Get Mystery Box with random crypto!

# ሰበር ዜና--- / 'በመንግስት ጫና በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረ | Amhara times

# ሰበር ዜና---
/
"በመንግስት ጫና በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ" -እስክንድር ነጋ

የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ ሀምሌ 16፣2014 ዓመተ ምህረት ካሉበት ቦታ በጻፉት ደብዳቤ፣ ተረኛና ጨቋኝ መንግስት በፈጠረው ጫና ሳቢያ በፓርቲያቸው በአመራርነትም ሆነ በአባልነት መስራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ይፋ አደረጉ። የደብዳቤያቸው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። ፊርማቸው ያረፈበት የአጅ ጽሁፋቸውም ከዚህ ደብዳቤ ጋር ተያይዟል።

/
ሀምሌ 16፣ 2014
/
ለባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
/

ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንድትሻገር ለዓመታት የበኩሌን አስተዋጽዖ ሳደርግ መቆየቴ ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ ግን፣ ተረኛው ጨቋኝ መንግስት በባልደራስም ሆነ በሃገር አቀፍ ደረጃ በፈጠረው የለየለት አምባገነናዊ ጫና ሳቢያ፣ በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ።
በመሆኑም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ አባላት፣ በየደረጃው ያሉ የፓርቲው አመራር አባላት፣ መላ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ከፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምሃ ዳኘው ጋር ሙሉ ለሙሉ በመተባበር ስራቸው የተቃና እንዲሆን እንድትተባበሯቸው በትህትና እጠይቃለሁ።
በመጨረሻም፣ እቅድ የተያዘለት የባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ዝግጅት እንዲከናወን ያለኝን ብርቱ ተስፋ እየገለጽኩ፣ ባልደራስ በሃገር አቀፍ ፓርቲነት አድጎ የማየት ተስፋችን ወደ ተግባር ተተርጉሞ ለማየት የፈጣሪ መልካም ፈቃድ ይሁን።

ከሰላምታ ጋር
እስክንድር ነጋ