Get Mystery Box with random crypto!

'ኢትዮጵያዊ ጀግንነታችን የማይነጥፍ ነው!!' በግዳጅ ቀጠና የሚገኙ የዕዝ ዋና አዛዥ ሀገራችን | Amhara Police Commission

"ኢትዮጵያዊ ጀግንነታችን የማይነጥፍ ነው!!" በግዳጅ ቀጠና የሚገኙ የዕዝ ዋና አዛዥ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ የማንንም ሀገር ወራና ተተናኩሳ አታቅም ያሉት የዕዝ ዋና አዛዥ የውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን ሉአላዊነቷን ለመዳፈር እና ሕዝቦቿን ለማሰቃየት ሁሌም ይጥራሉ ግን አይሳካላቸውም ብለዋል።

የጀግኖች ሀገር ኢትዮጵያ ተሸንፋም ተንበርክካም አታውቅም ፤ በእኛም ዘመን አትደፈርም በቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ትከበራለችም ብለዋል።

ጠላት የቱንም ያህል ቢፎክር በስነ ልቦናም ይሁን በማቴሪያል ዝግጁነታችንን አጠናክረን ትላትን የፈፀምነውን ገድልና ጀግንነት ማስቀጠልና ድል ማስመዝገብ የሚችል አስተማማኝ ኀይል ፈጥረናል።

ኢትዮጵያን ነክቶ በሰላም የተኛ የለም ያሉት የዕዙ ዋና አዛዡ ጠላቶቻችን እስኪጸጸቱ ድረስ በለኮሱት እሳት ወደ አመድነት የሚቀይራቸው የመከላከያ ኃይል አፍርተናል ብለዋል። መረጃው የመከላከያ ሰራዊት ነው።