Get Mystery Box with random crypto!

በጽናት ለድል እንበቃለን! እናሸንፋለንም! እድሜ ዘመኑን ሙሉ ከሰላም ይልቅ ጦርነትን እንደ መልካ | Amhara Police Commission

በጽናት ለድል እንበቃለን! እናሸንፋለንም!

እድሜ ዘመኑን ሙሉ ከሰላም ይልቅ ጦርነትን እንደ መልካም አማራጭ የሚቆጥረው ውያኔ በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ዳግም ወረራ ፈጽሟል።

ወራሪው ቡድን ከኢትዮጵያ ሰላም ይልቅ መከፋፈልን፣ ከህዝብ አንድነት ይልቅ ጥላቻና ልዩነትን ዘርቶ ሲኮተኩትና ሲንከባከብ የኖረ ቡድን ነው። ጥፋትን እንጂ ፈጽሞ የሰላም መንገድን መርጦም ሆነ ተከትሎ አያውቅም።

የዚህን የሽብር ቡድን ወረራ ለመቀልበስ ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይላችን፣ ሚሊሺያና ፋኖ በጀግንነት እና በቆራጥነት ስሜት እየተፋለመ ነው። የውያኔን ቀቢጸ ተስፋ አምክኖ ለድል መብቃት በሚችልበት አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የክልላችን ህዝብና መላ ኢትዮጵያውያን የጠላትን የተለመደ ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ወደጎን በመተው ከጠላት ጋር እየተፋለመ ለሚገኘው ጥምር ጦር ህዝባዊ ደጀንነታችሁ እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብሁ፤ በአንድነትና በጽናት የጠላትን እንቅስቃሴ ቀልብሰን በቅርብ ለድል እንበቃለን። እናሸንፋለንም።

ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ርእሰ መሥተዳድር

ኢትዮጵያና እና ልጆቿን ፈጣሪ ይባርክ!