Get Mystery Box with random crypto!

አንድ የመከላከያ ሰራዊት መኮንን ይህን ጽሁፍ በገጼ ላይ እንዳወጣው በጠየቀኝ መሰረት፣ እነሆ አስተ | Betty Tafese Official

አንድ የመከላከያ ሰራዊት መኮንን ይህን ጽሁፍ በገጼ ላይ እንዳወጣው በጠየቀኝ መሰረት፣ እነሆ አስተናግጀዋለሁ። አመሰግናለሁ ።

የብረት አጥር ክንዳቸው የማይነጥፍ

ሃገራችን እትዮጵያ በታሪክ ማንንም ወራና ተተናኩሳ አታቅም ግን በቃ ሁሌም ጠላት አይኑ ባያት ቁጥር ለመውረር ሉዓላዊነትዋን በመዳፈር ህዝብዋን ለማሰቃየት ይጥራል ።

የጀግኖች ሃገር ኢትዮጵያ ግን ተሸንፋና ተንበርክካ አታውቅም ምክንያቱም በደም ስራቸው ሁሌም ጀግናና አሞተ መራራ ቆራጥ ልጆች አልዋት ።

አዎ በይበልጥ የልጆችዋን መጠርያ መከላከያ ትለዋለች። ታድያ ዛሬ ላይ ሃያል፣ ግዙፍ፣ የብረት አጥር ክንዳቸው የማይነጥፍ በስነ ልቦናም ይሁን በማቴሪያል ዝግጁነቱ የተጠናከረ ትላትን የሰራውን ገድልና ጀግንነት ማስቀጠልና ድል ማስመዝገብ የሚችል ሃይል ተፈጥሯል ።

ጠላቶቻችን ሁሌም አንድ ነገር ይችላሉ-መፎከር። ግን እውነት እላችኋለሁ ኢትዮጵያ ነክቶ ወደ ቤቱ ተመልሶ በሰላም የተኛ የለም። ምክንያቱም ያነደዱትን እሳት ቆስቁሶና የተዳፈነውን ሴራ ጉልጉሎ በማውጣት ለምን መጀመርያ ለኮስነው ብለው እስኪፀፀቱ ድረስ በለኮሱት እሳት ወደ እሳተ ገሞራነት ቀይሮ የሚያቃጥል፣ ወደ አመድነትም የእብሪትን ክምር የሚቀይር፣ የመከላከያ ሃይል ተገንብቷልና ።

ጠላቶቻችን ከቻሉ መልሰውና ደጋግመው ያስቡበት አለበለዚያ ግን ሞታቸው መቅረቡን አስበው በመጨረሻም ትርጉም የለሽ ዋጋ ይከፍላሉ።
ይህንን የመሰለ የሞራል ስንቅ ሼር ባታደርጉት እውነት ያስተዛዝባል። ሼር ፔጁን like አድርጉ መረጃ አንዱ የጦር መሳሪያ ነው።#ሼር_follow_ያርጉ

ለፈጣንና ታማኝ መረጃዎች @emsmereja ን join ማድረጎን አይርሱ
@emsmereja
@emsmereja
@emsmerej