Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ-አምሓራ ሚድያ Bete amhara media

የቴሌግራም ቻናል አርማ bete_amharamedia — ቤተ-አምሓራ ሚድያ Bete amhara media
የቴሌግራም ቻናል አርማ bete_amharamedia — ቤተ-አምሓራ ሚድያ Bete amhara media
የሰርጥ አድራሻ: @bete_amharamedia
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.35K
የሰርጥ መግለጫ

በሀገራችን ኢትዮጵያ በፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እንድሁም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ትንታኔ የሚሰጥ ምርጥ የቴሌግራም ቻናል።
Offical Group @BeteamhramediaGroup
Telegram፦ https://t.me/Bete_amharamedia
Facebook፦ https://www.facebook.com/beteamharamediaa/

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 16:32:36
ወልድያ ዩኒቨርስቲ
341 views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:30:02
358 views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:29:55 ሕወሓት በራያ ግንባር ጦርነት ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ከፋኖዎች ጋር በምሽግ ውስጥ ነበረኩ ። ጦርነቱ በየደቂቃው ተለዋዋጭ በመሆኑ አንድ የጠራ ምስል እስካገኝ ድረስ ከመፃፍ ታቅቤ ቆይቻለሁ።
ፋኖ ፣ መከላከያ ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ከራማ ኪዳነ ምህረት እስከ ጎብዬ ፣ በላጎ እና ቃሊም ድረስ የሞት ሽረት ውጊያ እያደረገ ነው።
ይሁን እንጅ አሁን በዚህ ሰአት የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የተወሰነው ሾልኮ ከጎብዬ በእስከ ዱቡብ ምዕራብ በኩል ዱርለበስ በሚባለው አካባቢ የአላውሃን ወንዝ ለመሻገር እየተንደረደረ ነው። ይህ አቅጣጫ በማመጫ ድጎ እየሱስ አድርጎ ወደ ወልዲያ የሚያስገባውን ዋሻው ለመዝጋት ነው።
ጥምር ጦሩ ዋሻውን ቀድሞ ቢይዝ ወልዲያን ማዳን ይቻላል የሚል መልዕክት አለኝ።
ባሳለፍነው አመትም የሕወሓት ቡድን ይህንኑ መስመር ተከትሎ ወልዲያ መግባቱ የሚታወስ ነው።
አማራ ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕወሓት ሕዝባዊ ሆኖ እንደመጣው ሁሉ ሕዝባዊ ሆኖ ካልተነሳ በስተቀር አንድ ቀን ጧት በራችንን ስንከፍት ደጃፋችን ላይ እናገኛቸዋለን።ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ


ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
362 views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:17:26 የደቡብ ወሎ አመራር ፋኖን ግንባር እንዳይገባ ከለከለ።
728 views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:17:07 https://www.facebook.com/103377659036549/posts/pfbid0JXkagrGjCrFSJkUA8xehRX5uC84BkJFUAAxNxknVMiBHf5kFbkZrYcFztXx6m96Ml/?app=fbl

የፋኖ ገፅ ነው ላይክ ሼር አድርጉት
723 views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:09:22 ከቤተ-አምሓራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ

ለህዝባችን ቀድመን እንዳንሞት ወደ ግንባር እንዳንሄድ በመንግስት አመራሮች ተከለከልን

በራሱ ትጥቅ እና ስንቅ እየታገለ ለህዝቡ ደጀንና መከታ የሆነውን ፋኖ የብልፅግና መንግስት እያሰረው፣ እያሳደደው፣ እየገደለው እና በጨለማ ቤት ሳይቀር አጉሮ መከራችንን እያበላን እንደምንገኝ ሃገር የሚያውቀው ሃቅ ንው፡፡ ይህን ሁሉ መከራ እየተቀበልን ዝም ያልነው ለህባችን ሰላምና ደህንነት ቅድሚያ ስለምሰጥ ነው፡፡

ነገር ግን በመንግስት አኩርፈን ህዝባችን ሲሰቃይ ዝም ብለን ማየት አንችልም፡፡ በመሆኑም ቀድሞ ህዝብ በሚያውቀው አደረጃጀት የደቡብ ወሎ ፋኖ፣የደሴና የኮምቦልቻ ፋኖ ውህደት አድርጎ “ቤተ አምሓራ ፋኖ” በሚል ስያሜ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በመሆኑም ዛሬ የደቡብ ወሎ አመራር ወደ ግንባር ሊገባ የነበረ ለወገን ጦር ከፍተኛ ደጀን ሊሆን የሚችል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቤተ አምሓራ ፋኖ ሰራዊት ወደ ግንባር ለመግባት ዝግጁትን ጨርሶ ባለበት ወቅት ወደ ግንባር እንዳንገባ ተከለከልን።

ወደ ግንባር እንድንገባ የትራንስፓርት ስምሪት እዲመቻች አድርጉልን ብለን በጠየቅነው መሰረት የደቡብ ወሎ ዞን አመራር የማናውቀውን ሀይል ትራንስፖርት አናመቻችም፤ ወደ ግንባር መቀሳቀሻም የስምሪትም (የመቀሳቀሻ) ደብዳቤም አንሰጥም ብለው የከለከሉን መሆኑን ህዝባችን እድታወቅልን እንፈልጋለን በማለት ተናግረዋል።
ከትናንቱ ያልተማሩ ህዝብን እንመራለን የሚሉ አመራሮች አሁንም ህዝባችንን ለሌላ ዙር ስደትና ሞት እየዳረጉት ይገኛሉ።

በዚህ ወቅት የወገን ጦር ከጠላት ጋር እየተፋለመ ባለበት ሰዓት ሂጄ ላግዝ፣ ልሙት የሚልን ሀይል በእልልታ መሸኘት ይገባ ነበር።
በተጨማሪም ለህዝባችን ቀድመን መድረስ ስንችል ጠላት በህዝባችን ላይ መከራ እዲበዛበት ጭምር እየተደረገ መሆኑን ህዝባችን  ይወቅልን ብለዋል።


ማሳሰቢያ ምናልባት ፋኖን ስምሪት መንግስት አይሰጠውም ለምን ዝምብሎ አይገባም ከተባለ አሁንም ድረስ ብዙ አባሎቻችን በእስር ላይ ያሉ በመሆኑ እና የተወሰነ ትጥቅ በመንግሥት እጅ ላይ ያለ በመሆኑ ከድሃ ኪሳችን አውጥተን የገዛነው መሳሪያ እንዲመለስ ለማድረግና በወጣው አስቸኳይ ጊዜ መመሪያ መሰረት በደሴም ሆነ በዞኑ ወረዳዎች ትጥቅ ይዞ ወደ ግንባርም መቀሳቀስ ስለማይቻል ፍቃድ እዲሰጠን ለማድረግ እንደሆነ እድታወቅልን እንፈልጋለን።
ስለሆንም ህዝባችን ይህንን አዉቆ በምናደርገው ትግል ከጎናችን እንዲሆን በክብር እንጠይቃለን
ድል ለአማራ ህዝብ

ቤተ-አምሓራ ፋኖ
ደሴ፣ አምሓራ፣ ኢትዮጵያ


#ሼርከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
764 views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:55:30
#መረጃ!

አቶ ስንታየሁ ቸኮል የ10 ሺህ ብር ዋስ የተፈቀደላቸው ቢሆንም ፓሊስ ይግባኝ ጠይቆባቸዋል።
/
በግፍ እስር ላይ ያሉት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባሉ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ በየፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፤ ፍርድ ቤቱም ለአቶ ስንታየሁ በ10ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን የዋስ መብት መሰጠቱን ተከትሎ ፖሊስ ይግባኝ ጠይቆባቸዋል።
በሀሰት ክስ የታሰሩት አቶ ስንታየሁ ከዚህ ቀደም ሁለት ግዜ ዋስትና ተሰጥቷቸው የከፈሉ ቢሆንም ፓሊስ ሳይለቃቸው መቅረቱ ይታወሳል።


ብሽቅ ስርአት
783 views11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:53:35 ከሮቢት - ቆቦ ድረስ ባሉ ጎዳናዎች የተረሸኑ የአማራ ወጣቶችና ገበሬዎች አስ***ክሬን አልተነሳም።

እህህህህ
759 views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:01:57
መረጃ ቆቦ

የህወሓት ታጣቂዎች በቆቦ ከተማ ንጹሃንን መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ!

ቆቦ ከተማን የተቆጣጠሩት የህወሓት ታጣቂዎች ንጹሃንን መግደላቸውን የራያ ቆቦ ወረዳ ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ገለጹ።መንግስት የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን መልቀቁን መግለጹን ተከትሎ የህወሃት ታጣቂዎች በራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን መገደላቸውን ነዋሪዎቹ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል።

ለደህንነታቸውን ሲባል ድምጻቸውን ቀንሰው በስልክ ያነጋገሩን ግለሰብ፤ በከተማዋ ወጣቶች መገደላቸውን ተናግረዋል።በቆቦ ከተማ ስልክ ይዞ መገኘት እንደሚስገድል የተናገሩት አስተያየት ሰጭዋ፤ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን አሁንም አለመነሳቱን ተናግረዋል።አሁን ላይ በቆቦ ከተማ በተለያዩ መንገዶች ላይ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን እንዳለ የተናገሩት ደግሞ ሌላ አስተያየት ሰጭ ናቸው። አሁን ባለው ሁኔታ አስክሬን ማንሳት እንዳልተቻለ የተገለጸ ሲሆን አሁንም ውጊያ እንዳለ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ እና አርሶ አደሮቹ “ፋኖ ናችሁ፤ የብልጽግና አባል ናችሁ፤ ሚሊሻ ናችሁ” በሚል ግድያ እየተፈጸመ እንደሆነ ገልጸዋል።በሮቢት ከተማ ብቻ ሁለት ወጣቶች መገደላቸውን ከስፍራው ወደ ወልዲያ የመጣ አንድ አስተያየት ሰጭ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግሯል።

Via Al Ain


ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
971 viewsedited  11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:53:41
"አምፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት አይቀየርም!"
//
መንግሥት የፋኖ ጓዶቼን ቢያሳድድም፣ለከፈልነው መስዕዋትነት ክሬዲት ባይሰጠኝም ከሀገሬ ክብር ስለማይበልጥብኝ ከፊት ለመሰለፍ ዝግጁ ነን፡፡ በተደጋጋሚ  የቆሰልኩት ለተከበረው ህዝቤ በመሆኑ ዛሬም ወገኔን የተከፈተበትን ጥቃት ለመመከትና ላለማስደፈር ወልቃይት ልጉዲ ላይ መሽገናል፡፡
ጠላት ባለበት ሄደን ለመቅበርም ማንኛውንም ግድጅ ዝግጁ ሆነን እንጠብቃለን፡፡

የአማራ ፋኖ
የቴዎድሮስ ብርጌድ
የገብርዬ ሻለቃ
ዋና አዛዥ
ሻለቃ ውባንተ አባተ፡፡


ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
918 viewsedited  10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ