያም ሆነ የአፍሪካ ቀንድ አለመረጋት ምንጭ ነው የምንለው፡፡

ሆኖም በአሳሳች የፕሮፖጋንዳ ሥራዎቹ ምክንያት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ በህወሓት ጉዳይ ላይ የተሳሳተ አቋም ሲይዝ ተስተውሏል፡፡ ዛሬ ግን ለዚህ አሳሳች ፕሮፖጋንዳው ያልተመቼ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በጠራራ ጸሐይ የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ወቅት ወረራ መፈጸሙ በገሃድ ታይቷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ ቀደም እንዳደረገው በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ማወናበድ አይችልም፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ህወሓት የፈጸመብንን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝና ከጎናችን እንዲቆም የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ሚያዚያ 08 /2016 ዓ‹ም / ባሕር ዳር

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja
16.5K viewsedited  06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 23:15:45 አዲስ አበባ እና አቅራቢያ ለምትገኙ በሙሉ!!

የOnline እቃዎችን በብዛት ዋጋ ከኛ ያገኛሉ

Amazon,Alibaba,Aliexpress, በኢትዮጵያ

Join us ከታች ይጫኑ፣ አሁኑኑ ይቀላቀሉ!

https://telegram.me/AddisEka1

https://telegram.me/AddisEka1

https://telegram.me/AddisEka1

https://telegram.me/AddisEka1

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ! በቅናሽ ይሸምቱ!

High Quality  Big Discount #Ethiopia
  ተአማኒነት እና ጥራት መገለጫችን ነው!
16.9K views20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 22:36:06 አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኗን የከተማዋ ከንቲባ ተናገሩ

የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ተገድለዋል

ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድባቸው በነበሩ የራያ አላማጣ አካባቢዎች አቅራቢያ የምትገኘው አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኗን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ ተናገሩ።

የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሄዳቸውንም ገልፀዋል።

ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ በራያ አላማጣ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች ለተከታታይ ቀናት በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ስጋት ውስጥ ገብታ የነበረችው አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የሆነችው ከትላንት ሰኞ ሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል

የራያ አላማጣ ባለሥልጣናት ለተኩስ ልውውጡ ምክንያት የሚያደርጉት በትግራይ ኃይሎች “ተከፍቷል” ያሉትን ጥቃት ሲሆን፣ የትግራይ ክልል ደቡብ ትግራይ ዞን ደግሞ የወረዳ አስተዳደሩ ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸውን በመጥቀስ ሌላውን አካል ተጠያቂ ያደርጋል።

ለቀናት በቀጠለው ግጭት ውስጥ የትግራይ ኃይሎች “ክፍለ ጦሮችን ማሰለፋቸውን” የሚናገሩት የራያ አላማጣ ወረዳ ባለሥልጣናት፤ ታጣቂዎቹ ሌሎች የወረዳውን አካባቢዎች መቆጣጠራቸውን እና ወደ አላማጣ ከተማ እየተጠጉ መሆኑን ሰኞ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ቢቢሲ በዛሬው ዕለት ያነጋገራቸው ሁለት የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ከሰኞ ከሰዓት ጀምሮ በርካታ ነዋሪዎች ወረዳውን እና ከተማውን ለቀው በመውጣት ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሸሻቸውን ተናግረዋል። ነዋሪዎች “ሸሽተውባቸዋል” ከተባሉ አጎራባች አካባቢዎች አንዱ ቆቦ ከተማ ሲሆን፣ አንድ የቆቦ ከተማ ኃላፊ ከትናትን ጀምሮ በርካታ ወደ ከተማዋ እየገቡ መሆኑን ገልፀዋል።

የራያ አላማጣ ወረዳ እና የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎችም ከሰኞ ጀምሮ አካባቢውን ለቅቀው መውጣታቸውን በአሁኑ ሰዓት ቆቦ እንደሚገኙ የገለፁት የአላማጣ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ተናግረዋል። ከትናንት ጀምሮ አላማጣ ከተማን እየተቆጣጠሩ ያሉት የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት መሆናቸውን ከንቲባው አስታውቀዋል።

“[አላማጣ] ከተማው መከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ ነው ያለው። ዙሪያው የተያዘው ግን በትግራይ ታጣቂዎች ነው” ያሉት አቶ ኃይሉ፤ በከተማዋ “ውስጥ ለውስጥ የትግራይ ታጣቂዎች” አሉ ሲሉ ከስሰዋል።

“ቦታውን ከተቆጣጠሩት እዚያ እየሠራን ነው ማለት አይደለም” ያሉት አቶ ኃይሉ፤ የራያ አላማጣ አካባቢዎች በአማራ ክልል ስር ከሆነ በኋላ በተመሠረው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የነበሩት ኃላፊዎች በአሁኑ ሰዓት ከተማውን እያስተዳደሩ አለመሆኑን ገልፀዋል።

የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሞላ ደርበው እና ለሌች ቁጥራቸውን ያልገለጿቸው ሰዎች በትናንትናው ዕለት መገደላቸውን ከንቲባው ተናግረዋል። የአቶ ሞላ ህልፈት ምክንያት ከትግራይ ኃይሎች ጋር በተደረገ “ውጊያ” አለመሆኑን ጠቅሰዋል።

“[አቶ ሞላ ሕይወታቸው ያለፈው] ከህወሓት ጋር በተያያዘ አይደለም። ሕግ የያዘው ነገር ስለሆነ ተጣርቶ የሆነ ነገር እስከሚባል ድረስ ዝርዝሩን [አልገልፅም]” ሲሉ ምክንያቱን ከመናገር ተቆጥበዋል።

(Via ቢቢሲ አማርኛ)

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja
17.0K viewsedited  19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 21:34:37
Get ready for the biggest GameFi launch of 2024

Launch: Raydium - 1800 UTC April 16 

Less than 14 hours remain until listing on Raydium

Solcraft is prepared to dominate the web3 gaming scene with their innovative integration of the Solana Blockchain-based $SOFT token

What to expect?
Cryptos Biggest Influencers 
Listings and trendings on top crypto hubs
Tier 1 Article & Media Publications
Partnerships With Industry Leading P2E Platforms & Communities

The Solcraft server & leaderboards are live!  Experinece web3 gaming like never before and earn real rewards backed by real liquidity.  Secure your $SOFT bag and prepare for an epic adventure

Website TG Community
Twitter
17.7K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 14:52:07
በኮሪደር ልማት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኑ

በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ምክንያት ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ መከልከሉንም ነው ፖሊስ ያሳሰበው፡፡


   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja
19.6K viewsedited  11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ