Get Mystery Box with random crypto!

Ahmed Habib Alzarkawi

የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi
የሰርጥ አድራሻ: @alzarkawihabib
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.53K
የሰርጥ መግለጫ

Hello World

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-17 18:20:18 እንኳን ደስ አለን ...

ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር ከ566 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል የራሷን ሪከርድ መስበሯን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ
7.7K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 17:54:48
አፋር-ለሀገር የሚጠቅም የትኛውም ነገር ከማድረግ ወደኋላ የማይል ህዝብ....
7.8K views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-15 20:31:29 ስለ ሱልጣን አሊሚራህ የሳዑዲ ንጉስ ፈሃድ የሰጡት ምስክርነት...

በአንድ ወቅት ሱልጣን አሊሚራህ በሳዑዲ ሪያድ ከተማ ከሳዑዲ ሰልጣን ማለትም ከመሊክ ፋይሰል ጋር በተገናኙ ጊዜ መሊክ ፋሃድ ለሱልጣን አሊሚራህ እንዲህ አሏቸው " ሱልጣን አሊሚራህ ሆይ! ከመሊክ ፈይሰል ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ለብዙ አመታት ተመልክቾታለሁ። የአንተ ፊት አይቀየርም ሁሌ በኑር እንደተሞላ ነው። እባክዎትን ምስጢሩ ምን ይሁን ብሎ ጠየቃቸው። በዚህ ጊዜ ሱልጣኑ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው። እኔ በባንክ ያጠራቀምኩት ገንዘብ የለኝም ። እንቅፍ የሚነሳኝ ድርጅት የለኝም። ስለዚህ የሚያሳስብኝ ከዱንያ ይልቅ የአኼራ ጉዳይ ስለሆነ ትዕዛዙን ለመፈፀም ብቻ ነው የሚተጋው ብሎ እንደመለሱላቸው በወቅቱ አብሮት የነበሩ ሠው ነገሩኝ። በዚህ ጊዜ የሳዑዲ ንጉስ መሊክ ፋሃድ እውነትህን ነው እኛ በሚያሳሰበን ብዙ ነገር ውስጥ ገብተን ነው እንዲህ ለመሆን ያልታደልነው ስሉ " መለሱላቸው። .====

=== ሌላኛው የሳኡዲ የዘመኑ ታዋቂ ባለሐብት ደግሞ " ገንዘብ አገኘን ነገር ግን ጤና አጣን " ብሎ ለሱልጣኑ መናገራቸውም ተሰምተዋል።
አዎ ሱልጣን አሊሚራህ ገንዘብ በእጃቸው ሳይነኩ ፣ ሳይቆጥሩ ነው የሞቱት። እንደ ኢትዮጵያ ንጉሶች ፣ እንደ ህወሓት መሪዎች ፣ እንደአፋር አመራሮች የሀገር ሀብት ፣ የህዝብ ሀብት በስልጣናቸው ተጠቅመው ከድሃ ጉሮሮ ነጥቀው ጎረቤት ሀገርና አውሮፓ ድረስ ይዘው አልሸሹም ። አልፎም በሚስቶቻቸው ፣ በልጆቻቸው ፣ በወንድሞቻቸው ስም ከህዝብ በነጠቁት ገንዘብ ሆቴልና ፈብሪካ ገንብተው ድንጋይ ላይ ድንጋይ ገንብረው ህንፃ አንፀው በታሪክም ሆነ በሚመሩት ህዝብ ዘንድ አልፎም ለህሊና ፍርድ አንገት ደፍተው ለቁጭት የሚዳረጉበት አንገት የሚያስደፋ ጥቁር ታሪክ አለስመዘገቡም። የአፋር ሱልጣን በምድሩ ቆይታቸው እንደተወደሱ ፣ እንደተከበሩ ከሚመሩት ህዝብ ጉሮሮ ነጥቀው አንዳች ህንፃና ፈብሪካ ሳይገነቡ ለገንዘብና ለሐብት ጀርባ እንደሰጡ እንደተጠየፉ ይህን ምድር ተሰናበቷት።

ሱልጣን አሊሚራህ ማለት በኢኮኖሚ በአለም በቱጃሮች ተርታ የምትሰለፈውን የሳዑድ አረቢያ ንጉስ መሊክ ፋሃድ ተማርኮባቸው የተደመመሙበት ስብዕና ተላብሰው የተወደዱ የጀግና ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ሱልጣን አሊሚራህ እንዲህ አይነት ጀግና አባት ጀግና መሪ ነበሩ።

ምንጭ፦ የታሪክ ፀሃፊ Allo Yayo Abu Hisham
8.4K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-15 20:31:28
7.9K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 19:00:29
ኤርትራ ዳግም ወደ ኢጋድ ተመለሰች

ኤርትራ ከ16 ዓመታት በኋላ ዳግም የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (IGAD) መድረክን መቀላቀሏን ይፋ አደረገች ። ኤርትራ የኢጋድ አባልነቷን ያቋረጠችው እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2007 ዓ.ም ነበር ። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል ኤርትራ የኢጋድ አባልነትዋን መቀጠሏን ትናንት በይፋዊ የትዊተር የመገናኛ አውታር ገጻቸው ጽፈዋል።

ኤርትራ በመድረኩ የአባልነቷ እንቅስቃሴዋን ዳግም ማስቀጠሏን እና ጅቡቲ በተካሄደው በ14ተኛው የኢጋድ መደበኛ ጉባኤ ላይ መካፈሏንም አክለዋል ። አቶ የማነ ኤርትራ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችበትን ምክንያት ባይገልጹም፣ ከሌሎች የኢጋድ አባል ሃገራት መቀላቀልና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲስፈን ለማገዝ መፈለጓን ጠቅሰዋል። የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ስምንት አባላት ሲኖሩት፦ እነሱም ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እና ዳግም የተመለሰችው ኤርትራ ናቸው ። ኤርትራ ከ16 ዓመታት በፊት ከኢጋድ ራሷን ያገለለችው የኢትዮጵያ ወታደሮች ሶማሊያ መግባታቸውን በመቃወም ነበር ።
10.0K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 18:54:49
የከዕአባ በር በትላንትናው እለት ተከፈተ....

ሁጃጆች ( ሰጋጆች) እንዲያዩት።

አሏህ ሆይ ከጎብኚዎቹ ጻፈልን አሚን !!

فتح باب الكعبة ليلة أمس ليراها المصلين

اللهم اكتبنا من زوارها
9.0K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 21:46:38
ኢጋድ፤ የዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን ዋና ጸሀፊነት ለተጨማሪ አራት ዓመታት አራዘመ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የዋና ጸሀፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን የስራ ዘመን ለተጨማሪ አራት ዓመታት አራዘመ። የቀድሞው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢጋድ ዋና ጸሀፊነታቸው እንዲቀጥሉ የተወሰነው፤ ዛሬ ሰኞ ሰኔ 5፤ 2015 በጅቡቲ በተካሄደው የድርጅቱ መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ነው።

ከመሪዎቹ ውሳኔ በኋላ ዶ/ር ወርቅነህ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “ጉባኤው በእኔ ላይ ሙሉ መተማመን አሳድሮ የስልጣን ዘመኔን ለሁለተኛ 4 አመት ስላራዘመልኝ ጥልቅ ደስታ ይሰማኛል” ብለዋል። ዶ/ር ወርቅነህ ኬንያዊውን ማህቡብ ማሊምን በመተካት የኢጋድ ዋና ጸሀፊነት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት በህዳር 2012 ዓ.ም ነበር።

በዛሬው የኢጋድ ስብሰባ፤ አባል ሀገራት በዙር በሚደርሳቸው የሊቀመንበርነት ኃላፊነት ስልጣን ላይም ለውጥ ተደርጓል። ላለፉት አራት ዓመታት ኢጋድን በሊቀመንበርነት ስትመራ የቆየችው ሱዳን የዛሬውን ጉባኤ ላስተናገደችው ጅቡቲ ኃላፊነቱን አስረክባለች። ኢትዮጵያ  ይህን የኃላፊነት ቦታ ለሱዳን አሳልፋ ከመስጠቷ በፊት ለዘጠኝ ዓመታት ኢጋድን በሊቀመንበርነት መምራቷ ይታወሳል።

በጅቡቲ በተካሄደው በዛሬው የመሪዎች ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ የጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ተሳትፈዋል። በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እና በሶማሊያ ጉዳዮች ላይ በዋነኛነት በመከረው በዚህ ስብስባ ላይ፤ ኤርትራ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኦስማን ሳለህ ተወክላለች።

ኢትዮጵያን ኢንሳይደር
10.0K views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 21:43:52
ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ናት የባህር በር ሊኖራት ይገባ ነበር..ግን ምን ዋጋ አለው በውስን ግለሰቦች ተራ ፎርሙላ Landlocked ሆና ቀረች..
8.2K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 13:17:07
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

#Ethiopia | ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የቀድሞ የአየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄን በመተካት ነው የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢነት የተሾሙት፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ግርማ ዋቄ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
9.7K views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 10:24:41 ኢንዶሚ ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው
በአገራችን በህጋዊ መንገድ ከውጪ አገር የሚገባ የኢንዶሚን ምርት የለም ተብሏል

በካንሰር የመያዝ እድልን የሚያስከትል ንጥረ ነገርን ይዟል በተባለው ኢንዶሚን ኑድልስ ላይ የተለያዩ አገራት ምርመራ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ማሌዥያና ታይዋን በኢንዶሚን ላይ “ኢቲሊን ኦክሳይድ” የተባለውን ካንሰር አምጪ ንጥረ ነገር በማግኘታቸው ምርቶቹን ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን፣ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ከውጪ አገር የሚገባ የኢንዶሚን ኑድልስ ምርት አለመኖሩን አመልክቷል፡፡ የባለስልጣኑ ምግብ ተቋማት ቁጥጥር ሃላፊ አቶ በትረ ጌታሁን ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በባለስልጣኑ ተመዝግቦ በህጋዊ መንገድ ከውጪ አገር የሚገባ ኢንዶሚን የተባለ ምርት አለመኖሩን ጠቁመው፤ በአገር ውስጥ የሚመረትና በባለስልጣኑ ቁጥጥር የሚደረግበት ምርት አለ ብለዋል። ጉዳዩ እንደተሰማ በዚሁ የአገር ውስጥ ምርት ላይ ምርመራ መደረጉን የገለፁት ሃላፊው በምርቱም ላይ የተባለውን ዓይነት ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር አለመገኘቱን አመልክተዋል፡፡በካንሰር የመያዝ እድልን ያስከትላል የተባለውን ንጥረ ነገር ይዟል በተባለው የኢንዶሚን ምርት ላይ ምርመራ ማድረግ ከጀመሩ የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ናይጄሪያ ስትሆን፤ ከኢንዶሚን ኑድልስ ምርት የተለያዩ ናሙናዎችንና ቅመማ ቅመሞችን በመውሰድ ኢቲሊን አክሳይድ የተባለው ንጥረ ነገር መኖር አለመኖሩን ለማወቅ ምርመራ እያደረገች መሆኑን አስታውቃለች፡፡በማሌዥያና ታይዋን ልዩ የዶሮ ጣዕም ባለው የኢንዶሚን ምርት ላይ ካንሰር አምጪው አደገኛው ንጥረ ነገር በመገኘቱ ምርቶቹ ከገበያ እንዲሰበሰቡ ተደርገዋል፡፡
ኢንዶሚን የተባለውን ኑድልስ የሚያመርተው የኢንዶኔዥያው ግዙፍ የምግብ አምራች ተቋም “ኢንዶፍድስ” የምግብ ምርቱ ጤናማ መሆኑን በመግለፅ እየተከራከረ ነው፡፡
6.6K views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ