Get Mystery Box with random crypto!

Amhara times

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharatimes1 — Amhara times A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharatimes1 — Amhara times
የሰርጥ አድራሻ: @amharatimes1
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.72K
የሰርጥ መግለጫ

ኑ ለኢትዮጵያ እንታገል
መረጃ በ @Amhratimesbot ልታደርሱኝ ትችላላችሁ

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 21:18:56 ሰበር ዜና!

ዋጃ ከተማ በጥምር ጦሩ ቁጥጥር ስር ዋለች።ዋጃ ከቆቦ ቀጥላ የምትገኝ ከተማ ነች። መከላከያው አሁን ወደ አላማጣ እየገሰገሰ ይገኛል። የስንቅናየትጥቅ ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥል!
1.7K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:55:35
2.1K views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:53:56 ሠራዊቱ ሕወሓት የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በብቃት እየመከተ መሆኑን መንግሥት ገለጸ

የሀገር መከላከያ ሠራዊት አሸባሪው ሕወሓት የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በተሟላ ብቃት በመመከት ላይ እንደሚገኝ መንግሥት ገለጸ።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በዚህም አሸባሪው ሕወሓት የተዘረጋለትን የሰላም አማራጭ ረግጦ ለሶስተኛ ጊዜ የከፈተውን ወታደራዊ ጥቃት አጠናክሮ መቀጠሉን መንግሥት አስታውቋል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ ለሰላም የተዘረጋውን መንገድ ትቶ፤ ለጦርነት ሲዘጋጅ መቆየቱ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

አሁንም በተለያዩ ግንባሮች የከፈተውን ጥቃት አድማሱን በማስፋፋት ለፍቶ አዳሪ ንጹሐን ዜጎችን ዒላማ እያደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡ ጊዜ ያለፈበትን የሰው ማዕበል የጦርነት ስልት በመከተል በሺዎች የሚቆጠሩ አዳጊዎችንና ወጣቶችን በገፍ እየማገደ፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

አሸባሪው ሕወሓት ግድያ፣ ማፈናቀል፣ የንብረት ማውደም፣ መሠረተ ልማት የማፈራረስና መሰል የጭካኔ ተግባራትን ለመፈጸም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ኃይል አሰባስቦ ወደ አማራና አፋር ክልል አዋሳኞች እየተንቀሳቀሰ ነው ብሏል መንግሥት። መንግሥት የዘረጋው የሰላም አማራጭ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይህ አሸባሪ ቡድን የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በተሟላ ብቃት በመመከት ላይ ይገኛል።
 
2.1K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 12:17:31 ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተላለፈ ጥሪ!

የትግራይ ወራሪ ሃይል በራያ ግንባር ጦርነት ከፍቷል። በራያ ግንባር በምዕራብ በኩል በጀመዶ መሃጎ እና ወደ ጊዳን መስመር ከፍተኛ ዉጊያ ከፍተዋል። በራያ ግንባር በምስራቅ በኩል ወደ አፋር ድንበር አካባቢ ቦተሊ እንዲሁ ጦርነት ከፍቷል።

ስለሆነም ሁሉም ህዝባችን ከጥምር ሃይሉ (መከላከያ ልዩ ሃይል ፋኖ እና ሚሊሻ) ጎን በመሆን በትጥቅና ስንቅ ጭምር ደጀን እንዲሆንና ትግሉን እንዲቀላቀል ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
3.3K views09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 09:22:24
Hands that are Greening a Nation:
4.5K views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 10:58:43
4.4K views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 10:58:42
4.1K views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 10:54:58
#BREAKING

ሶስተኛው ዙር ሙሌት በስኬት ተጠናቀቀ።

የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሶስተኛው ዙር ሙሌት በስኬት ተጠናቆ ውሃ በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የግድቡን ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ለማብሰር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገኘታቸውን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።
3.8K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 08:41:02 # ሰበር ዜና---
/
"በመንግስት ጫና በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ" -እስክንድር ነጋ

የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ ሀምሌ 16፣2014 ዓመተ ምህረት ካሉበት ቦታ በጻፉት ደብዳቤ፣ ተረኛና ጨቋኝ መንግስት በፈጠረው ጫና ሳቢያ በፓርቲያቸው በአመራርነትም ሆነ በአባልነት መስራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ይፋ አደረጉ። የደብዳቤያቸው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። ፊርማቸው ያረፈበት የአጅ ጽሁፋቸውም ከዚህ ደብዳቤ ጋር ተያይዟል።

/
ሀምሌ 16፣ 2014
/
ለባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
/

ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንድትሻገር ለዓመታት የበኩሌን አስተዋጽዖ ሳደርግ መቆየቴ ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ ግን፣ ተረኛው ጨቋኝ መንግስት በባልደራስም ሆነ በሃገር አቀፍ ደረጃ በፈጠረው የለየለት አምባገነናዊ ጫና ሳቢያ፣ በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ።
በመሆኑም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ አባላት፣ በየደረጃው ያሉ የፓርቲው አመራር አባላት፣ መላ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ከፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምሃ ዳኘው ጋር ሙሉ ለሙሉ በመተባበር ስራቸው የተቃና እንዲሆን እንድትተባበሯቸው በትህትና እጠይቃለሁ።
በመጨረሻም፣ እቅድ የተያዘለት የባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ዝግጅት እንዲከናወን ያለኝን ብርቱ ተስፋ እየገለጽኩ፣ ባልደራስ በሃገር አቀፍ ፓርቲነት አድጎ የማየት ተስፋችን ወደ ተግባር ተተርጉሞ ለማየት የፈጣሪ መልካም ፈቃድ ይሁን።

ከሰላምታ ጋር
እስክንድር ነጋ
3.3K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 12:19:28 #ሰበር

ከክልል አደረጃጀት ጋር በተያያዘ በወልቂጤ ከተማ የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ነው። ከተማው ሙሉ በሙሉ ፀጥ ብሏል። የአድማው ጠሪ ሆኖ የመጣ አካል ባይኖርም በትላንትናው እለት ወረቀት ተበትኖ ነበረ።

በተያያዘ ዜና ቆሴ ከተማ ከትላንትና ጀምሮ ከሀዲያ ዞን በመጡ ወጣቶች ሰዎች ተደብድበዋል፣ ሱቆች ተዘርፈዋል፣ ጉራጌዎች " ክላስተሩን ካልደገፋችሁ ከተማውን ለቃችሁ ውጡልን" እየተባሉ እንደሆነ እየገለፁ ነው።
2.6K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ