Get Mystery Box with random crypto!

ከቤተ-አምሓራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ ለህዝባችን ቀድመን እንዳንሞት ወደ ግንባር እንዳንሄድ በመንግስ | ቤተ-አምሓራ ሚድያ Bete amhara media

ከቤተ-አምሓራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ

ለህዝባችን ቀድመን እንዳንሞት ወደ ግንባር እንዳንሄድ በመንግስት አመራሮች ተከለከልን

በራሱ ትጥቅ እና ስንቅ እየታገለ ለህዝቡ ደጀንና መከታ የሆነውን ፋኖ የብልፅግና መንግስት እያሰረው፣ እያሳደደው፣ እየገደለው እና በጨለማ ቤት ሳይቀር አጉሮ መከራችንን እያበላን እንደምንገኝ ሃገር የሚያውቀው ሃቅ ንው፡፡ ይህን ሁሉ መከራ እየተቀበልን ዝም ያልነው ለህባችን ሰላምና ደህንነት ቅድሚያ ስለምሰጥ ነው፡፡

ነገር ግን በመንግስት አኩርፈን ህዝባችን ሲሰቃይ ዝም ብለን ማየት አንችልም፡፡ በመሆኑም ቀድሞ ህዝብ በሚያውቀው አደረጃጀት የደቡብ ወሎ ፋኖ፣የደሴና የኮምቦልቻ ፋኖ ውህደት አድርጎ “ቤተ አምሓራ ፋኖ” በሚል ስያሜ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በመሆኑም ዛሬ የደቡብ ወሎ አመራር ወደ ግንባር ሊገባ የነበረ ለወገን ጦር ከፍተኛ ደጀን ሊሆን የሚችል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቤተ አምሓራ ፋኖ ሰራዊት ወደ ግንባር ለመግባት ዝግጁትን ጨርሶ ባለበት ወቅት ወደ ግንባር እንዳንገባ ተከለከልን።

ወደ ግንባር እንድንገባ የትራንስፓርት ስምሪት እዲመቻች አድርጉልን ብለን በጠየቅነው መሰረት የደቡብ ወሎ ዞን አመራር የማናውቀውን ሀይል ትራንስፖርት አናመቻችም፤ ወደ ግንባር መቀሳቀሻም የስምሪትም (የመቀሳቀሻ) ደብዳቤም አንሰጥም ብለው የከለከሉን መሆኑን ህዝባችን እድታወቅልን እንፈልጋለን በማለት ተናግረዋል።
ከትናንቱ ያልተማሩ ህዝብን እንመራለን የሚሉ አመራሮች አሁንም ህዝባችንን ለሌላ ዙር ስደትና ሞት እየዳረጉት ይገኛሉ።

በዚህ ወቅት የወገን ጦር ከጠላት ጋር እየተፋለመ ባለበት ሰዓት ሂጄ ላግዝ፣ ልሙት የሚልን ሀይል በእልልታ መሸኘት ይገባ ነበር።
በተጨማሪም ለህዝባችን ቀድመን መድረስ ስንችል ጠላት በህዝባችን ላይ መከራ እዲበዛበት ጭምር እየተደረገ መሆኑን ህዝባችን  ይወቅልን ብለዋል።


ማሳሰቢያ ምናልባት ፋኖን ስምሪት መንግስት አይሰጠውም ለምን ዝምብሎ አይገባም ከተባለ አሁንም ድረስ ብዙ አባሎቻችን በእስር ላይ ያሉ በመሆኑ እና የተወሰነ ትጥቅ በመንግሥት እጅ ላይ ያለ በመሆኑ ከድሃ ኪሳችን አውጥተን የገዛነው መሳሪያ እንዲመለስ ለማድረግና በወጣው አስቸኳይ ጊዜ መመሪያ መሰረት በደሴም ሆነ በዞኑ ወረዳዎች ትጥቅ ይዞ ወደ ግንባርም መቀሳቀስ ስለማይቻል ፍቃድ እዲሰጠን ለማድረግ እንደሆነ እድታወቅልን እንፈልጋለን።
ስለሆንም ህዝባችን ይህንን አዉቆ በምናደርገው ትግል ከጎናችን እንዲሆን በክብር እንጠይቃለን
ድል ለአማራ ህዝብ

ቤተ-አምሓራ ፋኖ
ደሴ፣ አምሓራ፣ ኢትዮጵያ


#ሼር



ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia