Get Mystery Box with random crypto!

Amhara Police Commission

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharapolicecommission — Amhara Police Commission A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharapolicecommission — Amhara Police Commission
የሰርጥ አድራሻ: @amharapolicecommission
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.41K
የሰርጥ መግለጫ

Peace keeper

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 21:08:09
በጽናት ለድል እንበቃለን! እናሸንፋለንም!

እድሜ ዘመኑን ሙሉ ከሰላም ይልቅ ጦርነትን እንደ መልካም አማራጭ የሚቆጥረው ውያኔ በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ዳግም ወረራ ፈጽሟል።

ወራሪው ቡድን ከኢትዮጵያ ሰላም ይልቅ መከፋፈልን፣ ከህዝብ አንድነት ይልቅ ጥላቻና ልዩነትን ዘርቶ ሲኮተኩትና ሲንከባከብ የኖረ ቡድን ነው። ጥፋትን እንጂ ፈጽሞ የሰላም መንገድን መርጦም ሆነ ተከትሎ አያውቅም።

የዚህን የሽብር ቡድን ወረራ ለመቀልበስ ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይላችን፣ ሚሊሺያና ፋኖ በጀግንነት እና በቆራጥነት ስሜት እየተፋለመ ነው። የውያኔን ቀቢጸ ተስፋ አምክኖ ለድል መብቃት በሚችልበት አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የክልላችን ህዝብና መላ ኢትዮጵያውያን የጠላትን የተለመደ ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ወደጎን በመተው ከጠላት ጋር እየተፋለመ ለሚገኘው ጥምር ጦር ህዝባዊ ደጀንነታችሁ እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብሁ፤ በአንድነትና በጽናት የጠላትን እንቅስቃሴ ቀልብሰን በቅርብ ለድል እንበቃለን። እናሸንፋለንም።

ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ርእሰ መሥተዳድር

ኢትዮጵያና እና ልጆቿን ፈጣሪ ይባርክ!
1.6K viewsNatnael Tibebu, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 17:04:45
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ አስቀመጠ፦

ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ የማይችል መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን ይመልከቱ!!
https://t.me/joinchat/AAAAAFic4YUKzCmrKYI8YA

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሊንኩን በመጫን
https://yt6.pics.ee/3z7l7q
1.8K viewsNatnael Tibebu, 14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 16:36:11 ʺ ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ነው" የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብል

ዋና አስተዳዳሪው ሁሉም ከዳር ዳር በመነሳት እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሕወሃት የሽብር ቡድን በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ዳግም ወረራ ከከፈተ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡

ሕዝብን ጠላት አድርጎ የተነሳው የሽብር ቡድኑ ወረራ በከፈተባቸው አካባቢዎች በደሎችን እየፈጸመ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችም የጠላትን ሕልም ለማምከንና ሀገራቸውን ለማጽናት እየተዋደቁ ነው፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስታዳደሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብል የሕወሃት የሽብር ቡድኑ ለሰላም የቀረበለትን አማራጭ ወደጎን በመተው ዳግም ጦርነት መክፈቱን ገልጸዋል፡፡

ጦርነቱን ጀምሮ መንግሥትን መክሰሱንም ተናግረዋል፡፡ ጠላት ከጦርነት ውጭ ሌላ ሥራ እንደሌለው ጠንቅቀን እናውቃለን ያሉት ዋና አስተዳደሪው፤ ዋነኛ ጠላታችን እንደሆነ በማንሳት መመከት የሚያስችል ውይይትና ዝግጅት ስናደርግ ቆይተናልም ብለዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ የከፈተውን ዳግመኛ ወረራ ለመመከት የመከላከያ ሠራዊት አስደናቂ ተጋድሎ ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻውና ፋኖው ጠላትን እያረገፈው እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ሕዝቡ ለጀግናውን ተዋጊ ኃይል እውነተኛ ደጀን እንዲሆን እየሠሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ማኅበረሰቡ እያደረገው ያለው አስተዋጽዖ የሚደነቅ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የፈለገው ቢሆን ጠላት ሊያሸንፈን አይችልም፣ ጠላት የትም አይደርስም፣ ይህን የሚያደርግ ሥራ እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

ጦርነቱ ባለበት አካባቢ ያለው ማኅበረሰብ በእልህና በወኔ ተነስቶ ጠላትን እየተፋለመ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የዞኑ የሥራ ኃላፊዎች ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የራያ ጀግኖች አካባቢያችንን አንለቅም ብለው ከጠላት ጋር እየተዋደቁ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

አብዛኛው ማኅበረሰብ ከአሁን ቀደም ከነበረው ወረራ ትምህርት በመውሰድ ከጠላት ፕሮፓጋንዳና የሐሰተኛ መረጃዎች ራሱን እየጠበቀ እንደሆነ የተናገሩት ዋና አስተዳደሪው።

ጠላት ደረሰብን እንጂ አልደረስንበትም፣ የትኛውም ማኅበረሰብ አካባቢውን ለቅቆ የትም መሄድ የለበትም፣ በጀግንነት መታገል አለበት፣ ታግሎ ማሸነፍ አማራጭ የሌለው ምርጫ ነውም ብለዋል፡፡

ሁሉም ከዳር ዳር በመነሳት መታገል እንደሚገባውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጀግኖቻችን በማጀገንና ከአሉባልታ በመቆጠብ ጠላትን መምታት ይገባልም ብለዋል፡፡

ለሕዝብ መድረስ ያለበትን መረጃ እናደርሳለን ያሉት ዲያቆን ተስፋው፤ ከዚያ ውጭ ባሉ ጠላት በሚያሰራጫቸው አሉባልታዎች መደናገር እንደማይገባም ገልጸዋል፡፡ ጠላት በተቀላቢ የማኅበራዊ ሚዲያ አርበኞቹ የተሳሳተ የጦርነት ዘገባና ሌሎች አሉባልታዎችን እንደሚያስተላልፍ መታወቅ አለበትም ብለዋል፡፡

በማኅበራዊ ሚደያ አሉባልታዎችን የሚያስተላልፉ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡ ማኅበረሰቡ ከበሬ ወለደ ወሬ ራሱን እንዲጠብቅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጦርነት ወደ ፊትም፣ ወደ ኋላም ሊል ይችላል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ነው፣ ከማኅበረሰቡ የሚጠበቀው ተዋጊውን ኃይል ማጀገን ነው፣ የፈለገ ቢሆን ጠላት የትም ሊደርስ አይችልም ነው ያሉት፡፡

ማኅበረሰቡ ከደጀንነት ባለፈ ተዋጊ ኾኖ ጠላቱን መቅጣት አለበት ብለዋል፡፡ ያለ መስዋዕትነት ድል እንደማይመጣም ገልጸዋል፡፡

በአሸናፊነት ስነ ልቦና የተገነባ ማኅበረሰብ ማሸነፉ አይቀርምም ብለዋል፡፡ ከዚሕ በኋላ ከጠላት ጋር መለሳለስ እንደማይገባም ገልጸዋል፡፡

ለጠላት ግብዓት የሚያቀብሉ ባንዳዎች እንዳሉ ያነሱት ዋና አስተዳደሪው እውነተኛ አማራ፣ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሆነን ምንም ነገር ለጠላት እንዳይደርሰው በማድረግ መቅጣት ይገባል ነው ያሉት፡፡

የሽብር ቡድኑ የመጨረሻ ጠላታችን ነው፣ በአንድ ልብ ቆመን፣ ሃብትና ጥቅማጥቅም ሳይደልለን ጠላትን መዋጋት መቻል አለብንም ብለዋል፡፡

ዘገባው የአሚኮ ነው
1.8K viewsNatnael Tibebu, 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 16:36:06
1.5K viewsNatnael Tibebu, 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 16:18:48
"ኢትዮጵያዊ ጀግንነታችን የማይነጥፍ ነው!!" በግዳጅ ቀጠና የሚገኙ የዕዝ ዋና አዛዥ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ የማንንም ሀገር ወራና ተተናኩሳ አታቅም ያሉት የዕዝ ዋና አዛዥ የውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን ሉአላዊነቷን ለመዳፈር እና ሕዝቦቿን ለማሰቃየት ሁሌም ይጥራሉ ግን አይሳካላቸውም ብለዋል።

የጀግኖች ሀገር ኢትዮጵያ ተሸንፋም ተንበርክካም አታውቅም ፤ በእኛም ዘመን አትደፈርም በቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ትከበራለችም ብለዋል።

ጠላት የቱንም ያህል ቢፎክር በስነ ልቦናም ይሁን በማቴሪያል ዝግጁነታችንን አጠናክረን ትላትን የፈፀምነውን ገድልና ጀግንነት ማስቀጠልና ድል ማስመዝገብ የሚችል አስተማማኝ ኀይል ፈጥረናል።

ኢትዮጵያን ነክቶ በሰላም የተኛ የለም ያሉት የዕዙ ዋና አዛዡ ጠላቶቻችን እስኪጸጸቱ ድረስ በለኮሱት እሳት ወደ አመድነት የሚቀይራቸው የመከላከያ ኃይል አፍርተናል ብለዋል። መረጃው የመከላከያ ሰራዊት ነው።
1.7K viewsNatnael Tibebu, 13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:38:23
"የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል የጠብ አጫሪውንና የአሸባሪውን የትህነግ ኀይል ወረራ ለመመከት ሁሌም በተጠንቀቅ ላይ ነው!!" ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ወልድያ ከተማ ወደ ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማነት የማደግ ይፋዊ የእውቅና መርሐግብር ላይ ከተናገሩት የተወሰደ።

ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን ይመልከቱ!!
https://t.me/joinchat/AAAAAFic4YUKzCmrKYI8YA

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሊንኩን በመጫን
https://yt6.pics.ee/3z7l7q
2.3K viewsNatnael Tibebu, 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 16:56:53
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ለከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች የስራ ኀላፊነት ሰጠ

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሸንን በአዲስ ለማደራጀት አዲስ ኮሚሽነር እና ለምክትል ኮሚሽነሮች ሹመት መሰጠቱ ይታወሳል። የዚሁ አካል የሆነው ምደባው ቀጥሎ በተቋሙ የምክትል ዘርፍ ኀላፊነት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች የስራ ኀላፊነት ሰጥቷል።

1. ረዳት ኮሚሽነር አበበ ዉቤ የአድማ መከላከል እና ልዩ ጥበቃ ምክትል ዘርፍ ኀላፊ በአሉበት ኀላፊነት የቀጠሉ

2. ረዳት ኮሚሽነር ደረጀ አቻምየለህ የማህበረሰብ አቀ/ወ/መ እና ትራፊክ ም/ዘርፍ ኀላፊ

3. ረዳት ኮሚሽነር መላኩ ሲሳይ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዘርፍ ኀላፊ

4. ኮማንደር ክንዱ ወንዴ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ምክትል ዘርፍ ኀላፊ ሆነው ከነሀሴ 18/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተመድበዋል።
2.4K viewsNatnael Tibebu, 13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:08:42 https://yt6.pics.ee/4ewthb
2.1K viewsNatnael Tibebu, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:36:19 አሸባሪው ህወሓት ቡድን ወደ ትግራይ ክልል ሊያስገባ የነበረው አደገኛ ዕፅ ተያዘ
**

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከአዲስ አበባ እስከ ሚሌ ኔትወርክ በመዘርጋት በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ክልል ሊያስገባው የነበረ በርካታ ኩንታል አደገኛ ዕፅ በህብረተሰቡ ጥቆማ እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

ሁለት ተጠርጣሪዎች በሰሌዳ ቁጥር አ.አ ኮድ 3-A40101AA ቶዮታ ዶልፊን ተሽከርካሪ ላይ አደገኛ ዕፁን ጭነው ሲያጓጉዙ በህብረተሰቡ በተሰጠው ጥቆማ መሰረት ከሌሎች የፀጥታ እና ደህንነት አካላት ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅሷል።

ከአደገኛ ዕፁ በተጨማሪ ለእኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ ሊውል የነበረ ሁለት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰባ ሺህ ብር (2,370,000.00 ብር) መያዙንም ገልጿል።

በህወሓት የሽብር ቡድን አባልነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በሚጠየቁበት ጊዜ አደገኛ ዕፁን የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ወደ ትግራይ ክልል ለማስገባት እንደሆነ ተናግረው ዕፁን ለመቀበል የተዘጋጀ ቡድን እንዳለም ጠቁመዋል።

ፖሊስም ይህንን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል በክትትል ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ይህ የሽብር ቡድን ዕፁን ሊያስተላልፍ የነበረው እንደለመደው የትግራይ ወጣቶችን በዕፅ አደንዝዞ ወደ ጦርነት ለመማገድ እንደነበረ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎቹ ተናግረዋል።

ይህ አደገኛ ዕፅ የተያዘው በህዝቡ ጥቆማና ቀና ትብብር በመሆኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋናውን እያቀረበ በየትኛውም ደረጃ የሚወጠኑ መሰል የወንጀል ተግባራትን ለመቆጣጠር ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ተገቢውን ቅንጅት በማድረግ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

EBC
2.2K viewsNatnael Tibebu, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 15:52:47
ለህወሃት የጦር መሳሪያ ጭኖ የኢትዮጵያ የአየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን መምታቱን አየር ኃይሉ አስታወቀ

የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የአየር ክልላችንን ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ ወድቋል::

ሠራዊቱ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።

በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የሀገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም ነው ያነሱት።

ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ትናንት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል።

በዚህም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ሃይልች እየተለበለበ ነው ብለዋል።

ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን ይመልከቱ!!
https://t.me/joinchat/AAAAAFic4YUKzCmrKYI8YA
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሊንኩን በመጫን
https://yt6.pics.ee/3z7l7q
2.5K viewsNatnael Tibebu, 12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ