Get Mystery Box with random crypto!

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽ | Bein sport news

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ፡፡

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከአዲስ አበባ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በወሰነው መሰረት አሁን ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢው ለመምራትና ለእንግዶቹ አስፈላጊውን አቀባበል ለማድረግ እንዲሁም የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ ከነገ አርብ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌትን በማንኛውም ሰዓት ማሽከርከር ፍፁም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

ክልከላው የሚመለከተው የፀጥታ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌቶችን መሆኑንም የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡

የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን መልእክት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ መልእክቱን ያስተለለፈ ሲሆን ÷ ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድም ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ጥር 28 እና 29 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚካሄድ ይወቃል፡፡

ምንጭ: Fana Broadcasting Corporate S.C