Get Mystery Box with random crypto!

ሠራዊቱ ሕወሓት የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በብቃት እየመከተ መሆኑን መንግሥት ገለጸ የሀገር መከ | Amhara times

ሠራዊቱ ሕወሓት የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በብቃት እየመከተ መሆኑን መንግሥት ገለጸ

የሀገር መከላከያ ሠራዊት አሸባሪው ሕወሓት የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በተሟላ ብቃት በመመከት ላይ እንደሚገኝ መንግሥት ገለጸ።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በዚህም አሸባሪው ሕወሓት የተዘረጋለትን የሰላም አማራጭ ረግጦ ለሶስተኛ ጊዜ የከፈተውን ወታደራዊ ጥቃት አጠናክሮ መቀጠሉን መንግሥት አስታውቋል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ ለሰላም የተዘረጋውን መንገድ ትቶ፤ ለጦርነት ሲዘጋጅ መቆየቱ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

አሁንም በተለያዩ ግንባሮች የከፈተውን ጥቃት አድማሱን በማስፋፋት ለፍቶ አዳሪ ንጹሐን ዜጎችን ዒላማ እያደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡ ጊዜ ያለፈበትን የሰው ማዕበል የጦርነት ስልት በመከተል በሺዎች የሚቆጠሩ አዳጊዎችንና ወጣቶችን በገፍ እየማገደ፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

አሸባሪው ሕወሓት ግድያ፣ ማፈናቀል፣ የንብረት ማውደም፣ መሠረተ ልማት የማፈራረስና መሰል የጭካኔ ተግባራትን ለመፈጸም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ኃይል አሰባስቦ ወደ አማራና አፋር ክልል አዋሳኞች እየተንቀሳቀሰ ነው ብሏል መንግሥት። መንግሥት የዘረጋው የሰላም አማራጭ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይህ አሸባሪ ቡድን የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በተሟላ ብቃት በመመከት ላይ ይገኛል።