Get Mystery Box with random crypto!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሰርጥ አድራሻ: @eliasmeseret
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 99.16K
የሰርጥ መግለጫ

Journalist-at-large

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-14 20:25:41 የዛሬ 50 አመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከካናዳ፣ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከቱርክ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጣልያን... ወዘተ ይበልጣል?

አንዳንድ 'ተቀፅላዎች' ይህን ስክሪንሾት በስፋት ሲያጋሩ እንደነበር ጥቆማዎች ደርሰውኝ ነበር፣ እንዲጣራም የጠየቁ አሉ። ነገሩ እንዲህ ነው፣

መረጃው በ Goldman Sachs የ 2022 ሪፖርት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እ.አ.አ በ 2075 ወይም የዛሬ 50 አመት 6.2 ትሪሊየን ዶላር የማደግ እድል እንዳለው ይጠቁማል። በዚህ መረጃ ላይ ታድያ እነ ከካናዳ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ቱርክ፣ አውስትራሊያ፣ ጣልያን ከኢትዮጵያ በታች የተቀመጡ ሲሆን ቻይና፣ ህንድ እና አሜሪካ ከ 1-3 ያለውን ቦታ ይዘዋል።

እውነታው ግን ወዲህ ነው፣

እንዲህ አይነት የኢኮኖሚ እድገት ትንበያዎች በአብዛኛው የወደፊት የማደግ አቅምን የሚያሳዩ ሲሆን በርካታ አሁናዊ እና የወደፊት እድሎችን እና መሰናክሎችን አያካትትም። በተጨማሪም ይህ አሀዝ በከፍተኛ ደረጃ የሚንተራሰው የህዝብ ብዛት ቁጥር ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት በ2075 አካባቢ 281 ሚልዮን ይገመታል፣ ይህም ለከፍተኛ ምርታማነት እና የኢኮኖሚ እድገት መሰረት የመሆን እድል አለው። ሪፖርቱ የጠቀሰውም ይህን ነው።

ይሁንና ተቀፅላዎቹ ሊያቀርቡት እንደፈለጉት ይህ ብቻውን የሀብት ወይም እድገት መለኪያ እንዳልሆነ አለም ተግባብቷል። ትክክለኛ እድገት መለኪያው ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል፣ የኑሮ ደረጃ መሻሻል፣ እንደ ውሀ፣ መኖርያ ቤት እና ኤሌክትሪክ ላሉ አገልግሎቶች ያለ ተደራሽነት... ወዘተ መሆናቸውን ራሱ Goldman Sachs ይጠቅሳል።

- የጋሪ እና ፈረስ ትራንስፖርት እናመጣለን እየተባለ ወደ ቀደመው ክፍለ ዘመን ወደኋላ ለመሄድ እየተንደረደርን

- በአለም ትላልቅ የሚባሉ ግጭቶች፣ ጦርነቶች፣ መፈናቀሎች እና ስደቶች እያስተናገድን

- የህዝብ የመኖር፣ የቤት ባለቤትነት፣ የስራ እና ተንቀሳቅሶ የማምረት አቅም እየተፈተነ... ወዘተ ባለበት ወቅት ይህን ትንበያ ይዞ ከካናዳ እና አውስትራልያ ልንበልጥ ነው ማለት ማደንዘዣ እንጂ ምንም ሊሆን አይችልም።

ብቻ መልካሙን ለሀገራችን እንመኛለን።

@EliasMeseret
24.9K viewsElias M, edited  17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 20:25:32
23.4K viewsElias M, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 19:17:17
ለእርሻ፣ ለኮንስትራክሽን እና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚውሉ ትራክተሮች እና ከባድ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳያስገቡ እንደተከለከሉ አስመጪዎች መናገራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነበበን

ይህም የሆነው ካለምንም መመርያ ሲሆን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያለ ምንም በቂ ምክንያት "የመኪና ማስገቢያ ፈቃድ አልሰጣችሁም" እንዳላቸው ገልጸዋል። ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃም የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትን ጠይቁ መባላቸውን አመልክተዋል።

ከሁሉም ግር የሚለው ደግሞ በቅርቡ በከተሞች በእንስሳት የታገዘ ትራንስፖርት እንዲኖር ስራ እየሰራ እንደሆነ የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከባድ ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ እንዲሰሩ መጠበቁ ነው።

በኤሌክትሪክ የሚሰራ ትራክተር? ገልባጭ መኪና? ግሬደር? ቡልዶዘር?

ታድያ ይህ እየሆነ ያለው በቢልዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ለጫካ ፕሮጀክት እየፈሰሰ፣ ተጨማሪ በመቶ ሚልዮን ዶላሮች የሚቆጠር ደግሞ ለከተማ ማስዋብ እና ለቱሪዝም ስፍራዎች ግንባታ እየዋለ ባለበት ወቅት ነው።

ነዳጅ ለማስገባት የዶላር በእጅጉ መመናመን እንዳለ እንረዳለን፣ ግን በአንድ በኩል ለወደፊት ሊቆዩ የሚችሉ የከተማ ማስዋብ ፕሮጀክቶች ላይ ገንዘብ እየፈሰሰ፣ በዚህ በኩል ደግሞ ያውም ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ የሆኑትን ግብርናን እና ግንባታን የሚያከናውኑ ቅንጡ ያልሆኑ ተሽከርካሪዎችን መከልከል ምን ያህል misplaced priorities እንዳሉብን ማሳያ ነው።

@EliasMeseret
26.9K viewsElias M, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 06:35:22 “ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ እና ከዳሽን ባንክ ጋር ያለው ግንኙነት እስካሁን አልተቋረጠም”--- የጤና ሚኒስቴር

"በተያዘው በፕሮግራም መሰረት በዓመት አራት ጊዜ እጣ መውጣት እያለበት እስካሁን 2 ጊዜ ብቻ ወጥቷል"--- የጤና ባለሙያዎች

ከሰሞኑ በተከታታይ ከሚደርሱኝ ጥያቄዎች አንዱ በጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ተጭበረበርን የሚሉ ዜጎች ይገኙበታል። ኢትዮጵያ ቼክ የሰራውን ዘገባ ላጋራችሁ

ከሰሞኑ “ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የተፈራረመውን የጤና ዘርፍ ሰራተኞች ቤት ግንባታ ስምምነት አፍርሷል፤ ቤት ለማግኘት ክፍያ የፈጸሙ የጤናው ዘርፍ ሰራተኞችም ተጭበርብረዋል” የሚሉና ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን እንዲያጣራ የሚጠይቁ መልዕክቶች ከተከታታዮቻችን ደርሰውናል።

የጤና ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ቼክ ባደረሱት ተከታታይ መረጃ የከፈሉት ብር ይመለሳል የሚል መረጃ ሲዘዋወር እንደተመለከቱና ይህም ማለት ማህበሩ ፈርሷል ብለው እንዲያስቡ እንዳረጋቸው ጠቁመዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ አክለውም የጎጆ ዕጣ በተያዘው በፕሮግራም መሰረት በዓመት አራት ጊዜ መውጣት እያለበት እስካሁን 2 ጊዜ ብቻ ወጥቷል፣ በውል ስምምነቱ መሰረት በየ 3 ወሩ ነው ዕጣ ይወጣል ቢልም በ ውሉ መሰረት ዕጣ አልወጣም እንዲሁም ችግሮች እንኳን ቢኖሩ እነዚህ ችግሮች ሲፈጠሩ ወቅታዊ መረጃ ለተመዝጋቢዎች አልተሰጡም የሚሉ ቅሬታዎች ቀርበዋል።

የጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክትን በተመለከተ ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ እና ዳሽን ባንክ ጋር የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራርሞ የመጀመሪያ ዙር እጣ ማውጣት ስነ ሰርዓት የተካሄደው ሰኔ 2015 ላይ ነበር።

በስነ ሰርዓቱም 200 ጤናው ዘርፍ ሠራተኞች የመጀመርያ ዙር የዕጣ እድለኞች ሲሆኑ ዕጣ  የማውጣት ሂደቱ በየሶስት ወሩ እንደሚቀጥልና እየሰፋ እንደሚሄድም ተጠቁሞ ነበር። ይህ መረጃም በወቅቱ በሚኒስቴሩ የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ ተጋርቶ ነበር፡ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02PnHVv2sH6DiS4B6m3H72FzPTVitoq2k2GBKEcPQyytBMPkZfZFDFctwHqBTWjB9El&id=100064567187444&mibextid=qC1gEa

ይሁን እንጂ “ሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ስምምነት ፈርሷል” የሚለውን መረጃ መነሻ በማድረግ ኢትዮጵያ ቼክ ከጤና ሚኒስቴር እና ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት አድርጓል።

በጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ ሰው ሀብት ልማት ማሻሻያ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አሰግድ ሳሙኤል ጉዳዩን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ የሰጡ ሲህን ‘በሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ስምምነት ፈርሷል’ የሚለው መረጃ ሀሰት መሆኑን ነግረውናል።

“ጤና ሚኒስቴር ከጎጆ እና ከዳሽን ባንክ ጋር ያለው ግንኙነት እስካሁን አልተቋረጠም። ያንን የሚያደርግ ከሆነ ጤና ሚኒስቴር በባለሙያው በኩል ነው የቆመው” ያሉት አቶ አሰግድ፤ “ማንኛውም በዚህ ሂደት ውስጥ የሚያልፍ ነገር ባለሙያው ላይ ማንኛውም አይነት ችግር የሚፈጥር ከሆነ (ጤና ሚኒስቴር) በፍጹም ዝም ብሎ የሚያይበት ነገር አይኖርም። ስለዚህ የመግባቢያ ስምምነቱ እስካሁን አልተቋረጠም” ብለዋል።

የጤና ሚኒስቴር ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ጋር ስምምነት ሲፈጽም የተቋሙን ህጋዊ ሰነዶችን ተመልክቶ መሆኑን የሚናገሩት ስራ አስፈጻሚው ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ፤ ዳሽን ባንክና ጤና ሚኒስቴር የተፈራረሙት ስምምነት አላማ 10 ሺህ ቤቶችን በ10 አመት ገንብቶ ለመጨረስ እንደሆነም ነግረውናል።

ባጠቃላይ ከ8000 በላይ ሰራተኞች የፕሮግራሙ አካል መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ አሰግድ፤ እስካሁን በሁለት ዙሮች 400 የጤናው ዘርፍ ሰራተኞች በጋራ የማህበር ቤት እንዲገነቡ እጣ እንደወጣላቸውም ይናገራሉ።

ይሁን እንጂ “እጣዎቹ ከወጡ በኋላ ችግር የሆነው ከመሬት አስተዳደር፤ ከአዲስ አበባ ማህበራት ማደራጃ ጋር ተያይዞ የተወሰኑ የአሰራር ለውጦች ተደረጉ። ከተማ ውስጥ ያለው ከመሬት ጋር ተያይዞ ያለው ችግርም የሚታወቅ ነው። ከተማ አስተዳደሩ ያንን ማኔጅ ለማድረግ በየጊዜው የሚያወጣቸው አዳዲስ ህጎች አሉ። እነሱ (ሂደቱን) አፌክት አድርገውታል” ብለዋል።

ስለዚህም እጣ የወጣላቸው እድለኞች በሚፈለገው ጊዜ ግንባታ ያለመጀመራቸውን በመጥቀስ “ትልቁ እኛም የገመገምነው ችግር አሁን ባልኩት ዉስጣዊም ዉጫዊም ችግሮች፤ ጎጆም ጋር ባለው ግንባታው ዘግይቷል የሚል ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም ጤና ሚኒስቴር የጤናው ዘርፍ ሰራተኞችን ለማበርታትና ለማትጋት ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ በተጨማሪ ሌላ የመኖሪያ ቤት ማግኛ አማራጮች ላይ እየሰራ መሆኑንም አቶ አሰግድ ሳሙኤል ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረዋል።

በሌ በኩል ጉዳዩን በተመለከተ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግን አስተያየት ለማግነት ለዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አለማዉ ጋሪ ብንደዉልም ለጊዜው መረጃ ማግኘት አልቻልንም።

@EliasMeseret
39.1K viewsElias M, 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 06:35:08
35.6K viewsElias M, 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 06:11:55 #ጥቆማ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና (Dire Dawa Free Trade Zone) ውስጥ ከሚገኘው የ UN የምግብ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ ለተራቡ ዜጎች ተብለው የሚወጡትን የምግብ አይነቶች እዛው የንግድ ቀጠና ውስጥ ፓኬጁ ላይ ባንዲራ በመጨመር ለሌላ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገው ከስፍራው እየወጡ እንደሆነ ከስፍራው እየደረሱኝ ያሉ ተደጋጋሚ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የሚመለከተው አካል ካለ በዜጎች ረሀብ የሚጫወቱትን እነዚህ አካላት ስርዐት ሊያስይዝ ይገባል።

@EliasMeseret
34.8K viewsElias M, 03:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 05:41:35
#የሚድያነፃነት የዛሬ 5 አመት ግንቦት 2011 ዓ/ም ላይ የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ አዘጋጅታ ነበር፣ በፕሮግራሙ ላይ ከዓለም ዙርያ የተውጣጡ የሚድያ ባለሙያዎች ታድመው ነበር፣ እኔም ተገኝቼ ነበር።

እለቱ በኢትዮጵያ እንዲከበር የተደረገው በወቅቱ በእጅጉ ተሻሽሎ የነበረውን የፕሬስ ነፃነት recognition ለመስጠት ጭምር ነበር። የተደረጉት ንግግሮች፣ ቃል የተገባባቸው ጉዳዮች እና ተስፋ ሰጪ ምልክቶች በርካቶች ነበሩ። በኢህአዴግ ስርዐት ውስጥ ለበርካታ አመታት በችግር ውስጥ ጋዜጠኝነት እንደሰራ አንድ ባለሙያ እኔም ተስፋ ታይቶኝ ነበር። 

ዛሬስ?

ዛሬ ላይ ያ ሁሉ ተቀይሮ ከድሮው እጅግ የባሰ የፕሬስ መብት ረገጣ ያለበት ግዜ ሆኗል። ጋዜጠኛ አይደለም ስህተት ሰርቶ ገና ለገና ለተቃዋሚ ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል፣ ግፎችን ሊያጋልጥ ይችላል እና ሚስጥር ሊያወጣ ይችላል ተብሎ ወደ እስር ቤት ተግዟል።

ከሰሞኑ እየሰማሁት እንደሆነው ደግሞ የመንግስት ሚድያዎች ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ጭምር ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እየገቡ ነው። በባለስልጣናት ቀጭን ትእዛዝ ይህን ዘግብ፣ ያንን አትዘግብ እየተባሉ ማስፈራርያ ጭምር እየደረሰባቸው ነው። ሌላው ቀርቶ አንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሙስናና እና ሌሎች ወንጀሎች ሰራተኞቻቸው ሲታሰሩ "የቀድሞ ሰራተኛ ብላችሁ ዘግቡ" በማለት በተለይ የመንግስት ሚድያዎችን እያስገደዱ ይገኛሉ።

"በፕሮግራም ላይ ተገኝቼ ለምን ዜና አልሰራህም?" ተብሎ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከስራው የተባረረው ነፍሱን ይማረው ጋዜጠኛ በቀለ ሙለታ አንድ ምስክር ነበር። በቅርቡ ከአዲስ ዘመን፣ ከኢዜአ፣ ከኢቲቪ፣ ከፋና... ወዘተ ስራቸውን የለቀቁም አሉ።

Free the media!

@EliasMeseret
34.4K viewsElias M, 02:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 04:39:00
ግለሰቡ ስርዐት የሚጎድላቸው እና ያልተገሩ መልዕክቶችን ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ከሚያሰራጩ ባለስልጣናት አንዱ ናቸው

እኚህ ግለሰብ አሁን ደግሞ BYD ስለተባለ የቻይና መኪና አምራች ኩባንያ ትዊት ባደረጉበት አንድ ፅሁፍ ህፃናት እንዲያዩት የማይመከር ድረ-ገፅ ከፍተው ሲያዩ እንደነበር የሚያሳይ ምስል አብረው ትዊት አርገው ነበር (ምስሉ ተያይዟል)፣ ኋላ ላይ እሱን አጥፍተው እና ድረ-ገፁን ቆርጠው መልሰው መረጃውን አጋርተዋል።

ለልጆቻችን ምን እናስተምር?

Pics: Sad Engineer

@EliasMeseret
35.9K viewsElias M, 01:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 22:44:29
ግድያን ለመሸፋፈን መሯሯጥ?!

በርካቶችን ያሳዘነውን የበቴ ኡርጌሳን የጭካኔ ግድያ "ከወንድማቸው ጋር ድብድብ ውስጥ ገብተው ነበር" እና አሟሟታቸው ከእርሻ ስራቸው ጋር በተያያዘ እንደሆነ ህዝብን ለማሳመን የሚደረገውን የማህበራዊ ሚድያ ዘመቻ አያይዤዋለሁ፣ የፕሮፋይል ፎቷቸው እንኳን የአንድ ምድብ ሰዎች እንደሆኑ ያስታውቃል።

ለማንኛውን ተአማኒነት ያለው ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ ሊደረግ ይገባል።

@EliasMeseret
39.7K viewsElias M, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 11:55:14
ለበርካታ ወራት በእስር ሲሰቃዩ የነበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሩ አቶ በቴ ኡርጌሳ በትውልድ ከተማቸው መቂ ከተማ በትናንትናው እለት ተገድለው እንደተገኙ ታውቋል

አርፈውበት ከነበረው ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው የተገደሉት አቶ በቴ በንግግራቸው እና በሰከነ አስተሳሰባቸው በብዙዎች ዘንድ የሚታወሱ ናቸው።

ነፍስ ይማር

@EliasMeseret
45.8K viewsElias M, 08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ