Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.97K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-24 20:14:35
ከሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ ስራ እስካሁን ከ9ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተነገረ

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 181 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሁሉም ወንዶች እንደሆኑና 4 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
27.2K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 10:21:34
ሐሰተኛ መረጃ

በአማራ ክልል የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት ይመለከታል በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ነው።

ሰሞኑን በአማራ ክልል ‘የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታትን ይመለከታል’ በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተጠቆመ።

ለሁሉም ዞንና ከተማ አስተዳደሮች በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ደብዳቤ የተጻፈ በማስመሰል የወጣው መረጃ ፍጹም ሐሰት መሆኑን ክልሉ አረጋግጧል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በክልሉ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።

በዚህም በክልሉ ያሉ የጸጥታ ኃይሎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ተቀናጅተው እያመጡት ያለው ውጤት ኪሳራ ያደረሰባቸው ኃይሎች በሚልሻውና ህብረተሰቡ ውስጥ መደናገርን ለመፍጠር አልመው የፈጸሙት እኩይ ድርጊት መሆኑ ተገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
39.4K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 18:33:49
ህ.ወ.ሓ.ት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ውይይት አላደረግኩም፤ መሰረታዊ ልዩነቶችም አሉን ሲል ገለጸ

የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እያደረጉ የሚገኙት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ትላንት እና ዛሬ እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎችን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ህወሓት እና ብልጽግና ፓርቲ ለመዋሀድ ተከታታይ ውይይትና ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ ከህወሓት አጭር መረጃ እንደተመለከተችው "ህወሓት እና ብልጽግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው" በማለት በይፋዊ ገጹ ሰፍሯል።

ይኹን እንጁ ልዩነቶቹ እንዳሉ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች በመኖራቸው ተከታታይ ውይይት ተጀምሯል ተብሏል።

"ከዚህ ባለፈ ግን ህወሓት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው" ሲል ድርጅቱ ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ሕወሓት ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ ነው በሚሉት ዘገባዎች የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር መጀመራቸው እና ከሁለት ሳምንታት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀ መንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው ድርድሩን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

እነዚሁ ዘገባዎች በህወሓት ውስጥ ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው" በሚሉ እና "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው" በሚሉት ሃሳቦች መከፋፈል መኖሩን የጠቆሙ ቢሆንም ህወሓት ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
44.4K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 13:54:25
የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለባቸው ባላቸው የተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

በዚህም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው አስታውቋል።

ከኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር፣ ከሶማሊያና ኬኒያ የሚያዋስኑ ድንበሮች 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ዙሪያ ዜጎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲል የጉዞ መረጃዎችን በሚሰጥበት ድረገፅ አስፍሯል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
44.8K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 12:27:43
በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ የለኝም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንደሌለው አስታውቋል፡፡

አጭበርባሪዎች የባንኩን ስምና አርማ እንዲሁም ቀለማት በመጠቀም ሀሰተኛ ገጾችን በመክፈት የማጭበርበር ወንጀል እየፈፀሙ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ለህበረተሰቡ በማሳወቅ ላይ እንደሚገኝም ባንኩ ገልጿል።

በምስሉ የተመለከተው በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ የቴሌግራም ገፅ ሀሰተኛ መሆኑን የገለፀው ባንኩ፤ ይህ ሀሰተኛ ገፅ አባላትን ስታስገቡ (Add member) ሽልማት ታገኛላችሁ በሚል የማጭበርበሪያ መልእክት የተከታዮቹን ቁጥር በማሳደግ ላይ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ባንኩ በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንደሌለው ግልፆ፤ ደንበኞች የባንኩን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ እና ከአጭበርባሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
30.3K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 07:42:01
በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ አቆሙ

በሳውዲ አረቢያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ እና አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ በተለያዩ አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ ማቆማቸው ተጠቁሟል።

በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል ሪያድ፣ ዲሪያህ፣ ሁረይማላ ከዱርማ እና አል ቁዋይያህ ይገኙበታል ተብሏል።

የሀገሪቱ መንግስት እንዳስታወቀው ለጥንቃቄ ሲባል በአሲር፣ ናጅራን እና በሌሎች የተጎዱ አከባቢዎች የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል።

ኪንግ ካሊድ ዩኒቨርሲቲ እና ናጃራን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም የቢሻ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲዎች በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ የተነሳ ስራቸውን ማቆማቸውም ነው የተገለጸው።

የሀገሪቱ ሚቲዎሮሎጂ ማዕከል በአየር ሁኔታ ዘገባው በምስራቅ እና በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክልሎች በቀጣይ ቀናት ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ እንደሚጥል ተንብዮአል።

ከመካከለኛ እስከ ከባድ ነጎድጓዳማ ንፋስና በረዶ የታጀበ የአየር ሁኔታ በሪያድ ክልል እስከ ሰኞ ድረስ እንደሚቀጥልም ማዕከሉ ገልጿል።

በተጨማሪም ማዕከሉ በቀይ ባህር እና በአረብ ባህረ ሰላጤ ላይ ያለው የባህር ላይ የንፋስ ፍጥነት በሰአት እስከ 50 ኪ.ሜ እንደሆነና እና በነጎድጓድ ጊዜ ከፍታው ከሁለት ሜትር ሊበልጥ እንደሚችል ማስታወቁን ገልፍ ኒዊስ ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
36.1K views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 07:41:56
በጾም ወቅት ምን ልጠቀም ብለዉ እያሰቡ ከሆነ በአንድ ማንኪያ ከ23 ግራም በላይ ፕሮቲን ሊያገኙበት የሚችሉትን 100% የቪጋን ፕሮቲን አመጣንልዎ።

በከፍተኛ ጥራት የተመረተ

አሁኑኑ ለማዘዝ 9369 ላይ ይደውሉልን፣ የዘርፉ ባለሟያዎች ትክክለኛዎቹን ምርቶች ለመምረጥ እና ፈጣን አቅርቦትን ለማዘጋጀት ይረዳዎታል።

የሚያስፈልገው ጓደኛ ካለዎት share ማድረግዎን አይዘንጉ!


አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ 9369


+251966113766

Join  https://t.me/+RCaZ_Ka6SOrlz0u5
32.1K views04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 07:41:40
መኪና ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ከፈለጉ ያለምንም ክፍያ
ይህንን የቴሌግራም መተግበሪያ ይቀላቀላሉ።

https://t.me/Poppycarmarket

0911248768   ይደውሉልን
31.1K views04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 17:40:22
ያለአግባብ ከተወሰደው ብር 96 ነጥብ 3 በመቶው ተመልሷል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ባሳለፍነው መጋቢት ወር ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ባጋጠመ ችግር ምክንያት 801 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ያለአግባብ መወሰዱን ባንኩ አስታውሷል፡፡

ከዚሁ የገንዘብ መጠንም እስከ አሁን 96 ነጥብ 3 በመቶ (771 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር) ተመላሽ መደረጉን የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ቀሪውን ያለአግባብ የተወሰደ ብር የማስመለስ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተመላከተው፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
39.5K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 15:57:05
በ41 ዓመቱ ፈጣኑን የማራቶን ሠዓት ያስመዘገበው አትሌት

ቀነኒሳ በቀለ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ከ2019 ወዲህ ፈጣኑን ሠዓት በማስመዝገቡ አድናቆት ተችሮታል፡፡

አትሌት ቀነኒሳ የዛሬውን የለንደን ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡

የዓለም አትሌቲክስም አትሌቱ የገባበት ይህ ሠዓት ከ2019 ወዲህ ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ ሲመዘገብ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለጽ አድናቆቱን ገልጿል፡፡

አትሌቱ ባለፈው የፈረንጆቹ ታኅሣስ ወር ላይ በቫሌንሲያ ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ19 ሠከንድ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን በለንደን ማራቶን ደግሞ ይህን ሠዓት በአራት ሰከንድ ዝቅ በማድረግ አሻሽሎታል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
40.7K viewsedited  12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ